2017-04-19 16:52:00

እልባት ያጣው የሰደተኞች ጸአት ወደ ኢጣሊያ


ከእድሜ በታች የሆኑት አለ ወላጅና ቤተ ሰብ የተሰደዱ ዜጎችና እርጉዝ ሴቶች የሚገኙባቸው በጠቅላላ አንድ ሺሕ ስምንት መቶ ከሰሓራ በታች ከሚገኙት አገሮች የተወጣጡ ስደተኞች በኢጣሊያ ሲቺሊያ ደሴት በሚገኙት የባህር በር በኩል በተለያዩ ተናንሽ ባለ ሞተር ጀልባዎች ተጉዘው ኢጣሊያ የገቡት ሕገ ወጥ ስደተኞች በካላብሪያ ክፍለ ሃገር በወረዳ በቪቦ ቫለቲያ በሚገኘው በባህር በር በኩል እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ተዘጋጀላቸው የስደተኞች መጠለያ ሰፈር መዛወራቸው ጉዳዩን የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገልጠው፡ ሌሎች 400 የሚገመቱ ስደተኞችም ወደ ካላብሪያ የስደተኞች መጠለያ ሰፈር ዛሬ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. መዛወራቸውንም አስታውቋል።

በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ በመዲትራኒያን የባህር ጉዞ ወደ ኢጣሊያ የገቡት ስደተኞች ዘጠኝ ሺህ መድረሳቸው ሲነገር ከናይጀሪያ ከሰነጋል ከሌሎች ከሰሐራ በታች ከሚገኙት አገሮች የመጡ ሕጻናት ሴቶችና የወራት ዓመት ዕድሜ የሆኑት ጭምር የሚገኙባቸው ሲሆን ላምፐዱዛ የሚገኘው 400 ስደተኞች ብቻ የማስተናገድ ዓቅም ያለው የስደተኞች መጠለያ ማዕከል በአሁኑ ሰዓት ከአንድ ሺሕ በላይ በሚገመቱ ስደተኞች እጅግ መጨናነቁ በላምፐዱዛ ደሴት ቆሞስ አባ ካርመሎ ላ ማግራ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃል ምልልስ ገልጠዋል።

በላምፐዱዛ የሚገኙት ስደተኞች ካሉበት መጠለያ ሰፈር ብዙዉን ጊዜ ለመጸለይም ሆነ የሚያስፈልጋቸው ሰብአዊ መንፈሳዊ እርዳታ ለማግኘት ወደ ቁምስናው ጎራ የሚሉ መሆናቸው አባ ላ ማግራ ገልጠው፡ የደሴቲቱ ሕዝብ ርህሩህ ቢሆንም ቅሉ በአሁኑ ሰዓት ከስደተኛው ብዛት አንጻር በቂ እርዳታ ለማቅረብ አቅም እንደሌለውና በብዛት ሕፃናትና ሴቶች ስደተኞች የተለያየ ችግር የደረሰባቸው ከዓመጽና ሞት በማምለጥ የመጡ በመሆናቸውም ይኸንን ሁሉ ጥለዉት ያለፈው ችግር ሰብአዊ ስነ አእምሮአዊ ማህበራዊ ጠባሳ የጣለባቸው በመሆኑ ጭምር ይኸንን ሁሉ በማገናዘብ ለድጋፋቸው ባለህ አቅም ከመራወጥ ወደ ኋላ ለማለት የማይቻል ነው። እንዲህ በመሆኑም የክልሉ ሕዝብ በተቻለው አቅም ሰብአዊ ትብብር ከማቅረብ ወደ ኋላ የማይል ነው።

ስደተኞቹ በሊቢያ ቆይታቸው የሚያጋጥማቸው ችግርና መከራ እሥራትና ግርፋት ሁሉ ከስደተኛው አንደበት ስትሰማው በእውነቱ ለማመን የሚያዳግትና እንዴት ሰው ለሰው ይኸን ያክል ይጨክናል ብሎ እራስን ከመጠየቅና ስደተኞች በሚገቡባቸው አገሮች ለሚገኙት መንግሥታት ይኸንን ጉዳይ ማስረዳቱ በእውነቱ ክባድ ነው። ስደተኞችን ማዳመጥ ይበጃል። ስለዚህ ስደተኞች ወደ መጡበት መሸኘት መልሶ ለስቃይና መከራ ማጋለጥና ስደተኞችን በሕገ ወጥ መንገድ ከቦታ ቦታ ለሚያንቀሳቅት የወንጀል ቡድኖች መልሶ ማስረከብና ለእነዚህ ወንጀለኞች በገንዘብ ሃብት ማደለብ ይሆናል። በመሆኑም የኤውሮጳ መንግሥታት በፖለቲካው እቅዳቸው ቅድሚያ መስጠት የሚገባቸው ነገር ቢኖር በዓለም ሰላምና መረጋጋት ማስፋፋትና ፖለቲካውም ሆነ ኤኮኖሚው ቅዱስ አባታችን ደጋግመው እንደሚሉት ሰብአዊነት ያማከለ ማድረግ ይጠበቅባቸዋ። ካልሆነ የስደተኛው ጸአት ከሚጠይቀው ወጪ አንጻር ብቻ በመመልከት ወደ መጡበት ይሸኙ የሚለው አነጋገር ለገዛ እራሱ ኢሰብአዊነትን ማስፋፋት ይሆናል ብሏል።።

የሰው ሕይወት አድን ማኅበራት በመርከቦቻቸው በኢጣሊያ የባህር ኃይል ድጋፍ እነዚህ ስደተኞች በመዲትራኒያን ባህር በማዕበልና በነፋስ ሲወቁና ፈጥኖ ደረሶ ከሞትና አደጋ እንዲተርፉ ይደረጋል ብዙዎችም የመዳን እድል ሳያገኙ ባህር የሚውጣቸው ስደተኞች ብዙ ናቸው ስለዚህ የባህር ድንበር ጸጥታና ደህንነት ጥበቃ በሚል መርሃ ግብር የኤውሮጳ የባህር ኃይሎች ትብብር ጥበቃ በማረጋገጥ ስደተኛው ወደ መጣበት መሸኘት የሚለው አነጋገር በእውነቱ የሞት አደጋ ከፍ የሚያደርግ እንጂ መፍትሔ አይሆንም ስለዚህ ድንበርንና ጠረፍን ከመንከባከብ ይልቅ ሰውን መንከባከብ ብቻ ነው መፍትሔው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.