2017-07-06 16:03:00

ኢጣሊያ፥ በፐስካራ የእግዚአብሔር ቃል ለዳግም ግንዛቤና ግኝት ላይ ያነጣጠረ የመጽሓፍ ቅዱስ ዓውደ ትርኢት


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢጣሊያ የፐስካራ ርእሰ ሰበካ የትምህርተ ክርስቶስ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ሰዎች ወደ መጽሓፍ ቅዱስ ለማቅረብ ከቃለ እግዚአብሔር ጋር ቅርርብ እንዲኖራቸው ለማገዝ በሚል ዓላማ የተመራ የእግዚአብሔር ቃል ለዳግም ግንዛቤና ግኝት ተኮር የሆነ የመጽሓፍ ቅዱስ ዓውደ ትርኢት በይፋ መጀመሩ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጁሊያ በዲኒ ገለጡ።

ይኽ በጸሎትና በቅዱስ መጽሐፍ ጥናትና ሥነ ትንተና የተሰኙትን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያማከለው የመጽሓፍ ቅዱስ ትርኢት በማስመልከት የፐስካራና ፐነ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቶማሶ ቫለንቲነቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ሰዎችን በተለይ ደግሞ አዲሱን ትውልድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ለማስተዋወቅ ወደ ቃለ እግዚአብሔር እንዲቀርብ ማድረግ ከሚለው ራእይ የተነቃቃ መርሐ ግብር ነው፡ ይኽ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የማቅርረቡና የማብራራቱ ሂደት ለየት ባለ መልኩ እርሱም በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ በማነጣጠር በምስልና በመንፈሳዊ ትርኢት የተደገፈ ሆኖ በሥነ ሐሳባዊ ትንተና ሳይሆን በትምህርተ ክርስቶስ ስልት የሚያቀርብ ነው። በዚህ ብቻ ሳይታጠርም ቃሉን አዳምጦ በመኖር በአስፍሆተ ወንጌል መሳተፍና ብሎም ቃሉን ጸሎትና የሕይወት ምርጫ ለማድረግ  እንዲችል የሚያግዘውን መንገድ የሚያመላክት ነው ብሏል።

 የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ማኅበረ ክርስቲያን ቤተሰቦችና የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልጋይ አካላት በጋራ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በመነጻጸርና እርሱነቱን በቃሉ ላይ በማኖር በማንበብ ቃሉን ሕይወት ለማድረግ የሚደገፍ መሆኑ ብፁዕነታቸው ገልጠው፡ ቤተ ክርስቲያንና አባላቷ በቃሉ ማእድ ዙሪያ የሚያሰባስብ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.