2017-05-19 17:05:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ሞትን አሸንፎ ከተነሣው ኢየሱስ ጋር መገናኘት ትካዜን ወደ ኃሴት ይለውጣል


እ.ኤ.አ. ግንቦት 18 ቀ 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በፊት 11 ሰዓት ተኩል Huntington-የአእምሮ ሕዋስ እያመነመ ቀስ በቀስ መላ ሰውነትን የሚያሰልል ብዙ ያተለመደና ገና መድኃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቁትን በብዛት በሽታው ከሚታይባት ከላቲን አመሪካና ከሌሎች አገሮች የተወጣጡ በወላጆቻቸው በጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች በበቤተ ክርስቲያን የማከሚያ ቤቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ቆሞሶች የተሸኙትን አገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎ ስድስተኛ የጉባኤ አድራሽ ተቀብለው ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገልጠዋል።

በዚህ በተካሄደው ግንኙነትም በኒው ዮርክ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ቲሞትይ ዶላን የተሸኙት ሰበካው በሚያስተዳድረው በዚህ ዓይነት በሽታ የተጠቁትን በብዛት ድጋፍ የሚያገኙበት ሰቃይን እናቅልል የተሰየመው ማእከል ውስጥ የሚረዱትን በመሸኘትም የተገኙ ሲሆን፡ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ እምብዛም በማይታወቅ በሽታ የሚጠቁትን ዜጎች የምትሰጠው አገልግሎ ከሩቅ ዓመታት የጀመረ መሆኑም በዚህ አጋጣሚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራኮ ራቫዚ በመግለጥ እንዳውም ይላሉ እ.አ.አ. በ2000 ዓ.ም. ጳጳሳዊ የሥነ ምርምር ተቋም በየዓመቱ የሚሰጠው ፒዮስ አስረኛ ሽልማት ለሁለት የዚህ በሽታ አናሥር በመለየት መድኃኒት እንዲገኝ በሚደረገው የምርምር ሥራ አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጡ ላሉት ወጣት የሥነ ሕክምና ሊቃውን መስጠቱ ማስታወሳቸው ሳባቲነሊ ይጠቁማሉ።

ቅዱስ አባታችን ለእነዚያ በሐኪሞቻቸው በጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎችና በወላጆና በቤተሰብ አባላት የተሸኙትን በዚህ የአእምሮ ሕዋስ እያመነመአ ቀስ በቀስ መላ ሰውነትን የሚያሰልል ብዙ ያልተለመደና ገና መድኃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቁትን ተቀብለው ምዕዳን ሲለግሱ፥ በቅድሚያ ንግግር በማስደመጥ ለቅዱስነታቸው የምስጋና ቃል ያሰሙት ህሙማንን ከቅዱስነታቸው ጋር ላስተዋወቁት ለክብርት ካታነኦና ለክቡር ሳቢነ አመስግነው፥ በተለያዩ አገሮች የሚገኙት በሥጋና በነፍስ የሚሰቃዩትን ሁሉ ሰላምታዮ ይድረሳቸው ብለው፥

“በብዛት እዚህ የተገኛችሁት ክሩቅና ረዥም ጉዞ በመጋፍፈጥ የመጣችሁ ናችሁ። ስለዚህ ከደረሰባችሁ በሽታ አንጻር እዚህ መገኘታችሁ ብርታት የሚጠይቅ ተግባር ነው። እናንተን ዕለት በዕለት በስቃያችሁ የሚሸኙዋችሁ ከጎናችሁ ካለ መለየት የሚንከባከብዋችሁ የሕክምና ባለ ሙያዎች  የቤተሰቦቻሁ አባላት እንዲሁም የበጎ ፈቃድ አባላት ሁሉ መልካም ተግባራቸው የሚደነቅ ነው። ፍቅር ሁሉን ነገር ተቻይ ያደርጋል።

በሽታው አለፎ አልፎ የሚታይ ስለ ሆነም እንደ በሽታ እውቅና ያላገኘ በመሆኑ ይኸውን በዚህ በሽታ የተጠቁት ተነጥለው ለመኖር የተገደዱ ሆነዋል። የታማሚው ቤተሰብም ይኸንን ሁሉ ችግር ለብቻው በመጋፈጥ በበሽታው በማፈር ለብቻቸው ተትወው ችግሩን በድብቅ ሲኖሩት ይታያል። የዚህ የግንኙነቱ መርሕ ቃል ‘ድብቅ ሆኖ መኖር ያብቃለት’ የሚለው ቃል መፈክራዊ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነት የሚጠይቅ በሽታውን ለመዋጋት ሊበረከት የሚገባውን አስተዋጽኦ የሚያነቃቃ ነው። ስለዚህ ቃሉን ድምጻችን ከፍ በማድረግ ለዓለም ሁሉ እናሰማ።

በበሽታው ምክንያት አፍሮና ተሸማቆ ተደብቆ መኖር ያብቃለት። ስለዚህ ቃሉን ከፍ እድረገን ለማሰማት የሚያበቃን እምነትና ኃይል ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ በምድራዊ ሕይወቱ ብዙ ባደረባቸው በተለያየ በሽታ ምክንያት ተነጥለው እንደ ሃፍረት ታይተው ከሁሉም በሁሉም ተገለው ይኖሩ የነበሩትን ተቀብሎ ስቃያቸውን የራሱ በማድረግ ከዚያ ዘርፈ ብዙ ለያይ ግንብ አጥር ነጻ እንዲወጡ አድርጓል። ለኢየሱስ ማንኛውም ዓይነት በሽታ ለመገናኘ እንጂ ለማግለልና ለተገሎ መኖር ምክንያት እይደለ። የሰው ልጅ በማንኛውም የሕይወት ደረጃ ይገኝ ክቡር መሆኑ ኢየሱስ በቃልና በሕይወቱ አረጋግጦልናል። ደካማነት ኃጢኣት ወይንም እርግማን አይደለም። የደካማነት ምልክት የሆነው በሽታ ለማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሊያጋጥም የሚችል ነው። ሆኖም ሰብአዊ ፍጡር የትም ይኑር በማንኛው ዓይነት ህላዌነትም ይገኝ በእግዚአብሔር ፊት ያለው ክብር ሊዘነጋ አይገባውም።

… እነዚያ በኢየሱ ይገኙና ከኢየሱስ ጋር ይገናኙ የነበሩት ህሙማን ዳግም መወለድን ገጠመኝ ያደርጋሉ ይለወጣሉም። እንደ ተፈቀሩና እንደተገኙም ያስተውላሉ። ስለዚህ ከእናንተ ማንም ጫና ወይን ሸክም ሆኖ ሊሰማው አይገባውም። በደረሰበት በሽታ ምክንያት በሽታው ተለይቶ ባለ መታወቁና መድኃኒም ገን ስላልተገኘለት ተደብቆ አፍሮ ከሌላው ሁሉ ተሰውሮ ለመኖር እዳያስብ፡ በእግዚአብሔር አይኖች ፊት የተከበራሁ ናችሁ። በቤተ ክርስቲያን አይኖች ፊት ክቡራን ናችሁ።

እነዚህ ህሙማን ግዜያቸውን እራሳቸን ሰውተው ከጎናቸው ሆነው የሚከታተሉዋቸውና የሚደግፉቸው ቤተሰብ ባይኖራቸው ኖሮ በእውነቱ ተነጥሎ የመኖሩ ችግር ለማሸነፍ ባልቻሉ ነበር። እናንተ የህሙማን ቤተሰብ ታማሚው በጉዞው የምትሸኙ ኣባቶች እናቶች ወንድምና እህት እዩልኝ ስሙልኝ የማይል ውፉይነት የተካነው አገልግሎታችሁ የሚደነቅ ነው። በርቱ። ለብቻችሁ እንዳልሆናችሁም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። እናንተ የዚያ የመኖር ዋስትና የሆነው የመተባበር የመደጋገፍ ተግባር በመላ ቤተሰብ መካከል ትስስርና ግኑኝነት እንዲኖር የምታደርጉ ናችሁ”

እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አያይዘው፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለእነዚያ በዚህ ዓይነት ልሙድ ባልሆነ በሽታ ለተጠቁት ቅርብ በመሆን በሕክምና ዘርፍ የሚያገለግሉትን በዚህ አጋጣሚም የሚሰቃዩትን የሚደግፈው ያንን መድኃኒት ያልተገኘለት በሽታ መድኃኒት ይገኝለት ዘንድ ቅድስት መንበር ለምትሰጠው ድጋፍና ትብብር የሚያገለግል ተቛም በማመስገን ይኽ አይነቱ ግልጋሎት ያለው አስፈላጊነትም እንዳሰመሩበት ጠቅሰው፥

“የምትሰጡት አገልግሎት ክቡር ነው። ምክንያቱም እነዚያ በእናንተ የሚወከሉ የህሙማን ቤተሰቦች ተሰፈኛው ተግባር የምታነቃቁ ተስፋን ተጨባጭ የምታደርጉ ናችሁ። እንዲህ ዓይነቱ በሽታ የሚደቅነው ተግዳሮት ሁሉ ለማሸነፍ ባላችሁ የጤና ጥበቃ ሙያ አማካኝነት የምትሰጡት አገልግሎት እግዚአብሔር ይባርከው። እናንተ የህሙማን ቤተሰቦች ተስፋ እንዳይቆርጡ ያንን በአሁኑ ሰዓት የሚታየው ሰብአዊነት ሚዛን የጎደለው ማኅበራዊና ሕክምናዊ ተግዳሮት ለማሸነፍ ህያው አብነት ናችሁ።

በበሽታው ላይ ቁሳዊና ሰብአዊ ድኽነት ሲታከልበት፡ እርሱም የወላጆች መለያየት ሲደረብበት፡ በሕይወት ትርጉም ላይ እማኔነት ሲጠፋ በሽታው ከሚያስከትለው ስቃይ በላይ ብሶ ተስፋ ሊያስቆርጥ ይችላል። በዚህ ዓይነት ሁነት ውስጥ ላሉት ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የትብብርና የድጋፍ ማኅበራት እጅግ አስፈላጊ ናቸው። እናንተ እነዚያ በቀቢጸ ተስፋና የሕይወት ትርጉም በማጣት ለሚገኙት ቀርበው የሚያጽናኑትን የእግዚአብሔር እጆች ናችሁ። መብቴና ክብሬ በማለት ለሚያቀርቡት የይገባኛል ጥያቄ ድምጽ ናችሁ”

ካሉ በኋላ ለእነዚያ በጉባኤው ለተገኙት ለሁሉም የሥነ ሕክምና ተመራማሪዎችና ሊቃውንት ይኽ በዓይነቱ ለየት ያለና ያልተለመደ በሽታ መድኃኒት ይገኝለት ዘንድ ሌትና ቀን ለሚያደርጉት ጥረት አመስግነው በእነዚያ የሥነ ሕክምና ሊቃውንት ምርምርና ሙከራ የህሙማኑ ተስፋ የተጣበቀ መሆኑም ገልጠው፡ ያንን የታመመውን የሚነጥል ለብቻው የሚተው የሞት ባህል ለማሸነፍ የሚያካሂዱት ጥረት አመስግነው ጥረታችሁና ድካማችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይባርከው ያሉት ቅዱስ አባታችን የለገሱት ምዕዳን ሲያጠቃልሉ፥

የተከበራችሁ ውዶቼ

እናንተ አቢይ ተስፈኛና የመንፈስ ግለት ያለባችሁ ማኅበረሰብ ናችሁ። የምትኖሩት ሁነት ስቃያችሁ የዚያ ተስፋውን ለሰጠን ክርስቶስ ሕያው ምስክርነት ነው። በስቃይ በሚመለከተው ፍርያማ በሆነው ሰናይ መንገድ አብረን እንጓዝ፡ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። እኔ ስለ እናንተ እንደምጸልየው ሁሉ አደራችሁ ስለ እኔ መጸለይ አትርሱ ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ማሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።  








All the contents on this site are copyrighted ©.