2017-03-17 16:44:00

ብፁዕ ካርዲናል አማቶ፥ ለሂትለር ሥርዓት እምቢ ያሉት የእምነት ሰማዕት ማይር ኑሰር የብፅዕና አዋጅ


እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ 10 ሰዓት በኢጣሊያ ቦልዛኖ ከተማ በሚገኘው ካቴድራል የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወክለው በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. በ 1945 ዓ.ም. በናዚው ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት የደም ሰማዕትነት የተቀበሉትን የእምነት ሰማዕት ዓለማዊ ምእመን ለእግዚኣብሔር አገልጋይ ሰማዕት ጁዘፐ ማይር ኑሰር ብፅዕናን እንድሚያውጁ የቅዱስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ከሰጠው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።

ለናዚው የሂትለር ሥርዓት እገዛለሁ የዚያ ሥርዓት ርእዮተ ዓለም እንደግፋለሁ ብሎ ቃለ መሓላ እንዲፈጽም ተጠይቆ እምነትና ታማኝነት ለክርስቶስ ብቻ ነው በማለቱ ምክንያት የደም ሰማዕትነት የተቀበለው የእግዚአብሔር አገልጋይ ጁዘፐ ማይር ኑሰር እ.ኤ.አ. በ1910 ዓ.ም. በኢጣሊያ ቦልዛኖ አውራጃ የተወለደ ገና ወጣት እያለም እምነትን በግልና በማኅበረ ክርስቲያን ውስጥ በመኖር በግብረ ሰናይ እየተረጎመ ለድኾች ቅርብ በመሆን ክርስቶስን ያበሰረ መሆኑ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ የሰጡት መግለጫ የጠቀውሰው የቅድስ መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ለእውነት ያለን ፍቅር ለህሊናችን ታዛዝነታችንን የቤተሰብ ክቡር እሴትን ድኾችን በልዩ ማፍቀርን የወጣት ትውልድ ሕንጸት ለወንጌል በነበረው ፍቅር ምክንያት አቅቦ የኖረ ለቤተ ክርስትያንና ለማኅበረ ክርስቲያን እግዚአብሔር የለገሰው ወንጌላዊ ሕይወት መኖር ተቻይ መሆኑ ያረጋገጠ ጸጋ ነው እንዳሉ ይጠቁማል።

አዲስ ብፁዕ ጁዜፐ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከዚህ ቀደምም ብፅዕነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ክርስትያን እንደ ክርስቶስ በሁሉም የሕይወት ደረጃና ሁነት የምድር እርሾና ጨው ሆኖ እንዲገኝ የተጠራ ነው በማለት ሰጥተዉት የነበረው ምዕዳን ያንን የብዙ ማኅበረ ክርስቲያን ስቃይ ስደት መከራ የሚያስታውስና አሁንም ጨውና እርሾ ሆነው በመገኘታቸው ምክንያት ለስቃይና ለመከራ ለሞት የሚዳረጉትን የሚያስታውስ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ አብራርተው እነዚህ ወንድሞች ካልአ ኢየሱስ ክርስቶስ ናቸው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመለክታል።

እ.ኤ.አ. በ 1934 ዓ.ም. ገና በ 24 ዓመት እድሜው በኢጣሊያ ትሬንቶ ክፍለ ሃገር የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ሊቀ መንበር ሆኖ መመረጡና በ 1939 ዓ.ም. በቦልዛኖ ለተቋቋመው የቅዱስ ቪንቸንዞ አዲስ ጉባኤ ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገለ ዘወትር በመሥዋዕተ ቅዳሴ ተሳታፊ ጸሎት መቁጸሪያ በየዕለቱ ደጋሚ ድኾችን በማገልገልና በሚተዳደርበትንም ሥራ በቃልና በሕይወት ክርስትናን ወይንም የክርስቶስ ተከታይነትን አለ ፈረቃ የመሰከረ እ.ኤ.አ. በ 1942 ዓ.ም. ሂልደጋርድን አግብቶ የአንድ ልጅ አባላት ለመሆን የበቃ የናዚው ጦር አባል እንዲሆንና ለሂትለርና በሂትለር ይመራ ለነበረው ለብሔራዊሶሻሊዝም ርእዮተ ዓለም የታማኝነት ቃለ መሓላ እንዲፈጽም የቀረበለትን ጥያቄ እምቢ እኔ የክርስቶስ ነኝ በማለት በመቃወሙ ምክንያት የደም ሰማዕትነትን የተቀበለ የክርስትና ሕይወት አብነት መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ የሰጡት ማብራሪያ የጠቀሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አያይዞ፥

ጁዘፐ ማይር ኑሰር በቦልዛኖ ክልል ነዋሪ የእናት ቋንቋውም ጀርመንኛ በመሆኑ በ 1944 ዓ.ም. ወደ ፖላንድ እንዲሄድ ጥሪ ተደርጎለት በኰኒዝ እንደደረሰም የናዚ አባል እንዲሆን ሲጠየቅ እምነቴ የሚቃወመው ተግባር ነውና አባል እንድሆን አልፈቅድም ለዚህ ርእዮተ ዓለም ታዛዥ አልሆንም በማለት የተገደለ፡ በሕይወቱ እያለ ከቅዱስ መጽሐፍ በተጨማሪ የቅዱስ ቶማስ ሞር መንፈሳዊ ድርሳናትን በጥለቅት ያነበቡና ጠንቅቀው የሚያውቁ የሮማኖ ጉዋርዲኒን ድርሰቶችን የቅዱስ ቶማስ ሞር ለእንግልጣር መራሔ መንግሥት በወህኒ ቤት እያለ የጻፈው መልእክት ‘የካቶሊክ የማንነት መለያው ምክንያት ለዚያች አገር ንጉሣዊ ሥልጣን አልገዛም ብያለሁ’ የሚል ያሰመረበትን ሃሳብ የሕይወቱ መርህ በማድረግ የተመሳሳይ ዕጣ ዕድል ተቋደሽ የሆነ ለህሊና መገዛትን  የመረጠ፡ ይኽ ምርጫው ደግሞ ካልአ ኢየሱስ እንዲሆን አደርገው”

እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ለናዚው ሥርዓት አልታዘዝም በማለቱ ምክንያት ወደ ዳጋው የእልቂትና የመቅሰፍት ወህኒ እየተወሰደ እያለ በጉዞው በናዚ ወታደሮች ይደርስበት በነበርው ስቃይና መግረፍት ለሞት መዳረጉና ይደስርበት የነበረው ስቃይ ሁሉ በትዕግስት ስለ ክርስቶስ የተቀበለው የሰማዕት ጁዜፐ የታርክ ማህደር የጠቀሰው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ በዚያኑ ወቅት ወደ ዳካው የመቅሰፍት ሰፈረ ለማድረስ ይሸኝዋቸው ከነበሩት የጀርመን ወታደሮች ውስጥ አንዱ ከብዙ ዓመታት በኋላ ያንን የ 14 ቀን ጉዞው በትውስት ሲገልጥ ካንድ ቅዱስ ጋር አብሬ ተጓዝኩ ሲል መናገሩና ይኽ ምስክርነት በቤተ ክርስቲያን የታሪክ ማኅደር የሰፈረ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል አማቶ በሰጡትን ማብራሪያ ጠቅሰው የዚህ አዲስ ብፁዕ ጁዜፐ ማይር ጁሰር በላቲን ሥርዓት ባሕረ ሐሳብ መሠረት የሰማዕትነት ክብረ በዓሉ ጥቅምት 3 ቀን ይውላል እንዳሉ አስታውቋል።

“ከአዲስ ብፁዕ የእምነት ብርታት ለወንጌል ታማኝነት ለሕሊና ታዛዥነትን እንማራለን፡ ክርስቲያን ክርስቶስን የሚያበስር ነውና ሁሉም እንደየ ጥሪው ክርስቶስን እንዲኖር ተጠርተዋል። የዓለም በሽታ የሚፈውስ ወንጌል ነው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉት የወንጌል ሃሴት መኖር ይጠበቅብናል። ክርስትና ሕይወት እንጂ ሞት እይደለም። ይኽ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን መስለው የኖሩት ቅዱሳን ሰማዕታት የእምነት አበው ያረጋግጥሉናል”

በሚል ቅዉም ሃሳብ ብፁዕነታቸ የአዲሱ የቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ጁዜፕ አማካለው የሰጡት መግለጫ አንዳጠቃለሉ  የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.