2017-07-06 15:59:00

ቅድስት መንበርና ኣል አዝሓር፡ ቅን ዓለም ለመገንባት የጋራ ውይይት አስፈላጊነት


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ካይሮ በሚገኘው በቅድስት መንበር የሐዋርያዊ ልኡክ ሕንጻ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የጋራ ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤትና የግብጹ አል አዝሓር መንበረ ጥበብ እስላማዊ የውይይት ማእከል መካከል የጋራ ውይይት መካሄዱ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደው የጋራ ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ይፋ ያደረገውን መግለጫ የጠቀሰ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

 ይኽ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የተካሄደው የጋራው ውይይት ያንን እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 1998 ዓ.ም. የተደረሰው የጋራው የስምምነት ሰነድ እንዲሁም እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 28ና 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊጳ. ፍራንቸስኮ በግብጽ ባካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት ካይሮ በሚገኘው በአል አዝሐር መንበረ ጥበብ ከመንበረ ጥበቡ ዓቢይ መምህር አህመድ ሙሃማድ አል ጣዪብ ጋር በመሆን ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በተሳተፉበት ታሪካዊው የሰላም ዓውደ ጉባኤ ተመክሮ መሠረት ያደረገ መሆኑ የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት መግለጫ ጠቅሶ ያመለከተው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ምንጭ ዜና አክሎ ዓውደ ውይይቱ ሰላምን ለማነቃቃትና ቅን ዓለም ለመገንባት የሚያስችል ፍርያማና ተደማጭነት ያለው የጋራ ውይይት ለማነቃቃት የጋራ አስተንትኖና ራእይ ለማቅረብ ቅድስት መንበርና አል አዝሐር መንበረ ጥበብ በጋራ እንደሚተጉ ለማረጋገጥ መሆኑ ይፋ የወጣውን መግለጫ ዋቢ በማድረግ ይጠቁማል።
All the contents on this site are copyrighted ©.