2017-03-09 08:34:00

የጾም ወቅት የዓለምን ክፋት ከሕይወታችን በንስሓ የምናስወግድበት ወቅት ነው።


ዐብይ ጾምን አስመልክተን በተከታታይ ለእናንተ አድማጮቻችን የተለያዩ አስተምህሮዎችን በማቅረብ ላይ እንገኛለን። በዐብይ ጾም ወቅት ምዕመናን ከእግዚኣብሔርና ከእህት ወንድሞቻቸው ጋር የሚታረቁበት ወቅት ነው። በኃጢያታችን ምክንያት እግዚኣብሔርን፣ ራሳችንን፣ ወንድም እህቶቻችንና ተፈጥሮንም ሳይቀር በድለናል። ይህንን በደላችንን ደግሞ በእዚህ በዐብይ ጾም ወቅት ለየት ባለ ሁኔታ ሱባሄበማድረግና ንስሓ በመግባት ከእግዚኣብሔር ጋር መታረቅ ያስፈልጋል። በዛሬው እለት የክፍል 7 አስተምህሮዋችን በጾማችን ወቅት የዓለምን ክፉ ነገሮች ከሕይወታችን በንስሓ ሚስጢር በማስወገድ ወደ እግዚኣብሔር ልንመለስ ያስፈላጋል በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያዘጋጀንላችሁን አጭር አስተምህሮ እናቀርብላችኃለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የእዚህን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክፍል 7

የጾም ወቅት የዓለምን ክፋት ከሕይወታችን በንስሓ የምናስወግድበት ወቅት ነው።

“ስለዚህ ለእግዚኣብሔር ተገዙ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙት ከእናንተም ይሸሻል። ወደ እግዚኣብሔር ቅረቡ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል፣ እናንተ ኃጢያተኞች እጆቻችሁን አጽዱ፣ እናንተ ወላዋዮች ልባችሁን አጥሩ። ተጨነቁ፣ እዘኑ አልቅሱ፣ ሳቃችሁ ወደ ለቅሶ፣ ደስታችሁ ወደ ሐዘን ይለውጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ እርሱ ከፍ ያደርጋችኋል” (የያዕቆብ መልእክት 4:7-10)።

በዐብይ ጾም ወቅት ከማንኛውም ነብሳችንን ከሚያጎድፍና ሥጋችንን ከሚበድሉ ነገሮች ራሳችንን የምንጠብቅበት ወቅት ነው። ሐዋሪያው ያዕቆብ ከደም ሲል በሰማነው መልእክቱ ዲያቢሎስን ተቃውመን ለእግዚኣብሔር እንድንገዛ ይመክረናል። ለእግዚኣብሔር ለመገዛት ደግሞ ከማንኛውም ኃጢያት መንጻት ይኖርብናል ማለት ነው። ከኃጢያታችን የምንነጻው ደግሞ ተጸጽተን ንስሓ ስንገባ ብቻ ነው። ታዲያ ለእኛ ለካቶሊክ ምዕመናን ንስሓ ማለት ምን ማለት ነው? ብለን ልንጠይቅ እንችል ይሆናል ጥያቄውም ወቅታዊ እና ተገቢ ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍሳችንና የሥጋችን ሐኪም ሽባውን ከኃጢአቱ ይቅር ብሎት አካላዊ ጤንነቱን እንደመለሰለት ሁሉ፣ (ማር.2፤1-12) ቤተ ክርስቲያኑም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የመፈወስና የማዳን ሥራዎቹዋን በራሱዋ አባለትም መካከል ቢሆን እንድትቀጥል ፈቃዱ ሆኗል። የሁለቱ ምሥጢራት ማለትም ምስጢረ ንስሐና ምስጢረ ቀንዲል ዓላማም ይኸው ነው።

ንስሐ የእርቅ ምስጢር

ወደ ምስጢረ ንስሐ የሚቀርቡ ሰዎች ስለፈጸሙት ኃጢአት ከእግዚአብሔር ምሕረትን ያገኛሉ። እንዲሁም ወደ ቅዱስ ሕይወት ይመጡ ዘንድ በፍቅር፣ በመልካም አርአያነት በጸሎት ስለእነርሱ ከምትተጋውና ኃጢአታቸው ካቆሰሉዋት ቤተክርስቲያን ጋር ይታረቃሉ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.