2017-07-13 17:19:00

ር.ሊ. ጳጳሳት ፍራንቸስኮ "የሚበልጥ ፍቅር" በሚል አርእስት አዲስ ሐዋሪያዊ መልእክት ለንባብ ማብቃታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስን ሐዋሪያዊ መንበር እንዲይዙ የተመረጡ 266ኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው ይታወቃል። ቅዱስነታቸው ይህ ሐዋሪያዊ ስልጣን ወይም ኃላፊነት በሚፈቅድላቸው መሰረት በላቲን ቋንቋ (Motu Proprio) በራሳቸው ተነሳሽነት በሐምሌ 4/2009 ዓ.ም. Maiorem hac dilectionem (ማዮሬም ሀክ ዲሌክሲዮኔም) በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም የሚበልጥ ፍቅር በሚል አርዕስት ይፋ ባደረጉት ሐዋሪያዊ መልእክታቸው እንደ ተለመደው ለእምነታቸው ሲሉ ነብሳቸውን አሳልፈው በመስጠት ደማቸውን በታላቅ ሰማዕትነት ላፈሰሱ ሰማዕታት ከሚሰጠው የሰማዕትነት ማዕረግ በተጨማሪ ለየት ባለ ሁኔታ የእግዚኣብሔር ታማኝ አገልጋይ በመሆን ነብሳቸውን ለዚህ አገልግሎት በመስዋዕትነት አቅርበው ያለፉ ሰዎች ሕይወታቸውን ለዚሁ አገልግሎት በገዛ ፍቃዳቸው አሳልፈው በመስጠታቸው የተነሳ እነርሱን እንደ ሰማዕታት አድርጎ ለመፈረጅ የሚያስችል አዳዲስ መስፈርቶችን ያካተተ ሐዋሪያዊ መልእክት መሆኑን ለመረዳት ተችሉዋል። ይህ በላቲን ቋንቋ Maiorem hac dilectionem (ማዮሬም ሀክ ዲሌክሲዮኔም)  በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎምየሚበልጥ ፍቅርበሚል አርእስት በሐምሌ 4/2009 .. የታተመው የቅዱስነታቸው ሐዋሪያው መልእክት  መሰረቱን ያደረገው ሰው ሕይወቱን ሰለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም” በሚለው በዩሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 15:13 ላይ በሚገኘው ጥቅስ ላይ በሚገኘው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ሆነም ለመረዳት ተችሉዋል።

በተጨማሪም ይህ ሐዋሪያዊ መልእክት ፈረጀ ብዙ የሆኑ ስልታዊ ቋንቋዎችን ተጠቅሞ ለእምነት ሲባል በሚከፈለው የደም መስዋዕትነት መካከል እና በገዛ ፈቃዳቸው ሕይወታቸውን ለእግዚኣብሔር አገልግሎት ይውል ዘንድ  አሳልፈው የሰጡ፣ ነገር ግን የደም መስዋዕትነት ያልከፈሉ ሰዎች መካከል ያለውን የዓላማ ትስስር ለመግልጸ ያመች ዘንድ ስልታዊ የሆኑ ቋንቋዎች የሚታዩበት ሐዋሪያዊ መልእክት ሲሆን ለምሳሌም ሕይወትን በስጦታ መልክ ማቅረብ በሚለው አመለካከት እና የደም መስዋዕትነት መክፈል በሚለው አመለካከት መካከል ያለውን ትስስር የሚገልጹ 5 መሰረታዊ የሆኑ መመዘኛዎችም ተካተውበታል።

Maiorem hac dilectionem (ማዮሬም ሀክ ዲሌክሲዮኔም)

 “የሚበልጥ ፍቅር

እነዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ፈለግ እና አስተምህሮ በመከተል በፍቃደኝነት እና በነጻነት ሕይወታቸውን ለሌሎች መስዋዕት አድርገው ያቀረቡ፣ ይህንንም ዓላቸውን እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ የጠበቁ ሰዎች ለየት ያለ ትኩረትና ክብር ይገባቸዋል። ይህ በጀግንነት የሰውት ሕይወታቸው በፍቅር ታጭቶ እና ተደግፎ እውነታን በመግለጽ ሙሉ እና ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ኢየሱስን በመምሰላቸው የተነሳ ነው ደማቸውን በማፍሰስ ለተሰው ሰማዕታትና እንዲሁም የክርስትና ስነ-ምግባራትን ጀጋና ልያስብል በሚችል ደረጃ ጠብቀው ለኖሩ ሰዎች የክርስቲያን ማኅበረሱብ አንድናቆቱን በእርግጠኛነት የሚችራቸው በዚሁ ምክንያት ነው።

የቅዱሳንን የሕይወት ሁኔታ የሚመረምረው በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው ማኅበር ድጋፍ እና አዎንታዊ ምክር እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 27/2016 .. በተደረገው ድሕረ ጉባሄ ላይ የብጽዕና ማዕረግ የሚገባቸው ክርስቲያኖች ሕይወት ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ተጠንቶ የሚከተሉት የመመዘኛ መስፈርቶች ወይም ደንቦች ተቀመጠዋል።

አንቀጽ 1.    ሕይወትን መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ የአንድ ግለሰብ የብጽዕና ወይም የቅድስና ማዕረግ አሰጣጥ ሂደት የደም መስዋዕትነት ከከፈለ ግለሰብ በተለየ ሁኔታ ይጠናል።

አንቀጽ 2. ለአንድ የእግዚኣብሔር አገልጋይ ለነበረ ግለሰብ የብጽዕናን ማዕረግ ለመስጠት የሚደረገው ሂደት ትክክለኛ እና ውጤታማ ይሆን ዘንድ ይህ የሕይወት መስዋዕትነት ከዚህ በታች ለተጠቀሱ መመዘኛዎች መልስ ሊሰጥ ይገባል።

በነጻነት እና በፍላጎት ሕይወትን መስዋዕት አድርጎ ማቅረብና በላቲን ቋንቋ propter caritatem  (ፕሮፐተር ካሪታተም) በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም ሕይወትን መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ (ይህም ማለት የጌታ ታማኝ አገልጋይ በመሆኑ የተነሳ) በቅርቡ የደም መስዋዕትነት እንደ ሚከፍል እያወቀ ሕይወቱን በእርግጠኛነት ለዚሁ አገልግሎት የሰጠ ሰው።

ለ) ሕይወትን ለመስዋዕትነት ማቅረብ እና ያለ ጊዜው የደም መስዋዕትነት መክፈል በሚሉት  ቃላት መካከል  የጠበቀ ግንኙነት ካለ

ሐ) ሕይወቱን መስዋዕት አድሮ ከማቅረቡ በፊት ቢያንስ ቢያንስ የተለመዱ ክርስቲያናዊ ስነ-ምግባራትን የጠበቅ እና እነዚህን ክርስቲያናዊ ስነ-ምግባራትን እስከ እለተ ሞቱ ድረስ የጠበቀ፣

መ) ቢያንስ ቢያንስ ከእዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ቡኃላ ቅድስናውን የሚገልጹ ምልክቶች እና ስም/ዝና ያተረፈ ሰው ከሆነ

ሠ) ይህ የእግዚኣብሔር አገልጋይ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ቡኃላ በእርሱ አማላጅነት አማካይነት የሚፈጸሙ ተዐምራት ለብጽዕና መዐረግ አሰጣጥ ሂደት በጣም ያስፈልጉታል።

አንድ የእግዚኣብሔር አገልጋይ የሆነ ሰው ሕይወቱን በስጦታነት መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ ሰው የተገባ እና ለብጽዕና ማዐረግ ብቁ ለመሆን ቀደም ሲል የተዘረዘሩትን 5 መመዘኛዎች ሊያሙላ ይገባል። በተለያዩ ሀገረ ስብከቶች ውስጥ አንድ የእግዚኣብሔር አገልጋይ የሆነ ግለሰብ የተመለከቱ መርሆች ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን ጥያቄ መመለስ ይገባቸዋል “ይህ የእግዚኣብሔር አገልጋይ የነበረ ግለሰብ ሕይወቱን በጀግንነት ለሞት አሳልፎ የሰጠው ልዩ በሆነ መንገድ የእግዚኣብሔር መልኮታዊ ፍቅር ስለነበረው እና ወይም ደግሞ ክርስቲያናዊ የሆኑ ሰነ-ምግባራትን በመጠበቅ እነዚህንም ክርስቲያንዊ ስነ-ምግባራትን በመጠበቁ የተነሳ በሕይወት እያለ በሕይወቱ የተለያዩ መስዋዕትነት በመክፈሉ የተነሳ ነው ወይ?” የሚለውን ጥያቄ ከግምት ያስገባ መሆን ይኖርበታ። 

 

 
All the contents on this site are copyrighted ©.