2017-07-20 15:28:00

የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት የአገራቸው ሕዝባዊ ምርጫ ግልጽና ነጻ እንዲሆን በማለት ጥሪ አቀረቡ


እ.ኤ.አ. ነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በኬንያ የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ ሰላማዊ ነጻና ግልጽ ታማኝ እንዲሆኑ የአገሪቱ በፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ በይፋ ጥሪ ማቅረባቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው ኅትመት አስታወቀ።

በኬንያ የሚገኙት የሁሉም ሃይማኖት መንፈሳዊ መሪዎች በዚህ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በርእሰ ከተማ ናይሮቢ አካሂደዉት ከነበረው ስብሰባ ፍጻሜ በኋላ ይፋ ባደረጉት የጋራ ጥሪ የአገራቸው መንግሥት ሊካሂድ ታቅዶ ያለው ህዝባዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ በተረጋጋ መንፈስ እንዲካሄድ የማድረግ ኃላፊነት አለበት ስለዚህ ይኽንን ኃላፊነቱንም በሚገባ ሊወጣ ይገባዋል ማለታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ፥ ምርጫው ታማኝ እንዲሆን የምርጫው ተቆጣጣሪ አካል ታማኝ የሚያሰኘው መመዘኛውን በመከተል ምርጫው በሚካሄድበት ወቅት ብቻ ሳይሆን ከምርጫው በኋላ ምንም አይነት ዓመጽ እንዳይከሰት ከወዲሁ ቀድሞ የመጠንቀቅ እቅድ ወጥኖ የምርጫው ሰላማዊ ሂደቱን በሚገባ በመከላከል ዋስትና እንዲሰጥና የምርጫው ሂደት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በመቆጣጠር የምርጫው ውጤት ሁሉም የሚያሳምን ሁሉም ካለ ምንም መጠራጠርን መወነጃጀል እንዲቀበለው የሚያደርግ ግልጽነት የተካነ አሰራር እንዲከተል አደራ ማለታቸው ይጠቁማ።

ሁሉም የመምረጥ መብት ያለው በማሳተፍ ማንኛውም ጠብ ዓመጽ ሊያነሳሳ የሚችል ተግባር እንዳይከሰት ምርጫው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሰላማዊ ሂደቱን እንዲቆጣጥርና የአገሩ የደህንነት ባለ ሥልጣን በሚገባ የሚቻለውን ሂደት በመከታተል መራጩ ሕዝብ ጥላቻንና ዓመጽን ሊቀሰቅስ የሚችል ማንኛውም አካል ከመምረጥ ተቆጥቦ አገሪቱን ለሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮና ለብልጽግና የሚሸኛትን የሕዝብና የአገር ጥቅም የሚያስቀድም አካል እንዲመርጥ የሁሉም ሀይማኖት መሪዎች ባወጡት የጋራ መግለጫ ጥሪ በማቅረብ እግዚአብሔር ለኬንያ ፍትህ፡ አንድነት፡ ሰላምና ነጻነት እና ብልጽግና ይለግስ በሚል ጸሎት ያስተላለፉት መግለጫ እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አስታወቀ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.