2017-05-06 13:59:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ግትር የሆነ ሐሳብ ያላቸው ክርስቲያኖችን አውግዘው በቤተ/ትያን ውስጥ ትሕትና እንዲሰፍን" ጥሪ አቀረቡ።


“አሁንም ቢሆን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የራሳቸውን ኃጢያት ለመሸፈን በማሰብ ግትር የሆነ አቋም የሚያራምዱ ሰዎች አሉ”። ይህንን የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 27/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው። ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት በእለቱ በተነበበው ከሐዋሪያት ሥራ 9፡1-20 በተወሰደው የመጀመሪያ ምንባብ ላይ በተጠቀሰው ግትር የሆነ ዓላማን በመላበስ ክርስትያኖችን ያሳድድ የነበረው ሳውል ወደ የዋህ እና ታጋሽ የክርስቶስ ወንጌል አብሳሪነት መቀየሩን በሚገልጸው በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

“ሳውል ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ሰማዕቱ እስጢፋኖስ በድንጋይ በተወገረበት ወቅት ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው በወቅቱ ሳውል “ወጣት፣ ግትር እና ምናባዊ አስተሳሰብ” የነበረው ሰው ነበር ካሉ ቡኃላ ሕግ ግትር መሆን እንዳለበት “አምኖ” የተቀበለ ሰውም እንደ ነበረ ጨምረው ገልጸዋል።

ሳውል ግትር አቋም የነበረው ነገር ግን “ታማኝ” የነበረ ሰው ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ ያወገዘው ግትር አቋም ያላቸውን እና “ታማኝ ያልሆኑ” ሰዎችን ነበር ብለዋል።

እነዚህ ግርት አቋም ያላቸው ሰዎች ሁለት ዓይነት ሕይወት ይኖራሉ፣ ራሳቸውን እንደ መልካም፣ ታማኝ አድርገው ያቀርባሉ፣ ነገር ግን በድብቅ ምጥፎ ነገሮችን ይፈጽማሉ። በሌላ በኩል ስንምለከት ደግሞ ይህ ወጣት ሰው ታማኝ ሰው ነበር። ይህንንም አምኖበታል። ይህንን ስል ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ የሚባሉ ወጣቶች በዚህ የግትርነት ፈተና ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ ብዬ አስባለሁ። የተወሰኑት ታማኝ እና መልካም የሆኑ ሰዎች ናቸው። በዚህ በትህትና መንገድ መራመድ እንዲችሉ እግዚኣብሔር እንዲረዳቸው መጸለይ ይገባናል።

ሌሎቹ ግን “ግትርነትን የሚጠቀሙት ድክመታቸውን፣ ኃጢያታቸውን፣ የግል ችግሮቻቸውን ለመሸፈን ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው በሌሎች ሰዎች ላይ በመረማመድ የራሳቸውን ሕይወት መገንባት ይፈልጋሉ ብለዋል። በዚህ ረገድ ሳውል በጣም ግትር የሚባል ሰው ነበር፣ በተለይም መናፍቅ የሆኑ ሰዎችን በሚያገኝበት ወቅት ሁሉ በፍጹም አይታገሳቸውም ነበር፣ እርሱ እንደ መናፍቅ ይቆጣራቸው የነበሩትን ክርስቲያኖች የሚያሳደደው  ለዚሁ ነው። ብያንስ ብያንስ ሳውል ሕጻናትን አይግድልም ነበር። አሁን ባለንበት ዘመን ክርስቲያኖችን የሚያሳድዱ ሰዎች  ግን ሕጻናትንም እንኳን አያስቀሩም።

ሳውል ክርስቲያኖችን በቁጥጥር ስር በማዋል በየሩሳሌም ወደ ሚገኘው እስር ቤት ሊያጉራቸው በማሰብ ወደ ደማስቆ ሄደ። ወደ ደማስቆም በመሄድ ላይ በነበረበት ወቅት “ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛልህ? ከሚል የትህትናን ቃል ከሚናገር አንድ ሰው ጋር ተገናኜ”።

“ይህ ግትር ነገር ግን አቀኛ የሆነ ወጣት ሰው፣ ራሱን እንደ አንድ ሕጻን ልጅ በማድረግ ጌታ ወደ ሚመራው ስፍራ ለማምራት ራሱን አስገዛ”። ይህም “የጌታ ትህትና ኃያል መሆኑን ያሳያል”። ሳውል የነበረው ጳውሎስ ከሆነ ቡኃላ ግን እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ወንጌልን ሰበከ፣ ለእርሱም ሲል ተሰቃዬ፣

ስለዚህም ይህ ሰው ከራሱ የሕይወት ልምድ በመነሳት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ በመንቀሳቀስ ወንጌልን ሰበከ፣ ተሰደደ፣ በብዙ ችግሮችም ውስጥ በማለፍ፣ ከቤተ ክርስቲያን በኩል በደረሰበት መከራ ጭምር፣ እርስ በእርሳቸው በሚጋጩ ክርስቲያኖች ሳይቀር በጣም ተሰቃየ። ነገር ግን ለሕግ በነበረው ከፍተኛ የሆነ ቅንዐት የተነሳ ጌታን ያሳድድ የነበረው ይህ ሰውኃጢያትን በመስራታችህ የተነሳ  ከእግዚኣብሔር ርቃችው ነበር አሁን ግን በሕሊናችው፣ በሰውነታችው፣ በአጠቃላይም ሁለነተናችው ነቀፋ የሌለባችው በመሆናችው ለእግዚኣብሔር ምስጋናን አቅርቡበማለት ለክርስቲያኖች ተናግሩዋል።

“በቂ በሆነ ነገር፣ በግትርነት እና በየዋህነት መካከል ውይይት ሊኖር ይችላል” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም “አንድ አቀኛ በሆነ ሰው እና በኢየሱስ መካከል የሚደረግ ውይይት ጣፋጭ የሆነ ውይይት ነው” ብለዋል። “ከዚህም ነው የእዚህ ከወጣትነቱ ጀመሮ ታዋቂ የነበረ፣ እስጢፋኖስ ሲወገር በስፍራው የነበረ፣ አሁን ግን ክርስቲያኖች እርስ በእርሳቸው በመጣላታቸው የተነሳ የተካደው ሰው ታሪክ የሚጀምረው ከዚሁ ነው” ብለዋል። ለአንድ አንዶቹ የጳውሎስ ሕይወት ልክ እንደ ክርስቶስ ሕይወት የውድቀት ሕይወት ይመስላል።

የክርስቲያን መንገደ መሆን የሚገባው ክርስቶስ ባሳየን መንገድ ላይ ወደ ፊት መራመድ ነው፣ ይህም የስብከተ ወንጌል መንገድ፣ የስቃይ መንገድ፣ የመስቀል መንገድ፣ የትንሣኤ መንገድ ነው። ዛሬ ለየት ባለ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሚገኙ እንደ ሳውል ግትር ለሆኑ ሰዎች፣ አቀኞች ነገር ግን ግትር ለሆኑ ሰዎች፣ ቅንዐት ላላቸው ነገር ግን ስህተት በመፈጸም ላይ ለሚገኙ ሰዎች እንጸልይ። አስመሳይ ለሆኑ ግትር ሰዎች፣ኢየሱስ እነርሱ የሚሉዋችሁን እንጂ የሚያደርጉትን ነገር አትፈጽሙእንዳለቸው ሁሉ ዛሬ ሁለት ዓይነት ሕይወት ለሚኖሩ ሰዎች  ጸሎት ማድረግ ይገብናል ካሉ ቡኃላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.