2017-04-24 15:44:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ "ምሕረት ማድረግ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ሊሆን ይገባል" አሉ።


ከፋሲካ በዓል ቡኃላ የሚገኘው ሰንበት ዳግማዊ ትንሣኤ ሰንበት ይባላል። ጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ በፋሲካ ቀን ከሙታን ከተነሣ ቡኃላ ለመቅደላዊት ማሪያም እና ለሌላኛዋ ማሪያም፣ ቀጥሎም  ለሐዋሪያቱ መገለጡ የሚታወቅ ሲሆን ከስምንት ቀን ቡኃላ ደግም ሐዋሪያት በፍርሃት ተውጠው በራቸውን ዝግተው በመጸላይ ላይ በነበሩበት ወቅት በድጋሚ ተግልጦላቸው “ሰላም ለእናንተ ይሁን አብ እኔን እንደ ላከኝ እኔም እናንተን እልካችኃለው” ብሎ የተናገረበት ሰንበት በመሆኑ የተነሳ ዳግማዊ ትንሣኤ ይባላል። በተጨማሪም ይህ ቀን በተለምዶ በላቲን ቋንቋ “ኢን አልቢስ in Albis” ይባላል። ይህም የሚያሳየው በፋሲካ በዓል የዋዜማ ቅዳሴ ወቅት በሚካሄደው የጥምቀት ስነ-ስርዓት ላይ ነጭ ልብስ በመልበስ ምስጢረ ጥምቀትን የተቀበሉትን ሰዎች ለማስታወስ የሚደረግ በዓልም ተደርጎ ይቆጠራል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በዚሁ እለት ማለትም በሚያዝያ 15/2009 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚያሳርጉት “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ፣ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነስቱዋል እና” ከሚለው ጸሎት ቡኃላ ባስተላለፉት መልእክታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ከትንሣኤ ቀን ሰንበት ቡኃላ ያለው ሰንበት እንደ የአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር 2000 ዓ.ም. ጀምሮ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ይህን የሰንበት ቀን “የእግዚኣብሔር መለኮታዊ ምሕረት የሚዘከርበት ወይም ደግሞ የሚታሰብበት ሰንበት እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው  አስታውሰዋል።

ምንም እንኳን በባለፉት ወራት ውስጥ ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመትን በደመቀ መልኩ ተከብሮ ያለፈ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን በዛሬው የሰንበት እለት ደግሞ ከእግዚኣብሔር ምሕረት የሚፈልቀውን ፀጋ በድጋሚ የምናስቀጥልበት ሰንበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በእለቱ ከዩሐንስ ወንጌል 20፡19-31 ተወስዶ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመስርተው ኢየሱስ ለሐዋሪያቱ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፣ እናንተ የሰዎችን ኃጢያት ይቅር ብትሉ ይቅር ይባልላቸዋል” በማለት ተናግሮ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ከሙታን በተነሳበት ቀን የኃጢያት ስሬዔት እና ምሕረት የተገኘበት ቀን መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ከሙታን የተነሳው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእርሱን ተልዕኮ በምድር ላይ ታስቀጥል ዘንድ  ለቤተ ክርስቲያን በቀዳሚነት ሰጥቷት የነበረው የመጀመሪያ ተልእኮ ተጨባጭ በሆነ መልኩ እግዚኣብሔር መሐሪ መሆኑን ለሁሉም እንድታውጅ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም የልብ ሰላምን ለእኛ በመስጠት እና ከጌታ ጋር በድጋሜ እንድንገናኝ  በማድረግ ተጨባጭ በሆነ ምልክት የእግዚኣብሔር ምሕረት የሚገለጽበት መሆኑንም ገልጸዋል።

ምሕረት አሉ ቅዱስነታቸው ምሕረት ከፍተኛ ጥላቻ እና በቀል ትርጉም የሌሽ እንዲሆኑ ያደርጋል  ካሉ ቡኋላ ምሕረት ልባችንን እንድንከፍት በማድረግ በተለይም ብቻቸውን ለሆኑ እና ለተገለሉ ሰዎች ቅርብ እንድንሆን ያደርገናል ብለዋል።

ምሕረት የፍትህ፣ የእርቅ እና የሰላም መሳሪያ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው በጥቅሉም ምሕረት የእምነታችን የማዕዘን ድንጋይ ነው ኢየሱስ ከሙታን መነሳቱን የምንገልጽበት ተጨባጭ የሆነ ምልክት ነው ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን መልእክት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.