2017-06-17 08:45:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ሙስና ሰውንና ኅብረተሰብን ለሞት የሚዳርግ ነቀርሳ


ዝገት (ፍርሰት) በሚል ርእስ ዙሪያ  ጳጳሳዊ የምሉእ ሰብአዊ እድገት ተንከባካቢ ጽሕፈ ቤት ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ቱርክሶን በቃለ መጠይቅ መልክ የሰጡትን መልስ ያጣመረ በጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ የፍልስፍና መምህር ተጻምሮአዊ-ዘይቤ ለተሰየመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ የፍልስፍና ሊቅ ቪቶሪዮ አልበርቲ አጠናቃሪነት የተደረሰ በመቅድሙ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጽሑፍ ያሰፈረ መጽሓፍ እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ለንባብ በበቃበት ዕለት ጳጳሳዊ ለምሉእ ሰብአዊ እድገት አገልግሎት ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት ከጳጳሳዊ የስነ ማኅበራዊ ስነ ምርምር ተቋም ጋር በመተባበር ሙስና ርእስ ያደረገ ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጉባኤ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳጳሳዊ የስነ ማኅበራዊ ስነ ምርምር ተቋም ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ቅዱስ አባታችን፥ ሙስና የሰዎችን አብሮነት የሚያኰላሽ ወንጀልን የሚያበረታታ በመጨረሻም አጥብቆ ደጋፊውንም ጭምር ለጥፋት የሚዳርግ በወንጀል ቡድኖች ልሙድ በሆነ አነጋገም ማፊያዊ ዘዬ የሞት ሂደት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በደረሱት መቅድም በማብራራት፡ ሙስና የሚል ቃል በእንግሊዝኛው Corruption ሥርወ ቃሉም corruptiō የሚለው የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም ልበ ስቡር ማለት ነው፡ የተናደና በአንድ ነገር ያደፈ ወይንም የቆሸሸ ልብ ልክ እንደ አንድ ሙት አካል ጠረናም ማለት ነው፡ ቅዱስ አባታችን ቃሉን እንዲህ በማለት ሲያብራሩ፡ ሙስና የመፈራረስ ክስተት ሲሆን ይኽም ቀስ እያለ መላ ውስጣዊ ሰብአዊ አካልንና ማኅበራራዊ አካልን የሚወርና የሚያፈራርስ ነው ብሏል።

ቅዱስ አባታችን ሙስና የሚለው ቃል የሰውን መለያ የሆነው በሦስት ደረጃ የሚቀመጠው ተገናኝ ባህርይ እርሱም ከእግዚአብሔር ጋር ከባለንጀራውና ከአካባቢው ጋር ያለው ግኑኝነት እንደ መነሻ ነጥብ በማረግ፡ አንድ ሰው ቅን ሲሆን ለጋራ ጥቅም ኃላፊነት የሚሰማው ይሆናል። በተቃርኖው ደግሞ ምግባረ ብልሽት ሲሆን ይወድቃል ጸረ ማኅበራዊ ተግባሮችን ይከተላል ተገናኝ ባህርዩን ያመክናል። በዚህ መልኩም የሰዎችን አብሮነት ጽናት የሆኑት አዕማዳትን ያወድማል። የግል ጥቅም ላይ ብቻ እንዲተኰር ያደርጋል። ይኽ ደግሞ ልክ ሁሉን አቀፍ አመለካከትና ተግባሮችን እንደሚበክል መርዝ ነው።

በአንድ ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚያ እጅግ የወንጀል ቡድኖች የሚንቀሳቀሱበት ክልል ተብሎ በሚነገርለት ስካምፒያ በመባል በሚጠራው በናፖሊ በሚገኸው ክፍለ ከተማ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ባስደመጡት ቃለ ምዕዳን ሙስና እንደ ጠረን ነው። ይገማል ብለው እንደነበርም የሚታወስ ሲሆን። ይኸውን በዚህ በደረሱት መቅድም ይኸንን ሓሳብ መለስ ብለው ሙስና መጥፎ ሽቶ ነው። ከአንድ ከገማ ወይንም ካደፈ ልብ የሚወጣ መጥፎ ሽታ ነው። ይኽ መጥፎ ጠረን ሌላውን ከመበዝበዝ ወደ ክፋት ክማዘንበል ከማኅበራዊ ፍትሕ መጓደል፡ ብቃትና ችሎታ መመዘኛ መሆኑ ቀርቶ አድልዎ የሚቀድምበት በመጨረሻም ያገልግሎት መሽጫ መጓደል የሚያስከትል በዚህ መልኩም መጥፎ የሆነው ጠረኑን አካባቢን አብሮ መኖርን ሁሉ ይበክላል። ለባርነት ይዳጋል የከተሞች ደህንነትንም ሆነ ለማኅበራዊ ጥቅም ተቆርቋሪነት ከዚህ በዘለለ መልኩም የተፈጥሮን ጥቅም አሳቢነት ሳይቀር ያኮላሻል።

ሙስና መቅሰፍት ነው፡ ተስፋን መጻኢን  ያጨልማል ለሞት ባህል መሠረትም ነው በማለት ቅዱስ አባታችን በደርሱት መቅድም ያሰፈሩት ሃሳብ ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን በመጽሓፋቸው ሙስና ዙሪያ ለሰጡት ሰፊ ትንተና ማእከል በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ዓይነቱ እከይ ተግባር እርሱም የዓለም መንፈሳዊነት ከመኖርና ከግድ የለሽነት ከበራዳማነት መንፈሳዊነት ከግብዝነትና አስመሳይነት ትዕቢት ከሚያስከትለው የባለ ድለኛነት መንፈስ ትጠበቅ ዘንድ አደራ እንዳሉ ባጠናቀሩት ዘገባ ያመላከቱት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው፥

ቅዱስ አባታችን ኃይለ ቃል በተሞላበ አነጋገርም ውበትና ውህበት ላይ በማተኮር ውበት ከየጌጣጌጥና ከቁንጅና ማእከል የሚሰጥ ተቀጥላ አይደለም፡ የሰው ልጅ በውስጡ ያለው ጸጋ ነው፡ በመሆኑን ይኸንን ውበት ለመኖር የሚቻለውም በፍትሓዊነት ነው፡ ስለዚህ ሙስናን መዋጋት ማውገዝ ያስፈልጋል። ሙሰኛው ምሕረት መጠየቅ ይቅርትን መለመን ይዘነጋል። ምክንያቱም ቸልተኛና ግብዝ በመሆኑም ነው፡ ቤተ ክርስቲያንና ክርስቲያኖች እንዲሁም ኢክርስቲያን ሁሉ አዲስ ሰብአዊነት ለመፍጠር የሚግዝ ኃይል የሚያመነጩ እንዲሆኑ አደራ በሚል ሃሳብ መቅድሙን እንድቋጩ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.