2017-03-19 11:37:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጪው ሚያዝያ 20 እና 21/2009 ዓ.ም ግብፅን እንደ ሚጎበኙ ተገለጸ።


ከቅድስት መንበር የሕትመት እና የዜና ክፍል በመጋቢት 9/2009 ዓ.ም የወጣው ዜና እንደ ሚያመልክተው በመጭው ሚያዝያ 20 እና 21/2009 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይፋዊ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለመድረግ ወደ ግብፅ እንደ ሚጉዋዙ ተገለጸ።

ከቅድስት መንበር የሕትመት እና የዜና ክፍል ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ግሬግ ቡሬክ ቅዳሜ እለት በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳሳወቁት “ቅዱስነታቸው በግብፅ ሪፖብሊክ ፓሬዚዳንት እና በግብፅ ሀገር ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፣ በተጨማሪም በግብፁ የኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ከሆኑት ቴዎድሮስ ሁለተኛ እና በግብፅ የታላቁ የአል ዓዛር መስጊዲ ኢማም በሆኑት ሼክ አህመድ ሞሃመድ ሌል- ታይብ በጋራ ባቀረቡላቸው የጉብኝት ግብዛ መሰረት ቅዱስነታቸው ወደ እዚያው እንደ ሚጉዋዙ ኃላፊው ጨምረው ገልጸው የዚህ ጉብኝት መርዓ ግብር በቅርቡ ይፋ እንደ ሚሆንም ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.