2017-06-29 12:31:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በስብከታቸው “ክርስቲያኖች ያላቸው ልዩ ጥንካሬ የመነጨው ከወንጌል ነው” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሳምንት አንድ ቀን ዘወትር ረዕቡ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ አስተምህሮ እነደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው እለት ይህንን አስተምህሮዋቸውን ለመከታተል ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያሰተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም የክርስቲያን ተስፋ በሚል አርእስት ስያደርጉት ከነበረው አስተምህሮ የቀጠለ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን፣ “ተስፋ የሰማዕታት ጥንካሬ ምንጭ ነው” ብለዋል።

የዚህን ዘገባ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የእለቱ የቅዱስነታቸው ጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው “እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፣ በእኔ ምክንያት በሁሉም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፣ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የሚጸና ይድናል” በሚለው በኢየሱስ ቃል ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ቅዱስ ወንጌልን በዓለም ዙሪያ እንዲያሰራጩ በላካቸው ጊዜ በቀላሉ ወጤታማ ትሆናላችሁ በሚል አስተሳሰብ ሳይሆን የሞላቸው፣ ነገር ግን በተቃራኒው “ወንጌልን የማብሰር ሂደት እና ተልዕኮ ሁል ጊዜም ቢሆን ተቃውሞ እንደ ሚገጥመው” በግልጽ አስረድቶዋቸው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። ክርስቲያኖች ይወዳሉ ወይም ያፈቅራሉ፣ ነገር ግን በአንጻሩ ክርቲያኖች ሁል ጊዜ አይወደዱም፣ ይነስም ይብዛም እምነትን የመመስከር ሂደት ሁሌም የሚከናወነው አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ዓለማችን ሁሌም ቢሆን በኃጢአት የተሞላ ነው፣ ክርቲያኖች ግን ሁል ጊዜም ቢሆን ከእዚህ ጎራ በተቃራኒው የተሰለፉ በመሆናቸው የተነሳ ነው ብለዋል። ይህም የሚደርሳብቸው አከራካሪ የሆኑ ሐሳቦችን ስለሚያቀርቡ ሳይሆን ነገር ግን “የወንጌል አመክንዮ” የሆነውን ተስፋ እና በኢየሱስ የታተመ አስተምህሮዎችን በማድረጋቸው የተነሳ መሆኑንም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ስለዚህ የክርስቲያኖች ሕይወት በፍቅር የተሞላ ነው፣ በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በተኩላዎች መካከል የሚገኙ በጎች” ጥንቃቄን ሊያደርጉ ይገባል፣ እንዲሁም አንድ አንዴም በጣም ብልጥ ሊሆኑ ይገባል ካሉ ቡኃል ነገር ግን ክርስቲያኖች ይህንን ተግባራቸውን ነውጥ አልባ በሆነ መልኩ ማከናወን ይገባቸዋል፣ ክፉ መንፈስን ለመዋጋት የክፋ መንፈስ ዘዴን መከተል አይገባም ብለዋል። 

“ክርስቲያኖች ያላቸው ልዩ ጥንካሬ የመነጨው ከወንጌል ነው” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ክርስቲያኖች እግዚኣብሔር ሁል ጊዜ ከእነርሱ ጋር እንደ ሆነ ማስታወስ ይኖርባቸዋል ብለው እግዚኣብሔር የስውር ሴራዎችን ከሚሸርቡ፣ በሌሎች ጀርባ ላይ ተንጠልጥለው ለራሳቸው ብቻ ሐብት በማካበት፣ አቅመ ደካማውን ከሚበዘብዙ ክፉዎች እና የማፊያ አባላት በላይ እግዚኣብሔር ጥንካራ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ብለው ሁልጊም ቢሆን እግዚኣብሔር ከምድር ወደ እርሱ የሚጮኸውን የአቤልን ደም ድምጽ ይሰማል ብለዋል።

ስለዚህም ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ከዓለም  በተቃራኒው" ጎራ ይሰለፋሉ ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም አሳዳጅ ከመሆን ይልቅ ተስዳጅ መሆን፣ እብሪተኛ ከመሆን ይልቅ ትሁት፣ የጦር መሳሪያ ቸብቻቢዎች ከመሆን ይልቅ፣ ለእውነት ያደሩ ፣ አስመሳዮች ሳይሆኑ ታማኞች እንዲሆኑ በማድረግ  እግዚኣብሔር በመረጠው ጎራ እንዲራመዱ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

የኢየሱስ ተከታይ መሆን ማለት ሰማዕት መሆን ማለት እንደሆነ በጥንት ጊዜ የነበሩ ክርስቲያኖች ያምኑ እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህም ማለት ምስክሮች መሆን ማለት ነው ብለዋል። “ሰማዕታት ለራሳቸው አይኖሩም፣ የራሳቸውን ሐሳብ ለማስረጽም በማሰብ አይጣሉም ነገር ግን ለወንጌል ታማኝ በመሆናቸው ብቻ ለሞት ይዳረጋሉ ያሉት ቅዱንስታቸው ያለምንም ስስት ነብሳቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ ብለዋል።

በቀድሞ ዘመነን ከነበሩት በላይ በአሁኑ ወቅት ብዙ ሰማዕታት ይገኛሉ ያሉት ቅዱስነታቸው ለዚህም ተስፋ የሆናቸው ምንም ዓይነት ነገር እና ማንም ሰው በክርስቶስ አማካይነት ከተሰጣቸው የእግዚኣብሔር ፍቅር ሊለያቸው አይችልም ከሚለው ተስፋ የመነጨ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት "እግዚአብሔር የእርሱ ምስክሮች እንድንሆን ሁልጊዜ ኃይልን ይሰጠናል" ካሉ ቡኃላ በተለይም ደግሞ በክርስቲያን ተስፋ ተሞልተን ተግባሮቻችንን በፍቅር መወጣት እንድንችል ያረዳናል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.