2017-03-01 10:54:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "“በእግዚኣብሔር መታመን በጣም አሰፈላጊ ጉዳይ ነው" ማለታቸው ተገለጸ።


“የዛሬው የወንጌል ቃል በእግዚኣብሔር እንታመን ዘንድ ጠንከር ያለ ጥሪ ያቀርብልናል፣ ለፍጡራን ሁሉ እንክብካቤን በማድረግ ላይ በሚገኘው በእግዚኣብሔር እንታመን ዘንድም ይጋብዘናል”። ይህንን የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሲሆኑ በትላንትናው እለት ማለትም በየካቲት 19/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ አስተምህሮን ለመከታተል ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ካስተላለፉት አስተምህሮ የተቀነጨበ ነው።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች የላውን ተጫአውት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በእለቱ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የስርዐተ አምልኮ አቆጣጠር ከማቴዎስ ወንጌል 6:24-34 ላይ በተወሰደው እና “ስለ ኑሮ መጨነቅ አይገባም” በሚል ጭብጥ ዙሪያ በሚያጠነጥነው የወንጌል ክፍል ላይ ትኩረታቸውን በደረገው አስተምህሮዋቸው እንደ ገለጹት “በእግዚኣብሔር መታመን በጣም አሰፈላጊ ጉዳይ መሆኑን አስምረው እርሱ ለፍጥረታት ሁሉ ምግብን የሚያዘጋጅና ቀን በቀን ለሕይወታችን ጥንቃቄን የሚያደርግልን በመሆኑ የተነሳ በእርሱ መታመን ይገባል ብለዋል።

የሰው ልጅ በብዙ ጭንቀት ውስጥ በመግባት የመረጋጋት ወሰኑን እንዲያልፍ የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች በሕይወቱ ይከሰታሉ። ይህ ጭንቅት ብዙን ጊዜ ከንቱ ነው። ምክንያቱም ጭንቀት የሕይወትን አቅታጫ በመለወጥ ስኬታማ እንድንሆን ሊያደርገን በፍጹም አይችልም በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከጭንቀታችን ሁሉ በላይ የሆነ፣ ልጆቹን በፍጹም የማይረሳ እግዚኣብሔር በመኖሩ የተነሳ ኢየሱስ ለነገ መጨነቅ እንደ ሌለብን በተደጋጋሚ ይመክረናል ይገስጸናልም ብለዋል።

ነገር ግን አሉ ቅዱስነታቸው “በእግዚኣብሔር መታመን ምህታታዊ በሆነ መልኩ ችግሮቻችንን ይቀርፋል ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ተገቢ በሆነ መንፈስ  ችግሮቻችንን  መጋፈጥ እንችል ዘንድ ብርታትን የሰጠናል፣ ‘ብርታት ያለኝ ሰው ነኝ ምክንያቱ በጣም በሚወደኝ እና በሚንከባከበኝ በእግዚኣብሔር ስለታመንኩኝ ነው” ብለን መናገር እንድንችል ይረዳናል ብለዋል።

“አምላክ ከእኛ በጣም የራቀ እና ስም-አልባ አካል አይደለም እርሱ መጠጊያችን፣ የመረጋጋት እና የሰላማችን ሁሉ ምንጭ ነው” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሱ የማያሳፍረንና በእርግጠኛነት ልንይዘው የሚገባው የደኅንነታችን መሠረት ነው፣ እግዚኣብሔርን የያዘ ሰው በፍጹም አያፍርም ብለዋል።

በዙሪያችን ዘወትር ከሚያነፈንፈው ሰይጣን የሚጠብቀን አምላክ ነው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን እኛ ሁልጊዜ የምንረዳው የምንገነዘበው እውነታ ባይሆንም ቅሉ አምላክ ግን የእኛ ጓደኛ፣ ተባባሪና አባታችንም ነው ብለዋል።

የሚወደን፣ የሚተባበረን የሚጠብቀን አምላክ እንዳለን ሳንገነዘብ ቀርተን፣ በእጃችን ልንዳስሳቸው በምንችለው በቁሳቁሶች ላይ ትኩረታችንን እንደርጋለን በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ሁኔታ ከቁሳቁሶች በላይ የሆነውንና እግዚኣብሔር የሚባል መጠሪያ ያለውን ውድ አባታችንን ብዙን ጊዜ ችላ እንለዋለን ብለዋል።

አሁን ባለንበት የወላጅ አልባነት ስሜት በሚሰማው ዓለማችን የእግዚኣብሔርን አስፈላጊነት ሊሰማን ያስፈልጋል ያሉት ቅዱስነታቸው እኛ ብዙን ጊዜ የምናደርገው ተቃራኒውን ነው፣ እግዚኣብሔርን መፈለግ ትተን ምድራዊ የሆኑ ቁሳቆሶችን በመፈለግ ላይ ተጠምደን እንገኛለን ብለዋል። ምድራዊ የሆኑ ነገሮችን በመፈለግ ሂደት በምንጠመድበት ወቅት ሁሉ ከእግዚኣብሔር ፍቅር ራሳችንን እናርቃለን ያሉት ቅዱስነታቸው ለሀብት እና ለመሳሰሉት ምድራዊ ነገሮች ግዜያችንን በምንሰዋበት ወቅቶች ሁሉ በእነዚህ ነገሮች ፍቅር እንልከፋለን ከእግዚኣብሔር መንገድ እንድንርቅም ምክንያት ይሆኑናል ብለዋል።

ምድራዊ የሆኑ ነገሮችን ለማግኘት የምናደርገው አድካሚ እና አሰልቺ የሆነ ፍለጋ ሕይወታችን ደስተኛ እንዳትሆን እንደ ሚያደርጋት ኢየሱስ አስተምሮናል ያሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ሐዋሪያቱ ይህንን ነገር ያስወግዱ ዘንድ “በቅድሚያ የእግዚኣብሔርን መንግሥት ፈልጉ ከእዚያን ቡኋላ ሌላው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል” ብሎ እንዳስተማራቸው አስታውሰው ምን አልባት የምንመካባቸው ጉዋደኞቻችን፣ ቤተሰቦቻችን፣ የሚወዱን እና የምንወዳቸው ሰዎች ልያስቀይሙን ልያሳፍሩን ይችሉ ይሆናል እግዚኣብሔር ግን ማንንም ከቶ አያሳፍርም ብለዋል።

በዛሬው ወንጌል (ማቴ 6:24) ላይ “እግዚኣብሔርን እና ገንዘብን በአንድነት ማገልግል አይቻልም” ተብሎ ስለተጠቀሰ እኛ ከእነዚህ ሁለት ነገሮች ምርጫ ማድረግ ይጠበቅብናል ያሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔርን ወይም ደግሞ ዘላቂ የሆነ ደስታ ከማይሰጠን ምድራዊ ጣኦት ከሆነውን ገንዘብ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ይገባናል፣ ይህ የምናደርገው ምርጫ የሕይወታችንን አቅጣጫ ይወስናል ብለዋል።

የእዚህ ምድር ጣኦት የሆነውን ገንዘብ በምንመርጥበት ወቅት ተጨባጭ፣ ነገር ግን አላፊ የሆኑ ለውጦችን በሕይወታችን ልናገኝ እንችላለን እጊዚኣብሔርን እና የእርሱን መንግሥት በምንመርጥበት ወቅት ሁሉ ግን ቅጽበታዊ የሆኑ ፍሬዎችን ወይም ለውጦችን በሕይወታችን ልንመለከት አንችል ይሆናል ያሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔርን እና የእርሱን መንግሥት በምንመርጥበት ወቅት ሁሉ ሕይወታችን በተስፋ ይሞላል፣ የክርስቲያን ተስፋ ደግሞ እግዚኣብሔር ለእኛ ቃል የገባልንን ነገሮች እንደ ሚፈጽም በማመን በተስፋ የሚደረግ ጉዞ በመሆኑ የተነሳ በመከራችን ወቅቶች ሁሉ እግዚኣብሔር በፍጹም አያሳፍረንም፣ የገባልንን የደኅንነት ቃል ኪዳንን በማስታወስ ሊረዳን ሁሌም ዝግጁ ነው፣ ታማኝ አባታችን ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ገለጹት ሁል ጊዜ በእግዚኣብሔ መተማመን እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ትረዳን ዘንድ እርሷን መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ይህም ምድራዊ የሆኑ ፈተናዎችን መገፈጥ የምንችልበትን ኋይል የሰጠናል በተጨማሪም ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ምስክር መሆን እንችል ዘንድ ስለ ሚያግዘን የእርሱን አማልጅነት ሁልጊዜ መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.