2017-04-22 10:21:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እና ፓትርያርክ በርተሌሜዎስ ቀዳማዊ በሚያዝያ 20 እና 21/2009 ዓ.ም. ግብፅን እንደ ሚጎበኙ ተገለጸ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳስት ፍራንቸስኮ እና የቁስጢንጢናያው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ የሆኑት ፓትሪያርክ በርተሌሜዎስ ቀዳማዊ በሚያዝያ 20 እና 21/2009 ዓ.ም. በግብፅ በሚገኘው በታላቁ የአላዓዛር ኢማም የእስልምና መዓከል በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሰላም ጉባሄ ላይ ይገኙ ዘንድ በሼክ አህመድ አል ጣይብ መጋበዛቸው ተገለጸ።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ በግብፅ በሚያደርጉት የሁለት ቀን ይፋዊ ጉብኝት ከግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ ኣል አዚዝ ጋር እንደ ሚገናኙ የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም በግብፅ ሀገር ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚያሳርጉም ጨምሮ ተገልጹአል።

የቅዱስነታቸው የግብፅ ይፋዊ ጉብኝት በቅርቡ በኮፕቲክ የኦርቶዶክስ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን ላይ በተሰነዘረው የአሸባሪዎች የቦንብ ጥቃት 45 ሰዎች መገደላቸው እና በርከት ያሉ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ከተገለጸ ወር ባልሞላበት ጊዜ መሆኑም ታውቁዋል።

ቀደም ሲል በግብፅ የቫቲካን ልዑክ የነበሩና በቫቲካን በሐይማኖቶች መካከል የሚካሄደውን ውይይት የሚያስተባብረው ጽሕፈት ቤት የበላይ ሐላፊ የነበሩት ሊቀ ጳጳስ ሚካኤል ፊዝጌራልድ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግብፅ የሚያደርጉት ጉብኝት ሊኖረው የሚችለውን እንድምታ አስመልክተው እንደ ገለጹት በዚህ በተለይም በአሁኑ ወቅት አሸባሪዎች በሚፈጽሙት ጥቃት ምክንያት ከፍተኛ በሆነ ችግር እና እርግጠኛ መሆን በተሳነው ማኅበረሰስብ ውስጥ የቅዱስነታቸው መገኘት ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ አስተዋጾ እንደ ሚኖረው ገልጸዋል።

ይህ ጉብኝት በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የተደረገ የመጀመሪያው ይፋዊ ጉብኝት አለመሆኑን የጠቀሱት ሊቀ ጳጳስ ሚካኤል ፊዝጌራልድ እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም. በወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዩሐንስ ጳውሎስ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸው እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

ሊቀ ጳጳስ ሚካኤል ፊዝጌራልድ እንደ ገለጹት ከጊዜ ወደ ጊዜ የግብፅ የኮቲክ ቤተ ክርስቲያን መሪ በሆኑት ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ቴውድሮስ እና በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መኃከል ያለው መግባባት እና ግንኙነት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው ለዚህም በዋቢነት ያስቀመጡት ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ቴውድሮስ የአሌክሳንደሪያ ፓትሪያርክ ሆነው በተመረጡበት ወቅት ከግብፅ ውጪ ያደረጉት የመጀመሪያው ጉዞ ወደ ቫቲካን እንደ ነበረ አስታውሰው ይህ አሁን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግብፅ የሚያደርጉት ጉብኝት የሁለቱን ሊቃነ ጳጳሳት ወዳጅነት ወደ ተሻለ ደረጃ ያደርሰዋል ብለው እንደ ሚያምኑም ጨምረው ገልጸዋል።

ሊቀ ጳጳስ ሚካኤል ፊዝጌራልድ ጨምረው እንደ ገለጹት በእነዚ ታላላቅ የሐይማኖት መሪዎች መኃከል የሚደረገው ውይይት ከምስራቃዊያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር የሚደረገውን ግንኙነት እንደ ሚያሻሽለው የገለጹ ሲሆን የአሁኑ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የግብጽ ጉብኝት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መሐከል ባለው የነገረ መለኮት ልዩነት ላይ ያተኮረ ውይይት የሚደረግበት ጉብኝት ሳይሆን በተቃራኒው በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ሊቃነ ጳጳሳት መኃከል ያለውን ግላዊ ግንኙነት ለማጠናከር ታቅዶ የሚደረግ ግንኙነት እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የግብፅ ጉብኝት የእስልምና እምነት ተከታይ በሆኑ የዓለማችን ሕዝቦች ውስጥ ሊኖረው ስለሚችለው እንድምታ የተጠየቁት ሊቀ ጳጳስ ሚካኤል ፊዝጌራልድ ሲመልሱ የዚህ ጉብኝት  ዋነኛው ዓላማ ከሆኑት ውስጥ አንዱ በግብፅ በሚገኘው ታላቁ የአልዓዛር የእስልምና ማዕከል እና በቫቲካን መኃከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደ ሆነ ገልጸው ለዚህም ግንኙነት መጠናከር በቅርቡ የታላቁ የአልዓዛር የእስልምና ማዕከል ዋንኛው ኢማም የሆኑት ሼክ አህመድ ኣል ታይብ በሮም ተገኝተው ቫቲካንን መጎብኘታቸው እና ይህም የቅዱስነታቸው ጉብኝት ለዚያ ጉብኝት ምላሽ በመሆኑ በጣም የሚደነቅ ጉብኝት መሆኑን ከገለጹ ቡኃላ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.