2017-05-01 16:45:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በግብጽ ለወጣቶች ያሰሙት ንግግር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የግብጹ የመጀመሪያ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን  በግብጽ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6 ሰዓት ከ 40 ደቂቃ ካይሮ በሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወክል ሕንፃ በመሄድ እዛው ይጠባበቋቸው በነበሩት 300 በሚገመቱ በግብጽ ከሚገኙት የኮምቦኒ ልኡካነ ወንጌል ትምህርት ቤት ተማሪ ወጣቶች አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ቃለ ምዕዳን ለግሰው ማጠናቀቃቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

እንወድዎታለን እናፈቅርዎታለን የሚል ወጣቶቹ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በጋራና በአንድ ድምጽ ካስተጋቡት ቃል በመቀጠል ቅዱስነታቸው፥

“እንደምን አመሻችሁ! ከእናንተ ጋር ስገናኝ ደስታዮ ወሰን የለውም። ከቅርብ እና ከሩቅ እኔን ለማኘት እዚህ ድረስ በመምጣታችሁ በእውነቱ አመስግናችኋለሁ እዚህ ድረስ መምጣታችሁ ለጽናታችሁ ምስክር ነው። ነገ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ  28 ቀን 2017 ዓ.ም. ካይሮ በሚገኘው የእግር ኳስ ሜዳ መሥዋዕተ ቅዳሴ አቀርባለሁ እንደ አንድ ቤተሰብ አብረን እንጸልያለን በጋራ አብረን እንዘምራለን በዓል እናከብራለን። ከዚህ ግኑኝነት ከመሰናበቴ በፊት ግን ከእናንተ ጋር አብሬ ለመጸለይ እወዳለሁ”

ብለው ቅዱስ አባታችን አብረው ከወጣቶቹ ጋር ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችን ሆይ ሲል ያስተማረንን ጸሎት ደግመው እንዳበቁም “ሐዋርያዊ ቡራኬ ከመስጠቴ በፊት ሁላችሁ በዚህች ደቂቃ የሜድዋችሁን የሚጠሉዋችሁን ሁሉንም አስቡ በጽሞና ስላሰብናቸውና ስላስታወስናቸው ሰዎች እንጸልይ” ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው እንዳበቁም ወጣቶች የተሰማቸውን ደስታ በጭብጨባ ካስተጋቡ በኋላ መሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቅ።








All the contents on this site are copyrighted ©.