2017-07-15 10:28:00

የቨነዝዋላ ብፁዓን ጳጳሳት፥ መንግሥት በተቃዋሚ ዜጎች ላይ እየወሰደው ያለው እርምጃ ኢሰባአዊ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰሙ


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሉእ ጉባኤውን ያጠናቀቀው የቨነዝዋላ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባወጣው የጋራ መግለጫ  መንግሥት በተቃዋሚ ዜጎች ላይ እየፈጸመው ያለው ኢሰብአዊ ተጽእኖ አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በማቆም ሰላማዊ መፍትሔ በማፈላለጉ ምርጫ ላይ እንዲተጋ በአንድ ድምጽ ጥሪ ማቅረቡ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።

በቨነዝዋላ ተከስቶ ያለውና ዕልባት ያጣው ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊና መንግሥታዊ ቀውስ ለማፈን መንግሥት እየተከተለው ያለው ስልት ችግሩን እጅግ ከማባባስ አልፎ አገሪቱን ለቀጣይ ውጥረት ሊያጋልጣት የሚችል በመሆኑ፡ መንግሥት ይኸንን እስካሁን ድረስ ለአንድ መቶ የሚሆኑ ዜጎች ለሞት የዳረገው ሕዝባዊ ዓመጽ ለማስወገድ ሰላማዊ መንገድ እንዲከተል ጥሪ ያቀረበው የቨነዝዋላ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባወጣው ለሁሉም የአገሪቱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች በስተላለፈው መልእክት፥ መንግሥት የሚከተለው ኢሰብአዊ ተግባር በማውገዝ ሕዝብ እየተጠየቀው ያለው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሊከበር ይገባዋል። ይኽ ደግሞ የመንግሥት ተቃዊሞችን የማሳደዱና ለእስርና ለስቃይ የመዳረጉ ተግባር ሕጋዊ ባልሆኑት ከአገሪቱ መከላከያ ውጭ በተመለመሉት መሳይ መከላከያ ኃይል አባላት አማካኝነት የሚፈጸመው የሰብአዊ መብትና ክብር ጥሰት እንዲቆም ጥሪ በማቅረብ መንግሥት ያቋቋመው አዲሱ የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት አገሪቱን ወደ ፈላጭ ቆራጭ ስርዓት የሚያሸጋግር ነው በሚል አገላለጥ፡ ይኽ ሶሻሊስታዊ ማርክሳዊ ወታደራዊ መንግሥት በማቆም የሕግ ተቋም የመከላከያው ተቋም ነጻነት የሚገታ አምባ ገነናዊ መንግሥት የሚያጸና ተግባር መሆኑ የገልጠው ሕዝብ መንግሥት እየተከተለው ያለው የደሞክራሲያው ሥርዓት አፋኝ ተግባር መቋረጥ አለበት በማለት ያተነቃቃው ህዝባዊ ዓመጽ ሰላማዊ ለሕዝብና ለአገር ጥቅም ያለመ እክሰ ሆነ ድረስ ሊከበርና ሰላማዊ ምላሽ ሊያገኝ ይገባውል እንዳለ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ባጠናቀሩት ዘገባ ገልጠው፥ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም. መንግሥት የሕዝብ ተመራጮች ምክር ቤት ሽሮ እራሱ የሰየመው የሕግ የወሰኛው የባላይ ምክር ቤት ውድቅ ለማድረግና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመልሶ ሥራውን እንዲቀጥል የሚጠይቅ ሊካሄደው የታቀደው ሕዝባዊ ውሳኔ ብፁዓን ጳጳሳት በሙላት በአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በኵል ድጋፋቸውን ገሃድ በማድረግ የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል አገሩንና የህዝብ አገልጋይ መሆን አለበት ብሏል።

በመጨረሻም ብፁዓን ጳጳሳቱ በአገሪቱ ተከስቶ ያለው የሰብአዊ ችግር ለመቅረፍ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚያግዝ የሰብአዊ እርዳታ መተላለፊያ መንገድ እንዲፈቀድ ጥሪ ማቅረባቸውንም የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል። 
All the contents on this site are copyrighted ©.