2017-04-29 14:11:00

ሼህ አመድ አል ጣይብ የታላቁ የአል ዛዓር የእስልምና ማዕከል ዳይሬክተር በዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ ላይ ያደረጉትን ንግግር


ከቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ሼህ አመድ አል ጣይብ የታላቁ የአል ዛዓር የእስልምና ማዕከል ዳይሬክተር በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 20/2009 ዓ.ም. በግብፅ በሚገኘው በታላቁ የአል ዛዓር ማዕከል በመካሄድ ላይ በነበረው ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ ላይ ያደረጉትን ንግግር እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

 

ቸር እና መሐሪ በሆነው በፈጣሪ ስም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከቫቲካን

ክቡራን እና ኩቡራት

ለሁላችሁምአል ሳላሙ ኃሌኩም ዋራ ሕማቱላሕ ባራካቱህበማለት ሰላምታዬን አቀርብላችኃለሁ።

አል ዛዓር እና የሙስሊም መማክርት ጉባሄ አባል የሆናችሁትን ሁሉ ጥሪዬን አክብራችሁ በመቀበል እዚህ በመገኘታችው እንኳን ደኽና መጣችሁ በማለት ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርብላችኃለሁ። ታላቁ የአል ዛዓር መዐከል ያቀረበላችሁን ጥሪ ተቀብላችሁ የሐይማኖት መሪዎች የተጣለባቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት፣ ለሰላም ለመሥራት የተጠራን ሙሁራን በመሆን በብጥብጦች የታመሱትን ሀገራት መልሰው እንድያገግሙ፣ ጦርነትን በመሸሽ ወደ በርሃ የሚሰደዱ ሰዎችን ለመታደግ የሰላም መልእክተኞች ሆናችው ግብፅን እና ታላቁን የአል ዛዓር መዕከልን ለመጎብኘት እዚህ በመገኘታችሁም አመሰግናለሁ። ብዙ ሰዎች እናት ሀገራቸውን በመተው በሰላም ይድረሱ ወይም አይድረሱ፣ ይሙቱ ወይም በባሕር ሰጥመው ይቅሩ ወይም አይቅሩ እርግጠኛ ሳይሆኑ ረጅም የሆነ ጉዞ  በማድረግ አዲስ ተስፋ የሚሰጣቸውን ሀገር ይፈልጋሉ። እንደ አለመታደል ሆኖ አሰቃቂ በሆነ መልኩ በየባሕር ዳርቻዎች ላይ የሰው ልጆችን ቅሪት አካል ማየት እየተለመደ መጥቱዋል።

ይህምበሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በሰብዓዊነት ላይ እየደረሰ የሚገኝ አሳዛኝ የሆነ እውነታ ነውብል ማጋነን አይመስለኝም። ማንም ሰው ይህንን አሰቃቂ እና አሳዛኝ እልቂት ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ተንትኖ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይችልም፣ ምክንያቱም ይህ ጉዳይ በጣም ድኽ የሚባሉትን፣ ወላጅ አልባ የሆኑትን ሕጻናትን፣ መበለቶችን እና አረጋዊያን ሳይቀር በቀጥታ እየጎዳ የሚገኝ ተግባር በመሆኑ ነው። ለዚህ ግን አንድ እና አንድ ምክንያት ብቻ ማስቀመጥ ግን እንችላለን፣ ይህም በቀጣይነት ሞትን እያፋጠነ የሚገኘው፣ የዓለማቀፍ ስምምነቶች ግድ ዬለሽነትን በማሳየታቸው ተበረታተው በስውር በሚደረጉ ስምምነቶች ምክንያት የሚፈጸመው በጦር መሳሪያ ምክንያት ነው ማለት እንችላለን። በሚነዙት የጥላቻ ምልእክቶች ምክንያት ግለት፣ ሃይማኖታዊ ሁከት፣ አክራሪነት፣ በጎሳዎች መካከል ግጭት፣ በአንድ ሀገር ወስጥ በሚኖሩ ሰዎች መካከል ልዩነቶችን በመፍጠር የሰው ልጅ ሕይወት ሊወጣው ወደ ማይችልበት የሲሆል መከራ ውስጥ ይከቱታል።

በጣም የሚያስገርመው ነገር ደግሞ ይህ ተግባር ክፍለ ዘመን ባስቆጠረ ስልጣኔ በሚታይበት፣ ከተሞች በተስፋፉበት፣ የሰው ልጆች መብት በተከበረበት፣ የመማር ማስተማር ሂደት በከፍተኛ የለውጥ ጎዳና ላይ ባለበት፣ አስገራሚ የሆነ የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ምጥቀት በሚታይበት አሁን ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን እየተፈጸመ የሚገኝ ተግባር መሆኑ ነው።

አሁን ያለንበት ዓለማችን የሐይማኖት ተቋማት ተልዕኮዋቸውን እንዲወጡ ለመፍቀድ ዝግጁ ነው ብዬ አላስብም። የትኛውንም ሐይማኖት፣ ቀለምን፣ ቋንቋን እና ዘር ሳይለይ፣ ሰብዓዊ መብቶችንም በማስከበር፣ ፍትህና በእኩልነት እንዲሰፍኑ በማድረግ የሰላምን እሴቶችን ማጉላት ያስፈልጋል።

ከሁሉም አስቀድመን ሐይማኖትን ከሐሰተኛ፣ ክፉ ተግባራትን ከማስፈጸሚያነት፣ ከአስመሳይነት ወይም ሐስተኛ ሐይማኖተኛነትን ከሚሉት  ጽንሰ ሐሳቦች ነጻ ልናወጣው ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ክፉ ጽንሰ ሐሳቦች ጠብን በመጫር፣ ጥላቻን በማስፋፋት ነውጥ ስለ ሚፈጥሩ ነው። በጣም ጥቂት የሚባሉ ሐይማኖተኛ ሰዎች በሚፈጽሙት ወንጀል ሐይማኖትን መወንጀል አስፈላጊ አይደለም። ለምሳሌም ጥቂት የሚባሉ ሰዎች በተወሰኑ የእስልምና ጥቅሶችን ተጽእኖ ምክንያት እና ጥቅሶቹንም በቸልተኝነት በመተርጎም በሚያፈሱት ደም፣ በሚገሉት ሰው፣ ጥፋትን ከምያፋፍሙ ተግባራቸው ምክንያት የእስልምና ሐይማኖት እንደ አሸባሪዎች ሐይማኖት ተደርጎ መቆጠር በፍጹም የለበትም። አለመታደል ሆኑ እነዚህ ሰዎች በቂ የሆነ የገንዘብ ምንጭ፣ የጦር መሳሪያ እና ስልጠና ይሰጣቸዋል። በተመሳሳይም የተወሰኑ የክርስትና እምነት ተከታዮች መስቀልን ይዘው ወንድ፣ ሴት፣ ሕፃናት፣ ተዋጊ እና እስረኛን ሳይለዩ በሚፈጽሙት አሰቃቂ ተግባር ምክንያት ክርስትና የሽብር ማፋፋሚያ እምነት ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም።

የተከበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እውነትን በመደገፍ፣ የእስልምና ሐይማኖት የግጭት እና የአሸባሪዎች ሐይማኖት ነው! የሚለውን ወቀሳ ሁሌም ቢሆን ስለሚቃወሙት ከልብ የመነጨ አድናቆታችንን ልንገልጽሎት እወዳለሁ። እርሶ እና በዚህ የተገኙ ታዋቂ የምሕራባዊያን እና የምስራቃዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሐይማኖት አባቶች ሐይማኖታዊ አስተሳሰቦችን፣ የሐይማኖት መግለጫ ምልክቶችን፣ ሐይማኖታዊ የሆኑ እሴቶች ከጥቃት እንዲጠበቁ የምታደርጉትን፣ እንዲሁም ቅጥረኛ በሆኑ ሰዎች ምክንያት በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል ግጭትን የሚዘሩትን ሁሉ ለመከላከል የምታደርጉትን ጥረት ከልብ አደንቃለሁኝ። ይህ የአል አዛዓር ተቋም ሰዎች በጋራ እንዲኖሩ፣ የጠፋው የውይይት መንፈስ በድጋሚ እንዲያንሰራራ፣ የሰዎችን እምነት ለማክበር እና ለመጠበቅ የሚሠሩ ማንኛውም ዓይነት ተግባራትን ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነው።

ሁላችንም ምድራችንን ከሚበዘብዙዋት እና ከሚያስበዘብዙዋት ሰዎች ማዳን አለብን። እኛ ሁላችን በስልጣኔ ንድፈ ሐሳብ ምክንያት የሚፈጸሙትን ግጭቶች፣ ታሪክን በመቋጨት ሐይማኖት የለሽነትን ለማስፈን የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን፣ ሐይማኖታዊ ያለሆነ ዘመናዊነትን ይህንንም ተከትሎ የሚፈጠሩትን ክፉ የሆኑ የጎንዮሽ እክሎችን እየፈጠረ የሚገኘውን  የፖሌቲካ ጫና መቃወም አለብን።

በመጨረሻም የምሕረት ምንጭ የሆነው እግዚኣብሔር ይህንን ስብሰባችንን የሰላምን ባሕል፣ ወንድማማችነትን እና አብሮ መኖርን የማጠናከሪያ እድል እንዲክፍትልን እለምናለሁኝ።

በጣም አመስግናለሁኝ

ታላቁ ኢማም ሼህ አህመድ አል ጣይብ

የታላቁ የአል አዛዓር ሼህ

ሚያዝያ 28/2017 .. ካይሮ ግብፅ

 








All the contents on this site are copyrighted ©.