2017-07-08 09:40:00

ሢመተ ጵጵስና በኢጣሊያ ለሚላኖ ሰበካ


በኢጣሊያ የሚላኖ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ በዕድሜ ገደብ መሠረት ከዚህ ሐዋርያዊ ሐላፊነታቸው እንዲሰናበቱ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና በማስደገፍ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያቀረቡት የእንደ ፈቃደዎት ይሁን ጥያቄ ቅድሱስነታቸው በማጽደቅ የሚላኖ ሰበኻ ሊቀ ጳጳስ ተዳትና ጠቅላይ ምክትል ሊቀ ጳጳሳት ዘሚላኖ በመሆን ላገለገሉት ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ኤንሪኮ ደልፒኒ ለሚላኖስ ሰበካ ጳጳስ በማለት እንደሸሙዋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ኤንሪኮ ደልፒኒ እስካሁን ድረስ ለሚላኖ ሰበካ ረዳትና ጠቅላይ ሓዋርያዊ ምክልት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ በመሆን በማገልገል ላይ እንደነበሩ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥  ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ደልፒኒ በኢጣሊያ ሎምባርዲያ አውራጃ ቫረዘ ክፍለ ሃገር በሚገኘው በጋላራተ ሰበካ ሐምሌ 29 ቀን 1951 ዓ.ም. ተወልደው እ.ኤ.አ. ሰነ 7 ቀን 1975 ዓ.ም. በሚላኖ ሰበካ ማዕርገ ክህነት የተቀበሉ ሲሆን። ብፁዕነታቸው ሚላኖ በሚገኘው ቅዱስ ልበ ዘኢየሱስ ካቶሊካዊ መንበረ ጥበብ በሥነ ጽሑፍ ቀጥለውም ሮማ በሚገኘው በጳጳሳዊ አጎስቲኒያኑም መንበረ ጥበብ በቤተ ክርስቲያን አበው ቲዮሎጊያ ጥናት ሊቅነት ያስመሰከሩ መሆናቸውም ያወሳል።

ከ1975 ዓ.ም. እስከ 1985 ዓ.ም. በሰቨዞ እንዲሁም በዘርእ ክህነት ትምህርት ቤት የጥንት ሥነ ጽሑፍ መምህር፡ ከ 1985 እስከ 1987 ዓ.ም. ቨነጎኖ በሚገኘው በዘርአ ክህነት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጥንት ሥነ ጽሑፍ መምህር ከ1987 እስከ 1989 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው የሎምባርዲያ ሰበካ ጳጳሳዊ ውሉደ ክህነት ወደ ሆነው ተቋም ተልከው የሥነ ጽሕፉና የአበው ቲዮሎጊያ ተኮር ልዩ የምርምር ጥናት አካሂዷል። ከ 1989 እስከ 1993 ዓ.ም. በቨንጎኖ የዘርአ ክህነት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤተ አለቃ በፍልፍናና የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ መምህር በተጨማሪም በመላ ሎምባርዲያ ክፍለ ሃገር የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤተ ኅብረት ዋና ጸሓፊ ከ1993 እስከ 2000 ዓ.ም. የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ ከ2000 እስከ 2006 ዓ.ም. ለሚላኖ ጳጳሳዊ መማክርት ቢሮ ሓላፊ ለሰበካው ሊቀ ጳጳስ የጥሪና የውሉደ ክህነት በተጨማሪም ለሚላኖ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት እንደራሴ፡ የሚላኖ ሰበካ ባዚሊካ የክብር ሊቀ ካህናትና የካህናት ምክር ቤት አባል በመሆን ማገልገላቸውንም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ከ 2006 እስከ 2007 ዓ.ም ለሚላኖ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ለስድስተኛው ሐዋርያዊ ክፍለ ከተማና ለመለኛኖ ተጠሪ ከሐምሌ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚላኖ ሰበካ ረዳትና ምክትል ሊቀ ጳጳሳት እንዲሁም የስተፋኒያኮ ስዩም ጳጳስ ሆነው ከተሾሙ በኋላ በዚያኑ ዓመት መስከረም 23 ቀን ማዕርገ ጵጵስና ተቀብለው እ.ኤ.አ ከ2012 ዓ.ም. ለሚላኖ ሰበካ ጠቅላይ ምክትል ሊቀ ጳጳስና የሎምባርዲያ ክፍለ ሃገር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ከዝህ ባሻገርም ለሎምባርዲያ ክፍለ ሃገር የካህናትና የውፉይ ሕይወት ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ድርገት ዋና ጸሓፊ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ ይኸው በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍርንቸስኮ ውሳኔ መሠረት በእድሜ መግፋት ምክንያት የሚላን ሰበካ ሐዋርያዊ ሐላፊነታቸው በቅዱስ አባታችን እጅ ላስረከቡት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላን በመተካት የሚላኖ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ መሾማቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል አስታወቀ።     
All the contents on this site are copyrighted ©.