2017-07-17 17:49:00

ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል የታናገረው የዘሪው ምሳሌ በዋነኛነት እኛን ይመለከታል።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በእለቱ በሚነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ እንደ ኢያደርጉ ያታወቃል። ይህንንም አስተንትኖ ለመታደም በርካታ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በዚያው በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ይሰበሰባሉ።

የዚህ አስተንትኖ መርዓ ግብር አንዱ አካል በሆነው በትላንትናው እለት ማለትም በሐምሌ 9/2009 ዓ.ም. ያደረጉት አስተንትኖ በማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ 13፡ 1-23 ላይ በተጠቀሰው በታዋቂው የኢየሱስ የዘሪው ምስሌ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ኢየሱስ ይህንን ምሳሌ በመጠቀም ልባችንን መንፈሳዊ ንቃት ያደርግ ዘንድ ጥሪ ያቀርባል ብለዋል።

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!የዛሬው ቅዱስ ወንጌል ታዋቂ የሆነውን የዘሪውን ምሳሌ ያቀርብልናል። ዘሪው ኢየሱስ ነው። እኛ ከዚህ ምሳሌያዊ አገላለጽ የምንረዳው ኢየሱስ አስትያዩቱን ወይም አመለካከቱን እያቀረርብልናል እንጂ የምያስገድደን፣ በግድ ወደ እርሱ ስቦ የሚያመጣን ሳይሆን ራሱን የሚሰጠን መሆኑን ልብ እንላለን” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ቃሉ ፍሬ ያፈራ ዘንድ የሚዘራው በትዕግስትና በፍቅር ነው፣ ነገር ግን እኛ በምን ዓይነት መልኩ ነው ይህንን ቃል የምንቀበለው? በማለት ጥያቄን አንስተዋል።

በዛሬው እለት ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው የዘሪው ምሳሌ በዋነኛነት እኛን ይመለከታል በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአብዛኛውም የሚተርከው ሰለ ዘሪው ሳይሆን ስለ መሬት እንደ ሆነውም ጨምረው ገልጸዋል። ኢየሱስ ልባችን ውስጥ ጠልቆ በመግባት፣ የሚዘራው የእግዚኣብሔር ቃል በየተኛው የልባችን ክፍል ላይ እንደ ሚወድቅ ይመለከታል በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ልባችን ልክ እንደ አንድ መልካም መሬት በሚሆንበት ወቅት ሁሉ ብዙ ፍሬን ያፈራል፣ ነገር ግን አንድአንድ ጊዜ ደረቅ በሚሆንባቸው ወቅቶች ሁሉ የተዘራው ዘር ወደ ውስጥ ጠልቆ ለመግባት ይቸገራል፣ በዚህም መልኩ በልባችን ውስጥ የተዘራ ዘር ልክ በመንገድ ዳር እንደ ተዘራ ዘር ይሆናል ብለዋል።

ዛሬ ኢየሱስ በተናገረው የዘሪው ምሳሌ ላይ በተጠቀሱት መልካም መሬት በሚለው እና መንገድ የሆነ መሬት  በሚሉት ሁለት ዓይነት የመሬት ዓይነቶች መካከል የሚገኙ ሁለት ዓይነት መሬቶች አሉ በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቀዳሚነት ደረቅ የሆነ የመሬት ዓይነት እናገኛለን “ይህም ብዙ አፈር የሌለው የመሬት ዓይነት ነው ዘር ቢዘራበት ቶሎ ይበቅላል፣ ነገር ግን ብዙ አፈር የሌለው የመሬት ዓይነት በመሆኑ የተነሳ ስሩን በጥልቀት ወደ ውስጥ መዘርጋት ያዳግተዋል ብለዋል። ይህም ጥልቅ ወይም ደግሞ ሰፊ የሆነን ልብ ለሌላችውን ሰዎች ይመስላል ያሉት ቅዱስነታቸው፣ ጌታን በቶል ይቀበላል፣ መጸለይ፣ መውደድ እንዲሁም መመስከር ይፈልጋል ነገር ግን ጽናት የሌለው ልብ በመሆኑ የተነሳ በአጭሩ ይቀጫል፣ ወደ መልካም መሬትነት እንዳይቀየር የሙጥኝ ብሎ የበሚይዘው ስንፍና ምክንያት ሊሰፋ የማይችል የልብ  ዓይነት ነው፣ ኢየሱስን የሚቀበለው ሲመቸው ብቻ ነው ብለዋል።

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ በተጠቀሰው የዘሪው ምሳሌ ላይ መልካም መሬት በሚለው እና መንገድ የሆነ መሬት መካከል ከሚገኘው ደረቃማ መሬት በመቀጠል እሾኻማ የሆነ የመሬት ዓይነት ይገኛል በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ዓይነት መሬት ላይ የሚበቅሉትን መልካም የሆኑ ቡቃያዎችን እሽኽ አንቆ እንደ ሚያስቀራቸውም ገልጸዋል። ይህ እሾይ የሚለው ቃል ምንን ያመለክታል? በማለት ጥያቄን በማንሳት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም የእዚህን ዓለም አሳብና የሀብት ፍቅርን እንደ ሚያመለክት ኢየሱስ በወንጌል መጥቀሱን አስታውሰዋል።

እሾኽ ከእግዚኣብሔር ጋር የማይሄዱ አስተሳሰቦችን እንደ ሚወክል በመጥቀስ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህም በዋነኛነት የዓለም ሀብትን ለማጋበስ የሚደረጉ ሩጫዎች፣ ለራሳችን ብቻ ሀብት እና ስልጣን ለማጋበስ በመፈልግ መኖር የሚሉትን የዚህን ዓለም ጣዎቶችን እንደ ሚወክል ቅዱስነታቸው አብራርተዋል።

ውደ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ዛሬ ኢየሱስ ውስጣችንን እንድንመለከት ይጋብዘናል በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በውስጣችን መልካም የሆነ መሬት የሚገኝ ከሆነ ለዚሁ ለተሰጠን ስጦታ ከማመስገን ባሻገር በውስጣችን የሚገኙትን መልካም ያልሆኑ የመሬት ዓይነቶችን መልካም ለማድረግ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ይህንንም በሚገባ በሕይወታችን መተግበር እንችል ዘንድ ዛሬ ቀርሜሎስ በሚል መጠሪያ እያከበርናት የምንገኘው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ የእግዚኣብሔ ቃል በትህትና በመቀበል በተግባር ላይ ማዋል እንችል ዘንድ፣ ልባችንን በማንጻት በውስጣችን ያለውን ጌታ መንከባከብ እንችል ዘንድ እንድትረዳን አማላጅነቷን መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ “የእግዚኣብሔር መልአክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን ጸሎት ከምእመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ ቡኃላ ቡራኬን ስጥተው ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተንትኖ አጠናቀዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.