2017-03-29 15:53:00

ሐዋሪያው ጳውሎስ አብርሃም የእምነት አባት ብቻ ሳይሆን የተስፋ አባት እንደሆነም ጭምር ያስተምረናል።


ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 20/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው “የክርስቲያን ተስፋ” በሚል አርእስት የሚይስተላልፉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ለመከታተል ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎንኝዎች ያደረጉት አስተምህሮ ክርስቲያኖች ሁል ጊዜም ቢሆን ተስፋቸውን በእግዚኣብሔር ቃል ላይ ማድረግ እንደ ሚገባቸው የሚያመለክት እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን አንድ አንድ ጊዜም በሰውኛ አገላለጽ “ተስፋ ማድረግ” በሚያዳግተን ጊዜያት ሁሉ በርሱ ቃል ተስፋ ማድረግ ይገባናል ማለታቸው ተገለጸ።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ያስተላለፉትን የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ሚከተለው አጠር ባለ መልኩ ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ! እንደምን አረፈዳችሁ

ዛሬ ሲነበብ በሰማነው ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ (4: 17-) ትልቅ ስጦታን ያቀርብልናል። በእርግጥ አብርሃም የእምነት አባታችን መሆኑን የምናውቀውና የለመድነው እውነታ ቢሆንም   ዛሬ ግን ሐዋሪያው ጳውሎስ፣ እኛ አብርሃም የተስፋ አባት እንደሆነ እንድንረዳ ያደርገናል። የእምነት አባት ብቻ ሳይሆን የተስፋ አባትነቱንም እንድንረዳ ያደርገናል።

የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደ ሚነግረን አብርሃም ያመነውየሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርግው አምላክ” (ሮሜ 4:17) ነው ያመነው። በአጭሩምበሥጋው መድከም ምክንያት መወልደ እንደ ማይችልና ሣራም መኻንና ያረጀች በመሆኑዋ መውለድ የማትችል መሆኑዋን ቢያውቅም በእምነቱ ግን ደካማ አልሆነም” (ሮም 4:19) አዎን! እኛም ይህንን ልምድ በመቅሰም በዚህ መልኩ እንድንኖር ተጠርተናል። ለአብርሃም የተገለጸው እግዚኣብሔር የሚያድን አምላክ፣ ተስፋ ከመቁረጥ የሚያወጣን ከሞትም የሚያድነን አምላክ ነው፣ ወደ ሕይወት የሚጠራን አምላክ። ይህም ነገር ዛሬ እኛ እንደ ምናውቀው እና እንደ ምናከብረው ይህ ነገር በፋሲካ ምስጢር ምልአትን አግኝቱዋል።

በእርግጥ ቅግዚኣብሔርኢየሱስን ከሞት አስነስቶታል” (ሮም 4:24) ምክንያቱም እኛም በክርስቶስ አማካይነት ከሞት ወደ ሕይወት እንሻገራለን። ስለዚህም በእውነት እኛ አብርሃምንየብዙ ሰዎች አባትብለን አፋችንን ሞልተን መናገር እንችላለን ምክንያቱም እርሱ አዲስ ፍጥረት ለሆንን ለእኛ ይህንን መልእክት ስለ ሚያስተጋብል ነው። ከኃጢያት እና ከሞት በክርስቶስ ተዋጀን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜም በእግዚኣብሔር ፍቅር እንድንታቀፍ አደረገን።

በዚህም አኳያ ሐዋሪያው ጳሎስ በእምነት እና በተስፋ መካከል ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት እንዳለ አሳይቶናል። እርሱምአብርሃም ያመነው እና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ ባልነበረበት ወቅት ነው” (ሮም 4:18) በማለት ይህንን እውነታ ያረጋግጥልናል። የኛ ተስፋ በምክንያት ላይ፣ አርቆ በማየት ላይ እና በሰው ልጅ እርግጠኛነት ላይ የተመረኮዘ አይደለም፣ ምንም ተስፋ በሌለበት፣ ምንም ዓይነት ነገር ተስፋ ማድረግ በማንችልበት ደረጃ ላይ ባለንበት ወቅት፣ ልክ አብርሃም በነበረበት ሁኔታ ውስጥ በምንሆንበት ወቅት ሁሉ ልናጸባረቅው የሚገባው ዓይነት ተስፋ ነው ሊኖረን የሚገባ።

አብርሃም እና ሣራ  በሕይወታቸው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ነበሩ፣ ልጅም አልነበራቸውም በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥም ቢሆን አብርሃም አመነ ተስፋ ባልነበረበት ወቅት ተስፋ አደረገ፣ ይህም ታላቅ የሆነ ነገር ነው።  ታላቅ የሆነ ተስፋ ሥር መሰረቱን ያደረገው በእምነት ላይ ነው፡ በዚህም መነገድ ብቻ ነው ተስፋ በለለበት ቦታ ተስፋ ማድረግ የምቻለው። አዎን! በራሳችን ቃል ላይ ተመርኩዘን ሳይሆን በእግዚኣብሔር ቃል ላይ ተመረኩዘን የምናደርገው ነገር ሊሆን ይገባል።

እኛ በዚህ ረገድ የአብርሃምን ምሳሌ እንድንከተልና ምንም እንኳን ባዶነትና በሞት አፋፍ ላይ እንደሆን በሚሰማን ወቅቶች ሁሉ ሳይቀርእግዚኣብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደ ሚፈጽም” (ሮም 4:21) ማመን ይጠበቅብናል።

አንድ ጥያቄ ባቀርብላችሁ ደስ ይለኛል። እግዚኣብሔር ሁላችንንም በመልካም ሁኔታ ውስጥ እንድንሆን እንደ ምፈልግ እና ተሰፋ የሰጠንን ነገሮች ሁሉ ወደ ምልአት እንደ ሚያደርስ እርግጠኞች ነን ወይ? ይህ የእግዚኣብሔር ኃይል ልባችሁ ውስጥ ይገባ ዘንድ ልባችሁን የእግዚኣብሔርን ምሕረትን እና ተስፋ ለምያስተምራችሁ መንፈስ ልባችሁን ክፈቱ ልባችሁን ለእግዚኣብሔር እምነት ክፍት አድርጉ ቀሪውን ነገር እርሱ ያከናውነዋል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!

በዛሬው እለት እግዚኣብሔር አባታችንን በራሳችን ኃይል እና ችሎታ ላይ በመተማመን ሳይሆን፣ ነገር ግን እግዚኣብሔር ቃል ከገባልን በሚመነጨው ተስፋ ተማምነን ትክክለኛ የአብርሃም ልጆች የምያደርገንን ፀጋ ይሰጠን ዘንድ እንለምነው። እግዚኣብሔር አንድ ጊዜ ቃል የገባውን ነገር ከፍጻሜ ያደርሰዋል። ቃል ከገባልን ነገር አንድ ቃል እንኳን ሳይፈጸም አያልፍም። እዚህ ዛሬ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰብነው ሁላችን የተከፈተ ልብ ካለን አንድ ቀን ሁላችን ዘላለማዊ በሆነው በሰማይ ቤታችን በሚገኘው ሥፍራ መገናኘት እንደ ምንችል ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ይህም እግዚኣብሔር ቃል የገባልን ነገር ነው። ልባችንን ከከፈትን ይህ የእኛ ተስፋ ነው። እግዚኣብሔር ይስጥልኝ!

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ይህ ቀደም ሲል ስትከታተሉት የነበራችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች  “የክርስቲያን ተስፋ” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያስተላለፉትን አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን ነበር።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.