2017-05-05 17:22:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ የቫቲካን የመገናኛ ብዙኃን ኅዳሴ ዓላማ ወንጌልን ለሁሉም ለማድረስ የሚል ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም.  በቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ድሕፈት ቤት ዋና ጸሓፊ የኔታ ዳሪዮ ቪጋኖ የተሸኙትን ለቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ቤት ጽሕፈት እያካሄደው ባለው አንደኛው ምሉእ ዓመታዊ ጉባኤ ተሳታፍያንን ተቀብለው “የሥነ አኃዝ ባህል የሚያቀርበውን አዲስ ግኝት የመጠቀም ብቃት ባለው የመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ወንጌል ለሁሉም በወቅታዊው ዓለም ማእቅፍ ማድረስ” የሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ትኩረት ያደረገ ቃለ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገለጡ።

አዲሱን በሥነ አኃዝ የተገነባው የመገናኛ ብዙኃን በመጠቀም የምህረት ወንጌል ለሁሉም ለተለያዩ ባህል ሰዎች ማበሰር ያለው አስፈላጊነት ያመለከቱት ቅዱስ አባታችን፥ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲከወን ያሳሰቡት ኅዳሴ ተከትሎ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በትክክል ኣ.ኤ.አ. ሰነ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በሳቸው ሕግ ውሳኔ የተቋቋመው የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ ተንከባካቢ ቤት ጽሕፈት በአዲስ መንፍስና በሥነ አኃዝ እድገት ማእቅፍ በአዲስ ስልትና ብቃት ቅድስት መንበርን በብቃትና በተገቢነት ማገናኘት የሚል ዓላማ ያደረገ እየተከተለው ያለው እቅድ፡ ኅዳሴው የማሰብ ችሎታ መረጃዊ ብልህነት የተከተለ ሆኖ የተለመደውን ለብዙ ዓመት ስትገለገልበት የነበርከውን ስልት መቀየር ግራ ሊያጋባ ይችል ይሆናል ነገር ግን ነገሮችን ስልቶችን ለማደስ የነበረውን ልማዳዊ ሁነት ላይ አወንታዊ ዓመጽ መከወን ግድ ይሆናል። አወንታዊ ዓመጹ ለአዲስ ግንባታ መሠረት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ይኸንን ጽሕፈ ቤት የሚያቋቁመው ባላቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን መሰረት ይፋ ባደረጉት ሕግ ውስጥ ተጠቅሶ ይገኛል።

የቫቲካን የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት የቅድስት መንበር የማስታወቂያና የማኅበራዊ ግንኙነት በአዲስ መንፈስ መከለስና የበለጠ ለማድረግ በሚለው ቅዉም ሃሳብ ላይ የጸና ኅዳሴ ተከትሎ የተቋቋመ የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጽሕፈ ቤት መሆኑ ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ምዕዳን ማብራራታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ አስታውቋል።

በዚህ ሂደትም አንጻር እ.ኤ.አ. ከሚቀጥለው 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በዚህ አዲስ ጽሕፈ ቤት ሥር ይጠቃለላል። የቫቲካን ረዲዮም የዚህ አዲስ ጽሕፈት ቤት አካል ሆኗል። የቫቲካን ረዲዮ የአዲስ የሥነ አኃዝ ግኝት ተጠቃሚ በማድረግ ወቅታዊ ሆኖ ለወቅታዊው ዓለም የተገባ ማድረግ ግድ ነው፡ ስለዚህ ኅዳሴው ቅርጽን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ይዞታውም ችምር በበለጠ እንዲካተትና እዲስተዋል የሚል ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ አያይዘው፥

የራዲዮ የስርጭት አገልግሎት ኅዳሴው በሙላት የሚከተል ቢሆንም ነገር ግን የሥነ አኃዝ እደ ጥበባዊ ግኝት በሙላት ተጠቃሚ ለመሆን ያልቻሉት ለምሳሌ አፍሪቃን የመሳሰሉት የተለያየ ችግር ያለባቸውን ክልሎች የሚዘነጋ ወይንም ችላ የሚል አይደለም ስለዚህ ወደ አፍሪቃ በአጭር ሞገድ የማሰራጨቱ መርሐ ግብር ቀጣይነት ይኖረዋል፡ ህዳሴው ያንን የአጭር ሞገድ አጠቃቀሙን በተስተዋለ መንገድ እንዲናበር የሚል እንጂ ጨርሶ የአጭር መጎድ ስርጭት ይቋረጥ የሚል አለ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በአጽንኦት ማስታወቃቸው ይጠቁማሉ።

“ሥራው ዓቢይ ነው ባልተናነሰ መልኩም ተግዳሮቱም አቢይና ሰፊ ነው። ቢሆንም ሥራው መፈጸመ ይኖበታል። ተግዳሮቱን አይቶ ሥራ ማስተጓጐል ምክንያታዊ አይሆንም። ታሪክ በእርግጥ የገጠመኝ ሃብት ነው። ስለዚህ ያንን የገጠመኝ ሃብት ወደ መጻኢ በሚያነቃቃ መንገድ መጠቀም ያስፈልጋል። ካልሆነ ለመስህብነት የሚማርክ የተዋበ ቤተ መዘክር ሆኖ ይቀራል። በዚህ አዲስ የግንኙነት ስልት ግንባታ ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ታታሪነት የሚጠይቀው የሙያ ኅዳሴና ወቅታዊ ሕንጸ እንዲያገኙ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው”

ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስ በማስከተልም፥

“ህዳሴውን ሙሉ በሙሉ እግብ ለማድረስ በሐዋርያዊነት ማለትም የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎና የተልእኮ ብርኃን መመዘኛ በመከተል ድኾችን በከፋ ሰብአዊ ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ የሚገኙትን በተለየ መልኩ ለማሰብና ለእነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል ትኩረት ለመስጠት የሁሉም ንቁ ተሳታፊነትን ይጠይቃል፡ እንዲህ ባለ ሁነትም ወንጌል ለሁሉም ለማድረስ ይቻላል፡ እንዲህ ሲባል በአካባቢ በክልሎች የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ለመተካት መጣጣር ማለት ሳይሆን በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኘውን ማኅበረ ክርስቲያን መደገፍ ማለት ነው”

ካሉ በኋላ “ያለፈው ልዕልናና ክብር ላይ የሙጥኝ ብሎ እንዲህ ነበርኩ ከሚለው ፈተና ተላቆ ልክ እንደ አንድ ቡድን በጣምራ ወቅታዊው የግኑኝነት ዘይቤ ለሚደቅነው ተግዳሮት ወቅታዊው ባህል የሚጠቀውን ዝግጁነት በማሟላት አለ ምንም ፍርሃና ካለ የፖለቲካዊ ትእይንታዊ ምናብ መሥራት ያስፈልጋል”  በማለት የለገሱት ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራቸስካ ሳባቲነሊ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.