2017-03-21 09:11:00

ሰባቱ ሥጋዊ/አካላዊ የምሕረት ተግባራት


ሥጋዊ/አካላዊ የምሕረት ተግባራት

የምሕረት ሥራዎች ማለት መንፈሳዊ እና ሥጋዊ/አካላዊ ለደረሱበት ባልንጀራችን የምንፈጽማቸው የፍቅር ሥራዎች ናቸው። አካላዊ የምሕረት ተግባራት የሚባሉት የሰው ልጆች ለሕያወታቸው ሕልውና የሚጠቀሙባቸው ቁሳዊ ነገሮችን ይመለከታል (የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ.2447)። ሥጋዊ/አካላዊ የምሕረት ተግባራት መሰረታቸውን ያደረጉት በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25: 31 ጀምሮ በጠጠቀሰው የኢየሱስ አስተምህሮ ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ይህም በዓለም መጨረሻ የሚሆነውን የፍርድ ሂደት የሚያመልክትና “ኢየሱስ በመላእክቱ ታጅቦ በፍርድ ወንበር ላይ በመቀመጥ፣ እረኛው በጎችን ከፍዬሎች  እንደሚለይ እርሱም ሕዝቦችን ይለያል፣ በጎቹን በቀኙ ፍዬሎቹን ደግሞ በግራው ያቆማቸዋል” እንደ ሚል በመጨረሻው ቀን በኢየሱስ ፊት በምንቆምበት ወቅት ለሚያቀርብልን ጥያቄዎች በድፍረት በቂ የሆነ ምላሽ መስጠት እንድንችል እና ከፍየሎቹ ተርታ ሳይሆን ከገበጎቹ ጎራ መሰለፍ እድንችል የሚያግዙን ተግባራትን መፈጸም ይገባል። በተለይም በዚህ በዓብይ ጾም ወቅት ለየት ባለ ሁኔታ አካልዊ የምሕረት ተግባራትን በተግባር ማሳየት ያስፈልጋል።

ሰባቱ ሥጋዊ/አካላዊ የምሕረት ተግባራት የሚከተሉት ናቸው።

  1. የተራበን ማብላት

     2. የተጠማን ማጠጣት

    3. የታረዘን ማልበስ

   4. መጠለያ የሌላቸውን ሰዎች ማስጠለል

  5. ሕሙማንን መጎብኘት

  6. የታሰረን መጎብኘት

  7. ሙታንን መቅበር








All the contents on this site are copyrighted ©.