2017-03-09 08:42:00

በኢትዮጲያ የሚገኙ አራት የቅድስት ሐና ማሕበር ደናግላን በደረሰባቸው የመኪና አድጋ አሰቃቂ በመሆነ መልኩ ሕይወታቸውን አጡ።


የሃዘን መግለጫ

የሥርዓተ ቀብር ሥነ ስርዓት

 የቅድስት ሃና ልጆች ማህበር አባል የነበሩት እህት ወይንሸት ገብሩ እህት ሞቱ ባባ እህት ግዴና ወልዱና እህት ሃና ባከቴ የካቲት 28 ቀን 2009 ዓ.ም ወደ ሀዋሳ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አብረዋቸው ይጓዙ የነበሩት የማህበሩ አባላት በደረሰባቸው አደጋ ህክምና እየተረዱ ይገኛሉ፡፡ እግዚአብሔር ለሞቱት የዘላለም እረፍትን እንዲሰጠቸው በህክምና ላይ የሚገኙትን እንዲፈውስ እንለምናለን። በዚሁ በደረሰው የመኪና አደጋ መላው የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሃዘንዋን እየገለጸች ለቅድስት ሃና ልጆች ማህበርና ለቤተሰቦቻቸው እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጥልን እንጸልያለን፡፡ 
ሐሙስ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ፍትሃት ቅዳሴ በልደታ ማርያም ካቴድራል ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ስርዓተ ቀብር በቅዱሳን ጴጥሮስ ጳውሎስ መካነ መቃብር የፈጸማል።

ብፁዕ አባታችን ካርዲናል ብርሃነየሱስ የአብይ ጾም መግብያን ምክንያት በድረግ ለመላው ለሃገራችን ህዝቦችና ለካቶሊካውያን ምእመናን ካስላለፉት መልእክት “በሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ የመኪና አደጋዎች እንደሚደርሱ በየጊዜው ከትራፊክ ፖሊስ ጽ/ቤት መስማት የተለመደ ሆኗል የብዙ ወገኖቻችን ሕይወት መቀጠፍና መጎዳቱ እንዲሁም አካል ጉዳተኛ መሆን እጅግ ያሳዝናል፡፡ የብዙ ቤተሰብ ሕይወት ባሳዛኝ ሁኔታ ይናጋል ብዙ ንብረትም ይወድማል፡፡ በተለይ በዚህ አብይ ጾም ወራት አደጋው የሚገታበት መንገድ በማሰብ እንድንጸልይና እንድንጠነቀቅ እንዲሁም የትራፊክ ህጎችን ደንቦችን እንድናከብር አደረራ እላለው” በማለት ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይ መልኩም በመጋቢት 27/1978 ዓ.ም. የእዚሁ ማሕበር አባላት የሆኑ ደናግላን ከአምቦ ወደ ጉዳር በመኪና በመጓዝ ላይ በነበሩበት ወቅት በገጠማቸው አደጋ በጉዳር አከባቢ በሚገኘው የአምቦ ውሃ ፋብሪካ አቅራቢያ በሚገኘው ድልድይ ውስጥ በመግባት 3 ደናግላን ሕይወታቸውን ማጣታቸው የታወሳል።

እግዚኣብሔር የእነዚህን አራት ደናግላንን ነብስ በአብራሃም፣ በይሳቅ፣ በያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለመላው የቅድስት ሐና ማሕበር ደንግላን እና እነርሱ ስያገለግሉዋቸው ለነበሩ ሰዎች ሁሉ በተጨማሪም ለመላው የኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ወዳጆች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። እግዚኣብሔር ከዳግመኛ ሐዘን ይሰውረን። አሜን!!

 








All the contents on this site are copyrighted ©.