2017-07-15 09:53:00

ካቶሊካውያን ክሮኣዚያና ኦርቶዶክሳውያን ሰርቢያ ቅይጡ የጋራ ድርገት


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 12ና ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅይጡ የጋራው የክሮኣዚያ ካቶሊካውያንና የሰርቢያ ኦርቶዶክሳውያን ድርገት በአገረ ቫቲካን በቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ ኣዳራሽ ስድስተኛው ዓውደ ጉባኤ በጳጳሳዊ የስነ ታሪክ ተመራማሪ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ኣባ በርናርድ አርዱራ ተመርቶ መካሄዱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ይኽ የተካሄደ ዓውደ ጉባኤ የዛጋብሪያ ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን የበፁዕ ካርዲናል አሎይዚየ ስተፒናች (እ.ኤአ. ግንቦት 8 ቀን 1898 ዓ.ም. በካራሲች የተወለዱ እ.ኤ.አ. የካቲት 10 ቀን 1960 ዓ.ም. በተወለዱባት ከተማ በሰማያዊ ቤት የተወለዱ፡ እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውልስ ዳግማዊ አማካኝነት ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፅዕና ያወጀችላቸው) ተክለ ሰብነት ላይ ያማካለ እንደነበርም የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፡ ካርዲናል ብፁዕ ሰተፒናች እ.ኤ.አ. ከ 1937 ዓ.ም. እስከ 1960 ዓ.ም. የዛጋብሪያ ሊቀ ጳጳስ በወቅቱ የመጀመሪያ ወጣት ብፁዕ ካርዲናል ለመሆን የበቁ መሆናቸውንም በማስታወስ፡ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤም የክሮአዚያ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤን በመወከል የተሳተፉት የዛጋብሪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጂሲፕ ቦዛኒች፡ የፖዘጋ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቱን ስኮቭርቸዪች የሞስታርና ዱቭኖን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ራትኮ ፐሪች፡ የክሮአዚያ የሥነ ታሪክ ተቋም አባላት የታሪክ ሊቃውንት ዩረ ክሪስቶና ማሪዮ ያረብ ሲሆን የሰርቢያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል የተገኙትም የሞንተነግሮና ሊቶራለ መጥሮፖሊታ አምፊሎሂየ የዛጋብሪያና ሉቢያና መጥሮፖሊታ ፖርፊሪየ፡ የኖቪድ ሳድናባካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢሪነይ የፓክራችና የስላቮኒያ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ጆቫን እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሥነ ምርምርና የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ድርጅት የሰርቢይ ልኡከ መንግሥት ፕሮፈሰር ዳርኮ ታናስኮቪች መገኘታቸው አስታውቋል።

ልባዊ መቀረረብና ምሉእ  ነጻነት የተኖረበት  ዓውደ ጉባኤው

ይኽ በክሮአዚያ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና የሰርቢያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቅይጡ የጋራው ድርገት ስድስተኛው ዓውደ ጉባኤ በአገረ ቫቲካን እንዲያካሂድ በመመኘት የሰርቢያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያክ ብፅዕ ወቅዱስ ኢረነይ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያቀረቡት ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ ተሰጥቶበት በቅድስት ማርታ ሕንጻ ሊካሄድ በመብቃቱና እንዲሁም የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ቅይጡ የጋራው ድርገት እንዲቋቋም በማድረጋቸውንም ምክንያት ተጋባእያኑ ቅዱስ አባታችንን በማመስገን፡ ሁሉም የቅይጡ ድርገት አባላት የካርዲናል ብፁዕ ስተፒናች ተክለ ሰብነት በዳግመ ንባብ ላይ በማተኰር ያንን ብፁዕ ተብለው እንዲታወጁም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ኃላፊነት መሆኑ በመታመን እያንዳንዱ አቢያተ ክርስቲያ ብፁዕና ከዛም ቅዱስ ብሎ ለማወጅ የሚከተለው የገዛ እራሱ መመዘኛዎች እንዳሉት ሙሉ በሙሉ ያስተዋለ ወንድማዊና ልባዊ መቀራረብ የታየበት በምሉእ ነጻነት ውይይት የተካሄደበት እንደነበርም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

አሁንም በክሮአዚያ ካቶሊካዊትና በሰርቢያ አርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል የሃሳብና ያመለካከት ልዩነት እንዳለ ነው

የዚሁ የጋራው ቅይጡ ድርገት አባላት የድርገቱ ሥራ በክልሉ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅትና ብሎም በ1960 ዓ.ም. ብፁዕ ካርዲናል ስተፒናች ያረፉበት ዓመት ወቅት የነበረው ታሪክና ተጨባጭ ሁነት በጥልቀቅ ግንዛቤ እንዲኖር ማድረጉንም በእርግጠኝነት በማስመር በዚያ እጅግ አስቸጋሪ ታሪክና ውጥረት በተሞላበት ወቅት በሕይወት የነበሩት በክልሉ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የሕይወት ታሪክና ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በጥልቀት በማንበብ፡ በዚሁ ዙሪያ ከተለያዩ አካላትና ምሁራን ስለ ጉዳዩ የሚሰጠው ትንተናና ንበት አቋም የመውሰዱን ጉዳይ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ልዩነቱ በጠቅላላ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው የዚያ ያለፈው ታሪክ ትንተናና ንበት የተለያየ መሆኑ የሚያሳይ ተጨባጭ አብነት መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመለክታል።

የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የሰማእታትና የአበ ነፍሳትና እረኞች ዝካሬ ለመጋራት

በካርዲናል ብፁዕ ስተፒናክ ሕይወት ዙሪያ የሚደረግ ጥልቅ የታሪክ ምርምርና በታሪክ ሁሉም አቢያተ ክርስቲያን አስከፊ ስደትና ስቃይ እንደደረሰባቸው ከሁለቱም አቢያተ ክርስቲያን ጐራም የደም ሰማዕነት መከፈሉ መጋቢያንና ምእመናን እምነቴን አልክድም በማለት ለሕልፈት መዳረጋቸው የተረጋገጥ ነው። ስለዚህ ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ከዚህ በመንደርደር የድርገቱ ሁሉም አባላት በማስተዋል የጋራ ታሪካዊያን ድርሳናት በማቅረብ ዝክረ ሰማዕታቱን ለመጋራት ቅይጡ የጋራው ድርገት እቅድ እንዳለው ከተካሄደው የጋራው ዓውደ ጉባኤ ለመረዳት መቻሉንም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.