2017-06-14 17:01:00

ንጽሕት ድንግል ማርያም የቆዳ ሕክምና ቤት ተቋም አዲስ ዋና አስተዳዳሪ መሾም


ቅድስት መንበር ፕሮፈሰር አንቶኒዮ ማሪያ ለዮዛፓ የንጽሕት ድንግል ማርያም የቆዳ ማከሚያ ቤት ተቋም ሊቀ መንበር የነበሩትን ዶክተር ማሪያ ፒያ ጋራቫሊያን እንዲተኩ መሾሟ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

አዲሱ የማከሚያ ቤቱ ሊቀ መንበር ሥራቸውንም ልክ በተሾሙበት ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲጀምሩ ቅድስት መንበር ባስተላለፈቸው ውሳኔ ገልጣ፡ በሊቀ መንበርነት ያገለገሉት ዶክተር ማሪያ ፒያ ጋራቫሊያ ማከሚያ ቤቱ አጋጥሞ ከነበረው የተወሳሰበ ችግር ለማላቀቅና ችግሩ በተከሰተበት ወቅት በብርታትና በጥበብ በመምራት ለሰጡት አገልግሎት ቅድስት መንበር እውቅና ሰጥታ በማመስገን አዲሱ ሊቀ መንበር አንቶኒዮ ማሪያ ለዮዛፓ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይኽ ከተቋቋመ ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው በኤውሮጳ ቀዳሚ ከሆኑት የቆዳ ማከሚያ ቤቶች ውስጥ አንዱ ተብሎ የሚነገርለትን በበለጠ ለተዋጣለት አገልግሎት የሚያበቃው ግፊት ለመስጠት ብቃት ያላቸውን  የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የሆኑትን አብሮቸው የሚያገለግሉትን የተቋሙ ምክር ቤት አባላት መርጠው ለቅድስት መንበር እንዲሳወቁ ቅድስት መንበር ማሳሰቧ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ተቋሙ የቆዳ ማከሚያ ቤት ብቻ ሳይሆን በሥነ ቆዳ ምርምርና የቆዳ በሽታዎች ዙሪያ ጥልቅ የሥነ ሕክምና ምርምር የሚከናወንበት ማእከል ጭምር መሆኑ በማስታወስ ይጠቁማል። 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.