2017-04-21 17:05:00

በቨነዝዌላ የተካሄደው ጸረ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ያነጣጠረ ሕዝባዊ ዓመጽና የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ስለ ጉዳዩ የሰጡበት መግለጫ


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በመላ አገረ ቨነዝዌላ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ማዱሮ የሚቃወም እጅግ ኃይለኛና መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ አመጽ መታየቱ ሲገለጥ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በበኩሉም ማንኛውም የተቃውሞ አድማ ሰላማዊ መሆን ይገባዋል በማለት አያይዘውም የአገሪቱ መንግሥት የደሞክራሲ ሥርዓት መግለጫና መስፈርት ናቸው የሚባሉትን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በውስጥ የሚያካትተው ባህርይ የሰረዘ ይመስላል ሲል ወቀሳ መሰንዘሩ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።

ይኽ ብዙ ሺሕ የሚገመት ሕዝብ  የተሳተፈበት በተለያዩ የአግሪቱ ከተሞች የተስተናገደው ጸረ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ማዱሮ ያቀና ሕዝባዊ ዓመጽ የኅብረተሰብአዊ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም ተከታይ የሆኑትን ርእሰ ብሔሩ የአገሪቱ መንግሥታዊ ስርዓት ወደ ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት እየቀየሩት ናቸው የሚል ወቀሳ ያነገበ እንደነበርም የገለጡት የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አያይዘው፥ ሕዝባዊ ዓመጹን ለመቆጣጠር በተሰማራው የጸጥታው ኃይል አባላትና በአድመኞች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሳቢያ ሁለት ወጣቶችና አንድ የጸጥታ ኃይል አባል መገደላቸው ገልጠው፥ በጠቅላላ ባለፉት ሦስት ሳምንታ ውስጥ በተደጋጋሚ በታየው ህዝባዊ ዓአጽ ምክንያት ስምንት ሰዎች ሕይወታቸው እንዳጡና በብዙ መቶ የሚገመቱ ደግሞ መታሰራቸው ከአገሪቱ የሚሰራጩትን ዜና ዋቢ በማረግ ይጠቁማሉ።

 ርእሰ ብሔር ማዱሮ በበኩላቸውም ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በቨነዝዌላ እንዲፈጸም የሚፈልገው መፈንቅለ መንግሥት እግብ ለማድረስ አልሞ ያነሳሳው የተቃውሞ ሰልፍ ነው ሲል በተቃዋሚው የፖለቲካ ኃይሎች ላይ ወቀሳ ሲሰነዝሩ ያም ሆኖ ይህ የተባበሩት የአመሪካ መንሥታት በቨነዝዊላ ለተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ዓመጽ ተጠያቂ አይደለሁኝም ሲል በሰጠው የማስተባበያ መግለጫ አክሎ በቨነዝዊላ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ ነው ሲል እንደገለጠ  ያስታወቁት ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አያዘው፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች የማያቋርጥ የተቃውሞ ሰልፍ ቀጣይ እንደሚሆን ነው ማለታቸውንም ይጠቁማሉ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም የቨነዝዌላ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በአገሪቱ ተከስቶ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ገልጦ፡ መንግሥት የሰብአዊ መብትና ክብር ካላከበረ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ነኝ ለማለት አይችልም በማለት፥

ዴሞክራሲይ የዜጎች ሰብአዊ መትና ክብር ጥበቃ ማለት ነው

የብፁዓን ጳጳሳቱ ምክር ቤተ፥

“ዲሞክራሲ የዜጎች ሕይወት ሰብአዊ መትና ክብር ጥበቃ ዋስትና የሚሰጥ ነው። እንዲህ በመሆኑም ማንኛውም መንግሥት የዜጎቹ ሰብአዊ መብትና ክብር የሚያከብር ካልሆነ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ነኝ ለማለት አይችልም፡ ዴሞክራሲያዊነቱንና ሕጋዊንቱንም ጭምር ያጣል። ምክንያቱም የአንድ መንግሥት አገልግሎት ዜጎቹን ሁሉ ካለ ምንም የአመለካከትና ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም ልዩነት በእኩል መከላከል የዜጎች ሰብአዊ መብትና ክብር ማስጠበቅ ነው። ሌላው አንድ መንግሥት ዴሞክራሲያዊ መለያውና ተግባሩን የሚያሳጣው ማኅበራዊ ሥልጣናትና ተቋማት ሁሉ በሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት ወይንም የፖሊቲካ ኃይል ፍጹም ቁጥጥር ውስጥ ማድረግ የሚል ስልጣንን ሁሉ የመቆጣጠር ኃይል ሲያደርግ ነው። በመሆኑም የዴሞክራሲ መሥፈርቶች እንዲከበሩ አደራ” እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

ብፁዓን ጳጳሳቱ ህሊናን ድምጽ ማክበርና መተግበር እንዳለበት ምዕዳን ያቀርባሉ

“ለሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት ናቸው የሚባሉት ሕይወት ነጻነት ጤናና ሌሎች ተካታች መብቶች መንከባከብና ማክበር የሁሉም ሰው ልጅ የኃላፊነት ግዴታ ነው፡ ይኽ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንና የሁሉም ምአመናን ኃላፊነት ጭምር ነው። ስለዚህ ሰብአዊ መብትና ክብር ለሁሉምና የሁሉም እንጂ ለአንዱ የፖለቲካ ጎራ ለአንድ የኅብረተሰብ ወይንም ለአንድ የሃይማኖት ወገን የሚመለከት ጉዳይ አይደለም።

በክርስቶስ የሚያምኑ አማኞችና መልካም ፈቃድ ያላችው ሰዎች ሁሉ ለኅሊናቸው ለዴሞክራሲያዊ መሠረታዊ መመሪያዎችና ለሕገ መንግሥት ታዛዥ በመሆን የዜግነት መብታቸውና ግዴታቸውን አውቀው ዜግነታዊ ኃላፊነታቸው እንዲወጡ”

የብፁዓን ጳጳሳቱ ምክር ቤት በማሳሰብ አያይዞ፥ “ሰላማዊ ሰልፍ የማካሄድና ተቃውሞ የማሰማት መብታቸው ሰዎችንና የጋራው ብሔራዊ ጥቅም በሚያከብር ኃላፊነት በተሞላው መንፈስና በሰላምማዊ መንገድ ሊያከናውኑ ይገባል” በማለት ያስተላለፉት መእክት እንዳጠቃለሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.