2017-05-08 16:57:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ብፁዕነታቸው ጎርጎርዮስ ሦስተኛ፥ የወንጌልና የሰላም አገልጋይ


በአንጽዮኪያ የግርካዊ መልኪታ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕነታቸው ጎርጎርዮስ ሦስተኛ ላሓም በግሪካዊ መልኪታ ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና መሰረት በእድሜ መግፋት ምክንያት በዚያች ቤተ ክርስቲያን ካላቸው ሐዋርያዊ መስተናብርነት ኃላፊነታቸው እንዲነሱ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያቀረቡት ጥያቄ ቅዱስነታቸው ተቀብለው አወንታዊ ምላሽ እንደሰጡበት የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

የግሪክ መልኪታዊ ስርዓት የምትከለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ የአንጽዮኪያ ፓትሪያርክ እስክትመርጥ ድረስ በሕገ ቀኖናው መሠረት በእድሜ በለጥ ያሉት በጊዚያዊነት እንዲተኩ የሚለው አንቀጽ ያስቀመጠው መስፈርት በመከተል የአለፖ የግሪክ መልኪታዊ ሥርዓት ለምትከተለው ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዣን ክለመንት ዣንባርት በሐዋርያዊ መሪነት ሥር በጊዚያዊ መሥተናብር ሐዋርያዊ ሥልጣን ሥር እንድትምራ መወሰናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለፓትሪያርክ ቅዱስነታቸው ጎርጎርዮስ ሦስተኛ ላሐም ባስተላለፉት መልእክት፥ ብፁዕነታቸው የወንጌልና የሰላም የሕዝበ እግዚአብሔር አገልጋይ በማለት እንደገለጧቸውና በዚያች ስቃይና አመጽ ግጭት በተሞላባት አገረ ሶሪያ ሰላም እንዲረጋገጥ መግባባት እንዲሰፍን ካለ መታከት የሚሰጡት አስተዋጽኦ ጠቅሰው በዚህ አጋጣሚም ለሁሉም የግሪክ መልኪታዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የውህደት የሱታፌና የወንጌል አገልግሎት ትእምርት የሆነውን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በእምነት የማጽናናት ጥሪ ምልክት የሆነው ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን በማረጋገጥ በጸሎቲ ዘወትር ህልዋን ናችህ እንዳሉ ያመለክታል።

ይክ በእንዲህ እንዳለም ብፁዕነታቸው ጎርጎሪዮስ ሦስተኛ ላሓም 85 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በሶሪያ የደማስቆ ርእሰ ቁምስና ክልል በሆነቸው በዳራያ የተወለዱ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በአንጽዮኪያ የግሪክ መልኪታ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ርስቲያን ፓትሪያርክ እንዲሆኑ ተሹመው በዚህ ሐዋርያዊ ሓላፊነትም ለ 17 ዓመት ያገለገሉ መሆናቸው ያስታወሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ በሶሪያ በጠቅላላ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና እርቅ እንዲወርድ በዚህ አገልግሎት በሚሰጡት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚታወቁም ያመልክታል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.