2017-05-30 15:02:00

“ክርስትያኖች ማንኛውንም ዓይነት ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መስተጋብር መፍጠር ይኖርባቸዋል"።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 21/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት “ክርስትያኖች ማንኛውንም ዓይነት ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መስተጋብር መፍጠር እና ልባቸውንም ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት ሊያደርጉ ይገባል” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት በመንፈስ ቅዱስ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የታወቀ ስሆን “ልባችንን የምያነሳሳው፣ እንዲንቀሳቀስ የምያደርገው እንዲሁም ስሜታችንን የሚያነሳሳው መንፈስ ቅዱስ ነው ብለዋል።

በሚቀጥለው እሁድ በግንቦት 27/2009 ዓ.ም. በሁሉም ክርስትያኖች ዘንድ የሚከበረውን የጴራቅሊጦስ በዓል ከግምት ባስገባው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት መንፈስ ቅዱስ በልባችን፣ በየቁምስናችን እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ይወርድ ዘንድ ቤተ ክርስትያን ትጸልያለች ብለዋል።

በእለቱ በላቲን የስርዓት አምልኮ አቆጣጠር መሰረት በቀዳሚነት በተነበበው እና ከሐዋሪያ ሥራ 19፡1-8 በተወሰደው ሐዋሪያው ጳውሎስ በኤፌሶን በነበረበት ወቅት በዚያ የነበሩ ጥቂት አማኞችን “በተጠመቃችሁበት ወቅት መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችሁ ነበር ወይ? ብሎ በጠየቃቸው ወቅት “መንፈስ ቁድስ የሚባል ነገር መኖሩን እንኳን አንውቅም” ነበር ብለው መልስ ሰጥተውት እንደ ነበረ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በጣም ጥሩ የሚባሉ የእመንት ሰዎች ነበሩ፣ ነገር ግን የአብ ስጦታ የነበረውን መንፈስ ቅዱስ አላወቁትም ነበር፣ “ጳውሎስ እጁን በእነርሱ ላይ በጫነባቸውም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደና በሌላ ቋንቋዎች መናገር” መጀመረቻውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

በቅዱስ ወንጌል ውስጥ  የተጠቀሱ ብዙ ሰዎች ለምሳሌም ኒቆዲሞስ፣ ዓስራ ሁለት አመት ሙሉ ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት፣ ሳምራዊው ሰው፣ ብዙ ኅጥያተኛ የነበሩ ሰዎች ኢየሱስን መገናኘት የቻሉት መንፈስ ቅዱስ ልባቸውን ስለ አንቀሳቀሰ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምዕመናን “መንፈስ ቅዱስ በሕይወቴ ውስጥ ምን ዓይነት ስፍራ አለው?” ብለው መጠየቅ እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

መንፈስ ቅዱስን “መስማት እችላለሁ ወይ? የሆነ ውሳኔ ከመወሰኔ በፊት እና የሆነ ነገር ከመፈጸሜ በፊት መንፈስ ቅዱስ እንድያነቃቃኝ ጸልያለው ወይ? ወይስ ልባችን ስሜት አልባ እና መረጋጋት በሚሳነው ወቅት ይህንን ጉዳይ ልባችን ዝም ብሎ ያዳምጣል ወይ?” በማለት ቅዱስነታቸው ጥያቄን አንስተዋል።

በወንጌል ውስጥ ይህን የመሳሰሉ ልቦች ይገኛሉ “እስቲ የሕግ ምሁራንን ለአንድ አፍታ እንመልከት፣ በእግዚኣብሔር ያምናሉ፣ ዓሥርቱን ትዕዛዛት ጠንቅቀው ያውቃሉ፣ ይሁን እንጂ ልባቸው ሁሌም ዝግ እና ያልተሸበረ ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው ምዕመናን ልባቸው እንዲታወክ ሊፈቅዱ ይገባል ካሉ ቡኃላ በዚሁ ሁኔታ በምንሆንበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ ምናባዊ የሆነ እምነትን አስወግደን ትክክለኛ ውሳኔ እንድናደርግ ይረዳናል ብለዋል።

“መንፈስ ቅዱስ በማንኛውም የሕይወት ጎዳና ላይ እንዲመራችሁ ጠይቁት። መንፈስ ቅዱስ ክፉን ከደጉ ለመለየት ትችሉ ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጣችሁ ጠይቁት፣ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በቀላሉ ክፉን ከደጉ መለየት እንድንችል ይረድናል ካሉ ቡኃል ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.