2017-04-29 09:53:00

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 18ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በግብፅ


የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 18ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በግብፅ

የጉዞ መረዐ ግብር፣ ዓርብ ሚያዝያ 20 እና 21/2009 ..

የጉዞ መነሻ፣  ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሮም፣ ጣሊያን

የመነሻው ሰዓት፣ በሮም የሰዓት አቆጣጠር 10፡45

መድረሻ፡ ካይሮ በግብፅ የሰዓት አቆጣጠር 14፡00

ርቀት፡ 2,350 ኪሎ ሜትር

የበረራው ጊዜ 3፡15 ደቂቃ

መመለሻ፡ ሚያዝያ 21/2009 ዓ.ም. በግብፅ የሰዓት አቆጣጠር 17፡00

ሮም መድረሻ፡ በሮም የሰዓት አቆጣጠር 20፡30

መግቢያ

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች በዛሬው እለት ዝግጅታችን ትኩረት ሰጥተን ወደ እናንተ የምናደርሰው ዘገባ የሚሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የሁለት ቀን ይፋዊ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ በትላንትናው እለት  ወደ ግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ላይ ይሆናል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትነው እለት ማለትም በሚያዚያ 20/2009 ዓ.ም. ጀምሮ በግብፅ በማድረግ ላይ የሚገኙት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ ቡኃላ ያደረጉት 18 ሐዋሪያዊ ጉብኝት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን 2,250 ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው በዛሬው እለት ግብፅ መግባታቸው ተዘግቡዋል።

በአሁኑ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግብፅ የሚያደርጉት ጉብኝት ከ20 አመታት ቡኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚደረግ ጉብኝት መሆኑ የታወቀ ሲሆን እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም. በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዩሐንስ ጳዎሎስ ሁለተኛ በግብጽ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግብፅ የምያደርጉት 18ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት የዛሬ ሦስት ስምንት ገደማ በሆሣዕና በዓል እለት በግብፅ በሚገኙ ሁለት የኮቲክ አብያተ ክርስቲያናት ላይ በአሸባሪዎች በተቃጣው ጥቃት ብዙ ክርስቲያኖች ከተገደሉ እና አብዛኞቹ ደግሞ ከቆሰሉ ከሶስት ሳምንታት ቡኃላ የሚያደርጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ሲሆን በማንኛውም ረገድ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን ጥቃቶች አውግዘዋል፣ በተለያዩ የሐማኖት ተቋማት መካከልም መግባባት እና መከባበር ላይ የተመሰረት ውይይት እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውም ይታወሳል።

የዚህ የቅዱነታቸው 18ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ዋንኛው ዓላማ በታላቁ በአል አዝዓር የእስልምና ማዕከል ዳይሬክተር ኢማም ሼህ አምድ አል ጣይብ፣ የግብፅ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት የሆኑት አብደል ፋታህ ሳሂድ ሁሴን ካሊል አል ሲሲ እንዲሁም እንዲሁም የአጠቃላዩን የግብጽ ሕዝብ 30% የሚወክሉት የግብፅ የኮፕት ክርስቲያኖች ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ቴውድሮስ ሁለተኛ በቀረቡላቸው ግብዣ ምክንያት እንደ ሆነ የታወቀ ሲሆን በተጨማሪም በዚህ ጉብኝታቸው እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ969 ዓ.ም. መቆርቆሩ የሚነገርለት የአል አዝዓር የእስልምና ማዕከል ባዘጋጀው ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ ላይ ተገኝተው ንግግር እንደ ሚያደርጉም ይጠበቃል።

የዓርብ እለት የቅዱስነታቸው የጉብኝት መርሀ ግብር

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.