2017-05-11 09:39:00

የተስፋ እናት የሆነችውን ማሪያምን ተመልከቱ


በጣም በርካታ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ዘወትር ረዕቡ እለት በቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ልማዳዊ በሆነ መልኩ የሚሰጠውን የጠቅላላ አስተምህሮ ወይም ትምህርተ ክርስቶስ ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንደ ሚሰበሰቡ ይታወቃል። የዚህ የጠቅላላ አስተምህሮ አንዱ አካል በሆነ በሚያዝያ 2/2009 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው ከዚህ በፊት “የክርስትያን ተስፋ” በሚል አርእስት ጀምረውት የነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ! በማለት አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “ ‘ክርስትያን ተስፋ’ በሚል አርእስት ጀምረነው የነበረውን አስተምህሮ በመቀጠል በዛሬው እለት አስተምህሮዋችን ደግሞ የተስፋ እናት የሆነችውን ማሪያምን እንመለከታለን” በማለት አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነትቸው ከመጀመሪያው አንስቶ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው የማሪያም ግጽታ አንደ የአንድ ድራማዊ ትይንት ተዋንያን ግጽታን የተላበሰች ይመስላል ብለዋል።

ይህም በቀላሉ የእግዚኣብሔር መልአክ ላቀረበላት ጥሪ “እንዳልከኝ ይሁንልኝ” ብላ በመመለሷ ብቻ የተፈጠረ ሳይሆን፣ ነገር ግን እርሷ ገና በማበብ ላይ በነበረ ወጣትን ውስጥ በነበረችበት ወቅት ምን እንደ ሚያጋጥማት ባታውቅም ቅሉ መልአኩ ላቀረበላት ጥያቄ በብርታት መልስ መስጠት ስለቻለች ነው ብለዋል።

ማሪያም በዚህ ሁኔታዋ በከፍተኛ ብርታት በመሀጸናቸው ውስጥ የሚገኘውን አዲስ ህጻን የውልደት ታሪክ እንደ ሚጠባበቁ በዓለማችን ውስጥ እንደ ሚገኙ ብዙ እናቶች አንዱ በመሆን ነበር የቀረበችው ብለዋል።

ይህ “እንዳልከኝ ይሁንልኝ” የሚለው የታዕዝዞ ቃል ማሪያም በእናትነት ጉዞዋ ወቅት አብርዋት በመጓዝ  የረዳት የመጀመሪያውን በር የከፈተ ቃል ነበር በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም መልኩ ማሪያም በቅዱስ ወንጌል ውስጥ በዙሪያዋ ይከናወኑ የነበሩትን ነገሮች በቅጡ ያልተረዳች፣ እንደ አንድ ዝምተኛ ሰው በመሆን ተጠቅሳ እንደ ነበረም አስታውሰው እያንዳንዱን ቃል እና ክስተት በልቧ ውስጥ ታሰላስል እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

“በዚህ የዝግጅት ወቅት በማሪያም ስነ ልቦና ውስጥ ከሁሉም ለየት የሚያደርጋት አንድ ነገር አለ” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ሕይወት አስተማማኝ ደረጃ ላይ በማይኖርበት ጊዜ ሁሉ እና በተለይም ደግሞ ነገሮች ወደ ጥሩ ፍጻሜ እየተጓዙ አለመሆናቸውን በምትረዳበት ወቅቶች ሁሉ ጭንቀት ውስጥ የምትገባ ሴት ዓይነት አይደለችም ብለዋል። ይሁን እንጅ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ባለመሄዳቸው የተነሳ በጠብ እና በጥላቻ ለነገሮች ምላሽ የምትሰጥ ዓይነት ሰው አልነበረችም በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ሕይወት በጥሩ ሁኔታ በማይጓዝበት ወቅት ሊከሰት የሚችል ጉዳይ ነበር ብለዋል።  “ማሪያም ግን ማዳመጥ የምትችል ሴት ነበረች” ያሉት ቅዱስነታቸው የተቀበለችሁን ይህንን ሕልውና ለእኛም በአደራ አስረክባናለች ካሉ ቡኃል ይህንንም ውርስ ያወረሰችን በሕይወቷ ውስጥ ገጥመዋት በነበረው በደስታ ወቅቶች ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በሕይወት ውስጥ ልከሰቱ ከሚችሉ በተለይም ደግሞ ልጇ በደረቅ እንጨት በተሠራ መስቀል ላይ በነበረበት ወቅት በተሰማት አሳዛኝ የሆነ ሁኔታ ጭምር ነው ያወረሰችን ብለዋል።

ማሪያም በድጋሚ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ብቅ ማለት የጀመረችው ኢየሱስ ለመስቀል ሞት ተላልፎ በተሰጠበት ቀን ነበር በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የቅዱስ ወንጌል ጸሐፊዎች ይህንን የእርሷን ዘግይቶ ብቅ ማለት ልጇ አብን በመታዘዝ ላይ በመሆኑ የተነሳ ይህ ምስጢር ይፈጸም ዘንድ ዝም ማለቷን ለማሳየት ፈልገው የፈጸሙት ጉዳይ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ነገር ግን በጣም ብዙ እና ጥሩ የሚባሉ የኢየሱስ የቅርብ ጓደኞች በፍርሃት ምክንያት እርሱን ጥለውት በሸሹበት በጣም ወሳኝ በሚባል ወቅት ነበር ማሪያም ብቅ ማለት የጀመረችው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እናቶች ከዳተኞች አይደሉም” ካሉ ቡኃላ በዚያን ጊዜ በመስቀሉ ሥር ማንም ሰው በቃላት መግለጽ የምያዳግተውን ያንን የጭካኔ ተግባር እየተመለከተች፣ ያ ንጹህ ሰው በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት፣ የልጇን የመጨረሻውን ስቃዩን በመመልከት እስከ መጨረሻ የሕይወት እስትንፋሱ አብራ መቆየቷ የእናትነት ባህሪዋን ለማሳየት ፈልገው ያደርጉት ነገር ነው ብለዋል። አራቱ ወንጌላዊያን ተመሳሳይ የሆነ የትረካ ስልት የተጠቀሙ እና በጣም ብዙ ማብራርያን የያዙ ናቸው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእናቱን በመስቀል ስር መኖር ቀለል ባለ ቋንቋ “እዛ ነበረች” በማለት ነበር የገልጸት ብለዋል። ስለ እርሷ ስሜት ምንም አልተናገሩም፣ ሐዘኗንም የሚገልጽ ምንም ነገር አልጻፉም ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው የእነዚህ ነገሮች ዝርዝር ሁኔታ ግን በባለ ቅኔዎች እና በሰዓሊያን አማካይነት ወደ ስነ-ጥበብ እና የስነ-ጹሑፍ ታሪክ ተለውጡዋል ብለዋል።

በቀላል ቋንቋ ማሪያም በመሰቀሉ ሥር ነበረች፣ ይቺ ወጣት የናዝሬት ሴት፣ አንደኛውን የእግዚኣብሔር ልጅ በእቅፋ ያስገባች ሴት በስተመጨረሻ ሁሉም ነገር ጨልሞባት ነበር በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በጨለማ እና ጭጋጋማ በሆነ ስፍራ ውስጥ ሕይወታችን በሚወድቅበት ጊዜ ሁሉ አንድ ሻማ ስናበራ ማሪያም በዚያ ትገኛለች ብለዋል። ምንም እንኳን እርሷ ልጇ ይህንን ሁሉ መከራ እየተቀበለ የሚገኘው በእኛ ምክንያት መሆኑን እና ከሙታን እንደ ሚነሳም ብታውቅም፣ ለእግዚኣብሔር እቅድ ያላትን ታማኝነት ለመግለጽ በማሰብ እና ከመጀመሪያ አንስቶ ራሷን እንደ የእግዚኣብሔር አገልጋይ አድርጋ ያቀረበች በመሆኗ የተነሳ ሁልጊዜም ቢሆን ማንም ሰው ሲሰቃይ ከእናትነት ስሜቷ በመነሳት እርሷም በቀላሉ ሐዘን ውስጥ ትገባለች ብለዋል።

ከመጀመሪያዎቹ  የቤተ ክርስቲያን ጊዜያት አንስቶ ደቀ መዛሙርቱ አንዱ ሲክደው፣ በጣም ብዙ የሚባሉት ደግሞ ጥለውት ሲሸሹ፣ በአጠቃላይ ሁሉም ደቀ መዛሙርት በፍርሃት በተሸበሩበት በዚያ ወቅት እነዚህ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ፈተናዎችን መቋቋም ባቃታቸው ወቅት እርሷ የተስፋ እናት ሆና ነበር በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ማሪያም በጽናት ቁማ ነበር ካሉ ቡኃላ ምንም እንኳን በመጀመሪያዎቹ የቤተ ክርስቲያን ምስረታ ወቅት በትንሣኤው ብርሃን የተሞላ ቢሆንም ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩም በዓለም ውስጥ በሚፈጠሩ ነገሮች የተነሳ በፍርሃት የተዋጠች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ብለዋል።

ለዚህም ነው እኛ ሁላችን እርሷን እንደ እናታችን የምንወዳት በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁሉም ነገሮች መጥፎ መስለውን በሚታዩን ጊዜያት ሁሉ በትዕግስት መጠበቅ እንደ ሚገባን ታስተምረናለች ካሉ ቡኃላ እርሷ ሁሌም ቢሆን በእግዚኣብሔር ምስጢር ትታመናለች በችግር ውስጥ በምንሆንባቸው ጊዜያት ሁሉ የኢየሱስ እናት የሆነችው ማሪያም ጉዞዎቻችንን በአሸናፊነት እንድንወጣ ታግዘናለች ካሉ ቡኃል ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.