2017-03-03 16:57:00

ቅ.አ.ርሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ርእዮተ-ዓለማዊ እምነት የወንድሞች ስቃይ የራሱን የማያደርግ ዓይነት መልዕልተ አምላኪ የሚያደርግ ነው


“የክርስቲያን ብሶል ስቁል ኢየሱስን ለመከተል የሚመራ እንጂ ወደ ያልተሰገወ መልዕልተ የሚሸኝ አይደለም። የተሰግወ የወንድሞችን ስቃይ የእራሱ ያደረገ እግዚኣብሔርን መከተል ነው” ይኽን ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ነግህ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት፥ በላቲን ሥርዓት ከኦሪት ዘዳም ምዕ. 30 ከቁ. 15-20 እና ከወንጌል ማርቆስ ምዕ. 9 ከቁ. 22-25 የተወሰደውን ምንባባት ላይ ተንተርሰ ባስደመጡት ስብከት ሲሆን። በዚህ ዓቢይ ጾም የጅማሬ ወቅት መለወጥ የሚለው ቃል በጥልቀት እየተስተጋባ ነው። የዕለቱ ሊጡርጊያም የመለወጥ ምዕዳን በማቅረብ ይኸንን ጥሪ ሰው እግዚኣብሔርና ጉዞ ከተሰኙት ከሦስት እውነታዎች ጋር ተጣምሮ እንደሚቀርብም ቅዱስነታቸው ጠቅሰው፥ የሰው ልጅ እውነታው፥ ከመልካሙና ከክፋት አንዱን መምረጥ ነው፥ ምክንያቱም እግዚኣብሔር ነጻነትን ስጥቶናል። ምርጫው የእኛ ነው። ምንም’ዃ ምርጫውም የእኛ ቢሆንም እርሱ ግን ለብቻችን አይተወንም። የመልካሙን መንገድ በትእዛዛቱ አማካኝነት ያመላክትልናል፡

 

ሌላው እውነታ ደግም እግዚኣብሔር ነው። ደቀ መዛሙርት የኢየሱስን ፍኖተ መስቀል ሊረዱ አልቻሉም፡ እግዚአብሔር ካለ ሓጢኣት በስተቀረ መላውን ሰብኣዊ እውነታን በራሱ ላይ አደረገ። አለ ክርስቶስ እግዚኣብሔር የለም፡ አለ ክርስቶስ እግዚኣብሔር አልቦ ስጋዌ ይሆናል ይኽ ዓይነቱ እግዚኣብሔር ደግሞ አልቦ እውነታ ይሆናል። ያልተሰገወ እግዚአብሔር ርእዮተ ዓለም የሚወልደው እግዚአብሔር ይሆናል። የእግዚአብሔር እውነታ ስለ እኛ የሚል ነው፡ ሊያድነን በክርስቶስ ተከውኗል። ከዚህ እውነታ እራሳችንን ስናገል ከክርስቶስ መስቀል ከጌታ እውነተና ስቃይ ስንርቅ ከፍቅር እንርቃለን ከእዚኣብሔር ፍቅር ከድህነት እንርቃለን፡ እንዲህ እያልን ስንርቅ ወደ ርእዮተ-ዓለማዊ እግዚኣብሔር እየቀረብን እንድሄዳለን። ርእዮተ ዓለማዊ እግዚኣብሔር፡ እኛን ለማዳን ለእኛነታችን ቅርብ ለመሆን የሚመጣ ስለ እኛ ብሎ የሚሞት አይደለ፡ ይኽ ደግሞ እውነተኛ እግዚኣብሔር አይደለም። የእግዚኣብሔር እውነታው ለማዳናችን የሚሞት ስለ እኛ የሚሰዋ ነው።

ቅዱስ አባታችን በመቀጠልም አንድ ሊጨበጥና ሊደረስ የሚችለው ነገር ብቻ ህልው ነው ብሎ የሚያምን ከሕይወት በኋላ ሕይወትና የአምላክ መኖር ማወቅ አይቻልም ብሎ የሚያምን ስነ ምርምር የሚከተልና አንድ አማኝ መካከል ስለ ተካሄደው ግኑኝነትና ውይይት ባለፈው ዘመን  በአንድ ፈረንሳዊ ደራሲ የተነገረው ታሪክ ዋቢ በማድረግ፡ ተጨባጭና ተደራሽ ብቻ በሚለው ስነ ምርምር የሚያምነው ነገር ግን ባለው መልካም ፈቃድ ተንደርድሮ አማኙን እግዚኣብሔር ከዛም ኢየሱስ ክርስቶስ በጠቅላላ ይኽ ዓይነቱ ነገር ፈጽሞ ሊገባኝ አይችልም። ክርስቶስ እንዴት ብሎ ነው እግዚአብሔር የሚባለው? ሲል አማኙን ይጠይቃል፥ አማኙም፥ ጥያቄህ ለእኔ ችግር እይደለም በማልት፡ እግዚኣብሔር ክርስቶስ ባይሆን ኖሮ ነበር ችግር የሚሆንብኝ ሲል ይመልስለታል። አዎ የእግዚኣብሔር እውነታው ይኽ ነው። ክርስቶስ ሆኖ የሚመጣ እግዚኣብሔር፡ የምኅረት መሠረቱም እርሱ ነው፡ የወንድሞቻችን ስቃይ የክርስቶስ ስቃይ ነው። የእግዚአብሔር ስቃይ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰው ሆኖ መጥቷልና። ስለዚህ ያለዚህ እውነት አቢይ ጸም መኖር ባልተቻለ ነበር። መለወጥ ይኖብናል። መለወጡ ወደ ረቂቀ እግዚአብሔር ሳይሆን፡ ተጨባጭና ክርስቶስ በሆነው እግዚአብሔር ላይ እምነታን በማድረግ ላይ ማደግ ነው። መለወጥ ይኖርብናል።

ሦስተኛው እውነታ ደግሞ ጉዞ ነው፡ ኢየሱስ፥  ሊከተለኝ የሚፈልግ እራሱን ይካድ ዕለት በዕለት መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” ይላል፡ ስለዚህ የጉዞው ተጨባጭነቱም ክርስቶስ ነው፡ ኢየሱስን መከተል ነው። እንደ ኢየሱስ የእግዚኣብሔር ፈቃድ መኖር፡ ዕለት በዕለት መስቀልን ተሸክሞ ገዛ እራስ መካድ ነው። ኢየሱስን ለመከተል ገዛ እራስ መካድ ያስፈልጋል፡ የምትሻው ማድረግ ሳይሆን ኢየሱስ የሚፈልገውን ማድረግ ነው። ሁሌ በኢየሱስ መንገድ መገኘት ነው። መንገዱም የሁሉም አገልጋይ መሆን እግዚአብሔርን ማምለክና መወደስ ነው። ይኽ ትክክለኛው መንገድ ነው። ብቸኛው የተረጋገጠ ዋስትና ያለው መንገድ ስቁል ኢየሱስን መከተል ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን፥  ይኽ መስቀል ለብዙዎች እንቅፋት ነው። እነዚህ ሦስት እውነታዎች፥  ሰው እግዚአብሔርና ጉዞ ለክርስቲያን ፈጽመው የማያደናግር ብሶል ናቸው በማለት የለገሱት ስብከት አጠቃሏል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.