2017-03-15 15:29:00

ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ያስተላለፉት አስተምህሮ “ተስፋ በማድረጋችሁ ደስ ይበላችሁ” በሚል ጭብጥ ዙሪያ እንደ ነበረ ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ቀጣይነት ባለው መልኩ በሣምንት ሁልት ጊዜ ዘወትር ርዕብና እሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች የጠቅላላ አስተምህሮን እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚህ ልማዳዊ የጠቅላላ አስተምህሮዋቸው አንዱ ክፍል በሆነው በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 6/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያስተላለፉት አስተምህሮ ከእዚህ በፊት “የክርስቲያን ተስፋ” በሚል አርዕስት ስያካሂዱት የነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበር የታወቀ ሲሆን “ተስፋ በማድረጋችሁ ደስ ይበላችሁ” በሚል አርዕስት በዛሬው እለት ያደርገት አስተምህሮ ቅዱስ ሐዋሪያ ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ 12:9-13 ላይ የተመረኮዘ አስተምህሮ እንደ ነበረም ለመረዳት ትችልዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!! 

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንተዳደርበት ዘንድ፣ በሕይወታችንም ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ ትእዛዛትን  ስጥቶናል እነዚህም “እግዚኣብሔርን አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነብስህ እና በሙሉ ሐሳብህ ውደድ የሚለው እና ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ የሚሉት በማቴዎስ 22:37-39 የተጠቀሱት መሆናቸውን አውስተው እነዚህ የፍቅር ሕግጋት በሕይወታችን በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቅሰው ስለዚህም እንድንዋደድ ተጠርተናል፣ ለክርስቲያኖች ከሁሉም በላይ መተዳደሪያ ሕጋቸው ይሆን ዘንድ እግዚኣብሔር የሰጠን “የፍቅር” ሕግ ነው ብለዋል።

“በፍቅር ሕግ የሚተዳደር ሰው ሁሉ በሕይወቱ ትልቅ የሆነ ደስታ ይኖረዋል፣ ከእዚህ ደስታ እና ይህን ደስታ ተከትሎ በሚመጣው ተስፋ ተሞልተን እግዚኣብሔርን መገናኘት ይችላል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ “ግብዝነት የሌለው እውነተኛ ፍቅር ይኑራችሁ” ብሎ እንደ መከረን ሁሉ እኛም ግብዝነት በሌለው ፍቅር እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ያስፈልጋል ብለዋል።

ታዲያ በሕይወታችን ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ የግብዝነት ፍቅር መኖር አለመኖርንና ፍቅራችን እውነተኛ መሆን አለመሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? በማለት ጥያቄን በማንሳት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሌሎች ሰዎችን የምንወደው የግል ፋልጎቶቻችንን እና ጥቅሞቻችንን ለማሳከት ፈልገን ብቻ ከሆነ ፍቅራችን በግብዝነት የተሞላ ነው ማለት ይቻላል ነገር ግን እውነተኛ ፍቅር ሁሌም የእግዚኣብሔር የፀጋ ስጦታ ነው ፣ ይህንንም የፍቅር ስጦታ ተገቢና እውነተኛ በሆነ መልኩ በተግባር ለማሳየት በቅድሚያ በምሕረትና በትሕትና የተሞላውን የእግዚኣብሔርን ፊት በቀዳሚነት መመልከት ያስፈልጋል ብለዋል።

ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ “በክርስቶስ ወንድማማቾች እንደ መሆናችሁ መጠን እርስ በእርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፣ ክፉን ነገር ጥሉ መልካምን ነገር ሁሉ ተከተሉ” በማለት ለሁላችን ጥሪ ያቀርብልናል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንም ጥሪ ተከትለን የእግዚኣብሔር ፍቅር መገለጫዎች መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል።

ይህንንም ጥሪ በተግባር ላይ ለማዋል በቅድሚያ እግዚኣብሔር ልባችንን እንዲፈውስ እና እንዲያድሰው መፈቀድ ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው በመካከላችን የሚኖረው ከሙታን የተነሳው አምላክ ልባችንን የመፈወስ እና የማደስ ብቃት ስላለው ይህንን ፈውስ ይሰጠን ዘንድ ልንማጸነው ይገባል፣ ድክመታችንን እና ውድቀታችንን የሚገነዘበው እግዚኣብሔር በምሕረቱ ይጎበኘናል ብለዋል።

እኛ እንደ አቅማችን ለወንድም እህቶቻችን የምናሳየው ፍቅር እና የምናደርገው ይቅርታ እግዚኣብሔር ለእኛ ከሚሰጠን ፍቅር እና ከሚያደርግልን ይቅርታ ጋር በፍጹም ሊነጻጸር አይችልም ያሉት ቅዱስነታቸው ሰዎችን በምንወድበት እና ይቅር በምንልባቸው ወቅቶች ሁሉ እግዚኣብሔርም እኛን ይቅር ይላል በእኛ ውስጥ ማደሩኑም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በአተምህሮዋቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት “የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ሐዋሪያው ጳውሎስ  ‘ተስፋ በማድረጋችሁ ደስ ይበላችሁ’ ብሎ በማንኛውም ሁኔታ በተስፋ የሚገኘው ደስታ በውድቀታችንም ጊዜ ቢሆን የእግዚኣብሔር ፍቅር እንደ ማይቀንስ እርግጠኞች እንድንሆን ያደርጋል ፣ ስለዚህም በእርሱ ፍቅር የተሞላ ልብ ይዘን በእርሱ ፍቅር ታምነን በእዚህ አስደሳች በሆነው ተስፋ ተስፋ በማድረግ በሚገኘው ደስታ ተሞልተን ይህንን ደስታ ደግሞ ለእህት ወንድሞቻችን ማካፈል የምንችልበትን ፀጋ እንዲሰጠን የእርሱን ፀጋ መጠየቅ ያስፈልጋል” ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.