2017-03-15 16:43:00

ቀዳሜ ስብከት ዘዓቢይ ጾም፥ አባ ካንታለመሳ ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ዕለት በዕለት ማደስ


የካፑቺን ንኡሳን አኃው ማኅበር አባል ሰባኬ ቤተ ጳጳስ አባ ራኒየሮ ካንታላመሳ እ.ኤ.አ. መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና መላ የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጳጳሳዊ አቢያተ ምክር እንዲሁም ቅዱሳን ማኅበራት ሊቀ መናብርትን ኅየንተዎችን ያሳተፈው በሐዋርያዊ መንበር በሚገኘው እመ መድኃኔ ዓለም ቤተ ጸሎት የዓቢይ ጾም ቀዳሜ ስብከት ማቅረባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ገለጡ።

ክቡር አባ ካንታልመሳ በዘመነ ምጽአት መንፈስ ቅዱስ ዙሪያ የጀመሩት አስተንትኖ በመቀጠል በዚህ ቀዳሜ የዓቢይ ጾም ስብከታቸው በኒቅያ ጉባኤ ውሳኔ ዘንድ በሁለተኛ ዓንቀጽ፥ “መንፈስ ቅዱስ የብቸኛው ጌታ የማዳን ተግባራቱን የሚገልጥ እውነት ላይ ግንዛቤው እንዲኖረን ይመራናል” ሲል ያስፈረው ሃሳብ ላይ ተንተርሰው በመንፈስ ቅዱስና ክርስቶስን በማወቅ መካከል ያለው ግኑኝነት ከሐዋርያት ታሪክ በመንደርደርና ቲዮሎጊያ በታሪክ የሰጠበት ጥልቅ ጥናት ሲተነትኑ፡ ገና ከጥንት ጀምሮ በጳውሎስና በየውሐንስ የሚገለጡት ሁለት ዓይነት ግንዛቤዎች እነደበነበሩ ጠቅሰው። አንደኛው ጠመቃዊ (ዶግማዊ-የማይሻርና የማይለወጥ ትምህርተ ኃይማኖት) ማለትም በክርቶስ ገዛ እራስ መሆን ላይ የጸና ክርስቶስ በገዛ እራሱ ለገዛ እራሱ መሆን የሚል መሆኑና ሁለተኛው ግንዛቤ ደግሞ ውስጣዊና ግላዊ እርሱም ክርስቶስ ባደረገልኝ ነገሮች አማካኝነት ማወቅ የሚል መሆኑ አብራርቷል።

የሉተራን ኅዳሴ ገና ከመወለዱ በፊት አንደኛው እርሱም ዶግማ ላይ የጸና ግንዛቤ አቢይ ጫና የነበረው ሲሆን፡ ከሉተራናዊ ኅዳሴ ክስተት በኋላ ክርስቶስ ለእኔ ባደረገልኝ አማካኝነት አውቀዋለሁ የሚለው ግንዛቤ ተስፋፍቶ መጥቷል። በዚህ ዓይነት ሂደት ውስጥ እየተኖረ አዕምሮአዊ ክስተት ያማከለ የብርሃን ዘመን እርሱም የአእምሮ ንቃት የሚከስተው የማወቅ ብርሃን ተብሎ ወደ ሚጠራው ባህል ተደረሰ። ይኽ ደግሞ ያንን ክርስቶስን ለማወቅ ካደረገልኝ ነገር መንደርደር የሚለውን አስተሳሰብ ወደ ጎን እንዲል በማድረግ፡ አቢይ ግምት ይሰጠው ወደ ነበረው ጥንታዊ አመለካከት እርሱም ሥነ ህልውና የሚል ሳይሆን የሥነ ህልውና ታሪክ ላይ የጸና የማወቅ ደረጃ በስፋት ተቀባይነት እያገኘ መጣ። እንግዲ እኛ የዚህ ሁሉ ባህል ድምርና ውጤቶች ነን ያሉት አባ ካንታላመሳ አያይዘው፥ ስለዚህ ክርስቶስ በገዛ እራሱ ስለ ገዛ እራሱ በሚገልጠው ማንነት ላይ ሳይሆን በተጨባጩ ታሪክ ኢየሱስ ማን ነበር በሚለው ታሪክ የሚገልጠው የክርስቶስ ማንነት ተቀባይነት ተሰጠው፡ በዚህ ዓይነት ክርስቶስ የማወቅ ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ተዘነጋ። መንፈስ ቅዱስ የተዘነጋውም በገዛ እራሱ ምክንያት ሳይሆን ክርስቶስ ማን መሆኑ ለማወቅ በሚጥረው አካል ነበር የተዘነጋው እንዳሉ ማሶቲ ገልጧል።

የክርስቶስ ሥልጣን ማወቅ የመንፈስ ቅዱስ ተግባር ነው

የክርስቶስን ሥልጣን ማወቅ፡ እውቅና መስጠት ወደ መንፈስ ቅዱስ ተግባራት መግባት ማለት ይሆናል። ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ከሚፈጥረው ታሪክ እና ኢየሱስ ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነጥሎ በታሪክ ውስጥ በማኖር በታሪክ የሚነገረው በጊዜና በቦታ ውስጥ የተካተተውን ኢየሱስን ማወቅ የሚለው ሰፊ ተቀባይነት አያገኘ መጣ። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በሰው መንፈስ ተተካ፡ ማለትም መንፈስ ቅዱስ የሚገልጠው የኢየሱስ ማንነት ሳይሆን እኔ ከታሪክ የሚገነዘበው የኢየሱስ ማንንት ላይ ተተኰረ። ባንጻሩ ይኽ ዓይነቱ ባህል መንፈስ ቅዱስን በልዩ መንፈስ የማጥናት ፍላጎት በእጅጉ አነቃቃ ከዚህ በመንደርደርም የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴዎች ተነቃቁ። “ከዚህ አዲስ መንፈሳዊና ቲዮሎጊያዊ ሁነት ውስጥ ስለ ኢየሱስ ምን ዓይነት እወቅትናና ምን ዓይነት ማወቅ ይፈልቃል?” እዚህ ላይ እጅግ አስፈላጊነት ያለው ጉዳይ ያንን በዚያ ዘመን የነበረው ፍልስፍና ያመጣው የአዳዲስ ተስፋ ወይንም የአዳዲስ ሥልቶች ግኝት ሳይሆን ያ ተራ የሆነው መጽሓፍ ቅዱስ የሚገልጠው ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው መለያ ዳግም ማግኘት ይሆናል። “ኢየሱስ ጌታ ነው! ወደ ሚለው አዲስ ሁነት ወደ ሆነው ሥልጣነ ክርስቶስ የሚገባው በመንፍስ ቅዱስ ሥራ ብቻ ነው” ቅዱስ ጳውሎስ ይኸንን አዲስ ክርቶስን የማወቁ ሂደት የላቀ እወቅት በማለት ብቻ ሳይሆን ልዑል እወቅት ሲል ገልጦታል። ይኽ የክርስቶስ ሥልጣን ማወቅ ክርስቶስ ጌታ ነው ብሎ መናዘዝና ማወጅ ላይ የጸና እውቀት ነው፡ ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው ኑዛዜና እወጃም በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ ካለህ እምነት ጋር የተጣመረ ነው፡ ይኽ ደግሞ የዳነ ሰው የሚያደርግ እምነት ነው።

“በከንፍፈሮችህ ኢየሱስ ጌታ ነው ብለህ የምታውጅ ከሆንክ በልብህ እግዚአብሔር ከሙታን እንዳስነሣው ታምናለህ ማለት ነው። ስለዚህ ትድናለህ፡ የዚያ ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው ቃል ያለው የገዛ እራሱ ኃይል በታሪክ ምሥጢረ ፋሲካን የሚያበራ ነው። ክርስቶስ ስለ እኛ ኃጢኣት ሞተ፡ ጻድቃን ወይንም ብፁዓን (justify) ሊያደርገንም ዘንድ ጌታ ነው፡ የሚያጸድቀን ብፁዓን የሚያደርገን ጌትነቱ ነው።”         

ያ ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው እምነታችንና እወጃችን ቆራጥ ውሳኔ የሚጠይቅ ግብረ እምነት ነው፡ ያ የምናዘዘውና የማውጀው ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው ግብረ እምነት የሕይወት ትርጉም ይወስናል። ይኽ ማለት ደግሞ፥

”አንተ ጌታ ነህ፡ አለ ምንም ጫናና ግፊት በነጻነት እገዛልኃለሁ፡ አዳኜ ነህ። ጌታ ነህ ስንል መሪዬ መምህሬና በእኔ ላይ ሁሉም ዓይነት ነጻነትና መብት ያለህ ነኽ ማለት ነው። እኔ የገዛ እራሴ ከመሆኔ በፊትና ከዛም ልቆ የአንተ ነኝ ማለት ነው፡ ምክንያቱም  ወደር በማይገኝለት ዋጋ ተበጅተኸኛል ገዝተኸኛልና። ብዙዎች በሃይማኖቶች መካከል ለሚደረገው የጋራው ውይይት ለመደገፍ በሚል ምክንያት የክርስቶስ ብቸኛነት የሆነውን መሠረተ ሃሳብ ለማገግለል ይቻላል አሊያም ማግለሉ ተገቢ ነው ብለው የሚያምኑ አሉ። ሆኖም ግን ኢየሱስ ጌታ ነው ብለህ መናዘዝና ማወጅ ሲባል የክርስቶስ ልዩ መሆንና ብቸኛ ጌትነቱን ካለ ማግለል መናዘዝና ማበሰር ማለት ነው።”

ከኢየሱስ ጋር ያለህን ግኑኝነት ማደስና ካለ ማቋረጥ እርሱን መፈለግ

ኢየሱስ አዳኝ መሆኑ ማወቅ አዳኝነቱን ማግኘት ይላሉ አባ ካንታላመሳ በዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ስቃይ የእግዚኣብሔ ህዳሴና ጸጋ ነው።

“ኢየሱስን በማወቅ ላይ የሚጸናው ዓይነተኛው እድገታችን መንፈስ ቅዱስ እምን ላይ ያጸናው ሕዳሴ ነው? ክርስቶስ ጌታ ነው የሚል ኑዛዜአችንና እወጃችን ኢየሱስ ተነስተዋል ህያው ነው ለሚለው ግንዛቤ በሚያበቃን ሁነት ላይ የጸና ነው። ኢየሱስ እንደ አንድ ሰው ወይንም ሰውና የተለያዩ የእምነት መሠረተ ሃሳብ ስብስብ ሳይሆን የስግደትና የዝክረ ርቱዕ ተሳቢ (ስድገት የሚደረግለትና የሚዘከር ነገር) ሳይሆን የሊጡርጊያና የቅዱስ ቁርባን ርቱዕ ተሳቢ ቢሆንም በመንፈስ ቅዱስ ህያውና ህልው የሆነ አካል ነው።”

ያሉት አባ ካንታላመሳ ያቀረቡትን ስብከት፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “Evangelii gaudium-ወንጌላዊ ሓሴት” በተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳናቸው ዘንድ፥ “በማንኛውም ሥፍራና ሁነት የሚገኘው እያንዳንዱ ክርስትያን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲያድስ ወይንም ደግሞ በእርሱ (በኢየሱስ ክርስቶስ) ለመገኘት እንዲፈቅድና ካለ ማቋረጥ እርሱን እንዲፈልግ እመክራለሁ። ማንም ይኸንን ጥሪ አይመለከተኝም ለማለት የሚያበቃው ምክንያት ማሰብ አይቻልም አይቻለውም” በማለት ያሰመሩበትን ሃሳብ ጠቅሰው ማጠቃለላቸው ማሶቲ አስታውቋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.