2017-07-10 16:41:00

“ኢየሱስ መስቀላችንን አብሮን ይሸከማል እንጂ፣ የእኛን መስቀል ሙሉ በሙሉ ብቻውን አይሸከምልንም" ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ


ዘወትር እሁድ ቀን በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ከሚቀርበው የመስዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል ይህንን መንፈሳዊ ስነ-ስርዐት ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰብሰቡ በርካታ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ቅዱስነታቸው በእለቱ በሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ላይ ተመርኩዘው መንፈሳዊ አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ያታወቃል።

የዚህ መርዐ ግብር አንዱ አካል በሆነው በትላንትናው እለት ማለትም በሐምሌ 2/2009 ዓ.ም. የቅዱስነታቸው አስተንትኖ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በተነበበው እና ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 11:25-30 በተወሰደው “እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ” በሚለው ቃላት ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

ኢየሱስ በተለያዩ ሁኔታዎች ለደከሙ ወይም ደግሞ የሕይወት ጫና የሚበዛባቸውን ሰዎች ሳይቀር ምንም ዓይነት ልዩነትን ሳይፈጥር  ይህህን ግባዣ ለሁላችንም ያቀርብልናል በማለት አስተንትኖዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “ሕይወት እንዴት ከባድ እንደ ሆነ ኢየሱስም ሳይቀር ጥንቅቆ ያውቃል” ካሉ ቡኃላ ኢየሱስ ልባችንን ሰላም የሚነሱ እና የሚያሸብሩ ብዙ ነገሮች እንዳሉም በሚገባ ይረዳል ብለዋል።

በዚህ ዓይነት የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ “ወደ እኔ ኑ!” የሚለው የኢየሱስ የግብዣ ቃል ነገሮች መልካም በማይሆኑበት ወቅቶች ሁሉ በእዚያ ሁኔታ ውስጥ ሁነን መኖር እንደ ሌለብን ያስገነዝበናል ያላት ቅዱስነታቸው ሕይወታችን በጨለማ ውስጥ በሚገባበት ወቅቶች ሁሉ ራሳችንን በማበረታታት በሕይወታችን ውስጥ የገጠሙንን ኢፍታዊ ወይም ደግሞ በዓለም ውስጥ የሚታየውን ደካማ የሆኑ አስተሳሰቦችን በድፍረት ለመዋጋት መነሳሳት ተፈጥሮአዊ የሆነ እንድምታ ያለው ጉዳይ ነው ብለዋል። ነገር ግን ኢየሱስ ከዚህ የጨላማ ሕይወት  እና ጫና የተሞላበት ስፍራ በአስቸኳይ ስቦ ሊያወጣን ይፈልጋል ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህም መልኩ ኢየሱስ ከእኛ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር፣ እጁንም ወደ እኛ በመዘርጋት እይታችንን ሁሉ ሁል ጊዜ በእውነተኛ መንፈስ ወደ ሚወደን ወደ እርሱ እንድናደርግም ይረዳናል ብለዋል።

ራሳችንን በራሳችን ቆልፈን ከምንገኝበት የጨለማ ስፍራ በራሳችን ኃይል ለመውጣት መሞከር የመጀመሪያው እርምጃ ሊሆን ይገባል በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከዚያ ጨላማ ከወጣን ቡኃላ ግን ወደ ዬት እንደ ምንሄድ ግን ልናውቅ የግባናል ብለዋል። በሕይወታችን ውስጥ ያስቀመጥናቸው ግቦች አንድአንዶችሁ አታላይ፣ አንድአንዶቹ ደግሞ ተስፋ ሰጪ፣ አንድአንዶቹ ደግሞ ለጊዜው የሚረብሹን ነገር ግን እኛ በፈለግነው እና ቀደም ሲል በመረጥነው  መንገድ እንድንሄድ በማድረግ ሕይወታችንን አወዛጋቢ ወደ ሆነ ነገር ውስጥ የከቱናል ያሉት ቅዱስነታቸው ለዚህም ነው ኢየሱስ ወደ እኔ ኑ በማለት ግብዣውን የሚያቀርብልን በለዋል.

በአብዛኛው ሕይወታችን ችግር ውስጥ በሚገባባቸው ወቅቶች ሁሉ በአብዛኛው ሰዎች ይረዱን ዘንድ ወደ እነርሱ መሄድ ይቀናናል ያሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ኢየሱስ በፍጹም ሊዘነጋ አይገባውም፣ ራሳችንን ለእርሱ ክፍት ማድረግ እና በሕይወት የገጠሙንን ተግዳሮቶች ሁሉ ለእርሱ በአደራ መስጠት ሊረሳ የማይገባ ጉዳይ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ጌታ ሁል ጊዜም ቢሆን ሊረዳን እየተጠባበቀ ይገኛል፣ ነገር ግን ይህ ማለት ጌታ ምህታታዊ በሆነ መልኩ ከችግሮቻችን ውስጥ መንጥቆ ያወጣናል ማለት አይደለም ያሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ የእኛን መስቀል ሙሉ በሙሉ ከእኛ ላይ አንስቶ ብቻውን አይሸከምም ካሉ ቡኃላ ነገር ግን እኛ መስቀላችንን በአግባቡ መሸከም እንችል ዘንድ ከእኛ ጋር በመተባበር መስቀላችንን ይሸከምልናል ብለዋል።

ወደ ኢየሱስ በምንቀርብባቸው ጊዜያት በመከራዎች እና በመከራዎች ሁሉ አብሮን ሊዘልቅ የሚችል ሰላም እናገኛለን ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን እንደ ሚሰጠን ኢየሱስ ቃል ገብቶልናል፣ ዛሬ በተነበበል ቅዱስ ወንጌል ማብቂያ ላይ እንደ ተገለጸው “ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀላል ነውና” በማለት ቃል ኪዳን ገብቶልናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በአስተንትኖዋቸው ማብቅያቸው ላይ እንደ ገለጹት “ወደ ኢየሱስ መቅረብን መማር ይኖርብናል” ካሉ ቡኃላ በተለይም ደግሞ አካልዊ የሆነ እረፍት በማድረግ ላይ በምንገኝበት በዚህ የክረምት ወቅት እውነተኛ የሆነ እረፍት የሚሰጠንን ጌታ መዘንጋት አይኖርብንም ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተንትኖ አጠናቀዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.