2017-05-29 17:01:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጀኖቫ ያካሄዱት የአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት ጽማሬ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ሰሜናዊ ክልል በምትገኘው በሊጉሪያ ክፍለ ሃገር ርእሰ ከተማ ጀኖቫ የአንድ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ማካሄዳቸው ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን። ቅዱስታቸወ ባካሄዱት ሐዋርያ ጉብኝት መርሐ ግብር መሠረት

            ከሠራተኛው ዓለም

ከሊጉሪያ ክፍለ ሃገር ብፁዓን ጳጳሳ ካህናት የዘረአ ክህነት ተማሪዎች የመናንያን ማኅበር አባላት ከሊጉሪያ ክፍለ ሃገር ሐዋርያዊ መንበር ተባባሪ ዓለማውያን ምእመናን በጀኖቫ ርእሰ ሰበካ ካቴድራል ቅዱስ ሎረንዞ

የሊጉሪያ ሰበካዎች የቅድስት ማርያም ጠባቂ ቅዱስ ሥፍራ ወጣት ልኡካን ማኅበር

ከስደተኞ ተፈናቃዮችና ከጎዳና ተዳዳሪዎች በቅድስተ ማርያም ጠባቂ ቅዱስ ሥፍራ በሚገኘው አዳራሽ ምሳ ተቋሰው

በጃኒና ጋስሊን የሕፃናት ማከሚያ ቤት ውስጥ በህክምና ላይ ከሚገኙት ሕጻናት

በጀኖቫ ኬነዲይ አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው የጀኖቫው የአንድ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በዚያኑ ዕለት ወደ ማምሻው ወደ ቫቲካን ሐዋርያዊ መንበራቸው መመለሳቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።

በጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ የሊጉሪያ ርእሰ ክፍለ ሃገር ጆቫኒ ቶቲ የመንግሥት ኅየንተ ፊያማ ስፐና የጀኖቫ ከንቲባ ማርኮ ዶሪያ ልክ 08 ሰዓት ከሩብ ገደማ አቀባበል ከተደገላቸው በኋላ እዛው ከሚገኘው በኢጣሊያ በሁለ መናው ትልቅ ተብሎ የሚነገርለት ኢልቫ በመባል የሚጠራው የብረታ ብረት ዓቢይ ፋብሪካ ሠራተኞች ጋር ተገናኝተው የጆኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በሠራተኞች ፊት በሁሉም ስም የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ካስደመጡ በኋላ ከአራት ሠራተኞች ዕለታዊ ተግዳሮት እርሱም ቢሮክራሲው የዕደ ጥበብ እድገት በሥራና ሠራተኛው ላይ ያለው ተጽእኖ ያማከላ የቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት በምድረግ በለገሱት ምዕዳን፥

በሁሉም ነገር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ሰብአዊነት መሆኑ አለበት፡ የሰብአዊ ተጨባጭ ሁኔታ፡ የሥራ መብትና ግዴታ እንዲሁም ሰብአዊና መዋዕለ ንዋይ ኃብት ሁሉ አንድ ቅንና የተወሃደ ኅብረተሰብ ለመገንባ በሚል ዓላማ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት፡ መብትና ግዴታ መጠበቅ አለበት። ሥራ ከዘፍትጥረት ጀምሮ ለሰው ልጅ የተሰጠ በመፍጠር ላይ የሚያሳትፍ የሰውን ልጅ አሳቢነት መግለጫ ነው። ስለዚህ በመከሰት ላይ ባለው የዕደ ጥበብ እንድገት በኤኮኖሚ ለውጥና የሕይወት ለውጥም ምክንያት ለተለያዩ ርእዮተ ዓለም እጅ ካለ መስጠት አለ ፍርሃት በኃላፊነት ስሜት መመልከት ያስፈልጋል። በርግጥ የተደላደለ ሕይወት መልካም ኑሮ በጥቂቱ እጅ ቁጥጥር ሥር አየሆነ ብዙኃኑ ደግሞ ሥራ አጥ ብቻ ሳይሆን ወደ ድኽነት እያዘገመ ነው። ስለዚህ ደጓሚ ኤኮኖሚ እንዲረጋገጥ መጣር ሳይሆን ሥራ ለሁሉም የሚል ዓላማ እውን ማድረግ ያስፈልጋል፡ ሥራ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ውስጥ የሚጠቃለ መሆኑ በስፋት ማብራራታቸ ለማወቅ ተችሏል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም ከሊጉሪያ ክፍለ ሃገር ብፁዓን ጳጳሳ ካህናት የዘረአ ክህነት ተማሪዎች የመናንያን ማኅበር አባላት ከሊጉሪያ ክፍለ ሃገር ሐዋርያዊ መንበር ተባባሪ ዓለማውያን ምእመናን ያሳተፈ በጀኖቫ ርእሰ ሰበካ ካቴድራል ቅዱስ ሎረንዞ ባደረጉት ግኑኝነት፡ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በሁሉም ሥም ለቅዱስነታቸው የምስጋና ቃል ካሰሙ በኋላ ቀጥለው ከሁለት የሰበካ ካህናት፡ የሊጉሪያ የደናግል ማኅበራት ጠቅላይ አለቆች ኅብረት ሊቀ መንበርና አንድ የካፑቺን ማኅበር አባል ያቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ካዳመጡ በኋላ በለገሱት ቃለ ምዕዳን፥

በዚህ በተዋከበውና ሩጫ በተሞላው ጥድፊያ የተከናነበው ወቅታዊው ዓለም ተስፋን አቅቦ እምነትን ማጎልበት እንዴት ይቻላል? ካህናት የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ክርስቶስን በመምሰል ወንድማማችነትን ማሕበራዊ ሕይወትን በመኖር ከክርስቶስ ወደ ክርስቶስ ለክርስቶስ መኖር  መቻል አለባቸው። ዋናው ክርስቶስን መምሰል ነው። በመስዋዕተ ቅዳሴና በጸሎት ላይ ያማከለ ሕይወት መኖር ያስፈልጋል። ኢየሱስ ከሕዝብ ጋር ነበር ሁሌ በጎዳና ለተነጠለው ለተገለለው ለታመመው በድኽነት ለተጠቃው ቅርብ ነበር፡ ነገር ግን ከሁሉም ገለል ብሎ የሚጸልይበትና ከአባቱ ጋር የሚገናኝበት ሰዓታትም ነበረው። ከአባቱ ጋር የሚያደርገው ግኑኝነት ከሕዝብ ጋር ለሚኖረው ግኑኝነት መሰረት ነው። ስለዚህ ክርስቶስን መምሰል ለሐዋርይዊ ግብረ ኖልዎና ለወንጌላዊ ልኡክነት ያነቃቃል።

በላቲን አመሪካ እንዲሁም በተለያዩ ሌሎች አገሮች እንደታየው ወጣቱን ሰብስቦ የመንፍሳዊ ማኅበር አባል ማድረግ ይደረገ እንደነበረው እርሱም የሚታየው የልኡካን እጥረትና የጥሪ መጓደል ያስከተለው ግሽበት ለማካካስ ተብሎ በስፋት ይታይ የነበረው አሰራር መቅረት አለበት። ለብዙ አደጋ እንዳጋለጥም ሁላችን የምናውቀው እውነት ነው። ጥሪው የጌታ ነው፡ ይኸንን ማስተዋል ይኖርብናል። ጥሪ ላይ ያማከለ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማነቃቃት ከባድ ነው ይገባኛል ነገር ግን በጽናትና በእምነት እንተግብረው። እምነት በፈጠራ ብቃት የሚሸኝ መሆን አለበት። በቃልና በሕይወት የሚመሰከር እምነት አሳማኝና ማራኪ በመሆኑ ናና ተከተለኝ የሚለው ኢየሱስ ነው እንዳሉ ሲታወቅ፡ በዚህ አጋጣሚም በግብጽ በአክራሪያን ታጣቂ ምስሊሞች እጅ እ.ኤ.አ. ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም. የተገደሉት የኦርቶዶክስ ምእመናን አስታውሰው፥ ከባለፉት ዘመናት በዚህ ባለንበት ዘመን የደም ሰማዕትነት እጅግ ከፍ ብሎ የሚታይ ስለ እምነት የሚገደለው የክርስቲያን ብዛት እጅግ ከፍ ያለ ነው ብለው ስለ ተገደሉት ሰማዕታት እንዲጸለይም ማሳሰባቸው ተገልጧል።

የሊጉሪያ ሰበካዎች የቅድስት ማርያም ጠባቂ ቅዱስ ሥፍራ ወጣት ልኡካን ማኅበር ጋር ባካሄዱት ግኑኝነትም፥ በቅድሚያ ቅዱስነታቸው ከአራት ወጣቶች የቀረበላቸው ጥያቄ በማስደገፍ፥ በሕይወት ማስተዋል ያለው አስፈላጊነት አብራርተው እምነትን አቅቦና እምነት እያጎለበቱ እምነትን ከሌሎች ጋር ተካፍሎ በመኖር አንድ ቅንና በምኅረትና በእርቅ ላይ የጸና ኅብረተሰብ ለማረጋገጥ የሕይወት ተጋርጦን ሁሉ ገጥሞ በሚነዛው አሉታዊ ዜና ተስፋ ሳይቆረጥ መልካም ዜና ማበሰርና ከሁሉም ጋር በመገናኘት መኖር ያለበትን ጥሪ በመለየት በምንጠራበት ጥሪ አማካኝነትም መኖርና ማገልገል ያለው አስፈላጊነት በጥልቀት አብራርተዋል።

ማፍቅር ሲባል በሩቁ ሳይሆን ቀርቦ እነዚያን በትልቅ ችግር ውስጥ የወደቁትን ሁሉ ቀርቦ ከወደቁበት በማንሳት አንተ ልእኔ ኢየሱስ ነህ ብሎ ኢየሱስ መምሰል ማለት ነው፡ ይከንን ፍቅር በምንጠራበት የጥሪ ሕይወት ውስጥ የሚገለጥ ነው፡ በመጨረሻም በአሁኑ ሰዓት በሜዲትራኒያን ባሕር ሕይወታቸውን የሚያጡ ስደተኞችን በማሰብም ይኽን ያክል የሰው ልጅ ሕይወት ለተሻለ ሕይወት በሚል ዓላማ በሚያደርገው ጉዞ በሚያጋጥም አደጋ መሞት በእውነቱ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን ለምንኖርበት ዓለም ፖለቲካ ማሕበረሰብና ኤኮኖሚ ጥልቅ ጥያቄ ነው፡ ሁላችን ማናችንም ሳይቀር የንጹሓን ሕይወት ተጠያቂዎች ነን። ቅንነት ፍትህና እኩልነት የጸናበት ዓለም ለመገንባት ሁላችን በምንኖርበት ጥሪ ኃላፊነት አለብን እንዳሉ ተገልጠዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.