2017-02-24 12:41:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው “ሁለት ገጽታ ያለው ሕይወት በመኖር ‘ለታናናሾቻችን’ እንቅፋት መሆን የለብንም" ማለታቸው ተገለጽ።


 “ሁለት ገጽታ ያለው ሕይወት በመኖር ‘ለታናናሾቻችን’ እንቅፋት መሆን የለብንም፣ ምክንያቱም ይህ እንቅፋት የሰውን ሕይወት ያበላሻልና፣ ይህም ተግባራችን መንፈሳዊ ለውጥ እንድንሻ ያስገድደናል” ይህንን የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ይህንንም መልእክት ያስተላለፉት በትላንትናው እለት ማለትም በየካቲት 16/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት መሆኑም ታውቁዋል።

እንደ የጎርጎሮሳዊያኑ የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል 9:41-50 ላይ በተወሰደው “የኋጢያት ምክንያት” በሚል አስርስት በቀረበው የኢየሱስ አስተምህሮ ዙሪያ ባጠነጠነው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከምታደናቅፍ “እጅህ ኋጢያት እንድትሰራ ምክንያት ከሆነ ቆርጠህ ጣለው፣ ዐይንህ ኋጢያት እንድትሠራ ምክንያት ከሆነ አውጥተህ ጣለው” ከሚለውን የእለቱ የወንጌል ቃል ጠቅሰው መልካም የሚባሉ ሰዎች ሁሉ በእግዚኣብሔር ላይ ከፍተኛ የሆነ መተማመን አላቸው የሰውን ሕይወት ሊያበላሹ፣ ሊያፈርሱትም ከሚችሉ እንቅፋቶች ራሳችንን መቆጠብ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት :

አሳፋሪ የሆነ ድርጊት መፈጸም ማለት ምን ማለት ነው? እንደ እኔ አስተሳሰብ ከሆነ የምንናገረው እና የምንሠራው ነገር የተለያየ ከሆነ፣ ሁለት ዓይነት ሕይወት የምንኖር ከሆን፣ ይህ ተግባራችን አስፋሪ ነው ማለት ይቻላል። አሳፋሪ ሕይወት ማለት በአጠቃላይ እኔ በጣም ጥሩ የካቶሊክ ምዕመን ነኝ፣ ሁል ጊዜ መስዕዋተ ቅዳሴን ለመሳተፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እሄዳለውኝ፣ የእከሌ ማሕበር አባል ነኝ ብለን በመመካት ስንናገር እና ነገር ግን ሕይወታችን ክርስቲያን ክርስቲያን የማይሸት ከሆነ፣ በምናስተዳድራቸው የግል ድርጅቶቻችን ውስጥ ተቀጥረው ለሚሠረ ሰራተኞች ተገቢ እና በቂ የሆነ ደሞዝ የማንከፍል ከሆነ፣ የሰዎችን ጉልበት የምንበዘብዝ ከሆነ፣ እጄ በወንጀል የቆሸሸ ከሆነ፣ በሕገወጥ መልኩ ያገኘውትን ገንዘብ ሕጋዊ ለማድረግ የምሞክር ከሆነ እነዚህ እና እነዚህን የመሳሰሉት ተግባሮች ስንፈጽም ደግሞ ሁለት ገጽታ ያለው ሕይወት እንኖራለን ማለት ነው። በምንኖርበት ሥፍራ ወይም ደግሞ በሥራ ቦታችንእንደ እርሱ ወይም እንደ እርሷ ዓይነት የካቶሊክ ምዕመን ከመሆን ይልቅ እምነት የለሽ ብሆን ይሻለኛልሲባል ስንት ጊዜ ሰምተን ይሆን? ይህን ነው እንግዲህ አስፋሪ ተግባ ነው የምላችሁ! ይህንን ነገር ስንሰማ መንፈሳችን ይዳሽቃል። ይህም ተግባር በእየቀኑ እይተፈጸመ ይገኛል። ማረጋገጫ ከተፈለገም በእየ እለቱ በቴሌቪን ወይም በጋዜጦች ላይ የሚወጡትንና የሚተላለፉትን ዜናዎች ማየት በቅ ይመስለኛል። በእነዚህ ጋዜጦች ላይ ብዙ ቅሌቶች ሲጋለጡ እናነባለን፣ ምንም እንኳን ጋዜጠኞች አንድ አንዴ እነዚህን ቅሌቶች አጋነው ለማቅረብ ቢዳዳቸውም፣ ቅሌት ለሰው ሕይወት እንቅፋት ይሆናል የምላችሁም በእዚሁ ምክንያት ነውብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ግለጹት “ሁለት ዓይነት ሕይወት የሚመነጨው የልባችንን መሻት ስንከተልና ከአዳም በወረስነው ኋጢያት ምክንያት ነው ካሉ ቡኋላ “እኛ ሁላችን መልካም ነገርን እንድናደርግ በመጠራታችን የተነሳ ሁለት ዓይነት ሕይወት እየኖርን መሆኑን እና አለመሆኑን ለማጣራት  ዛሬ ራሳችንን መመርመር ይኖርብናል ካሉ ቡኋላ መልሱ አዎን ከሆነ መልካም ተግባራችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል፣ ነገር ግን መልሱ ሁለት ዓይነት ሕይወት መኖራችንን የሚያረጋግጥ ሆኖ ከተገኘ ዛሬውኑ መንፈሳዊ ለውጥ ማድረግ ይጠበቅብናል፣ ይህንንም የለውጥ ጉዞ በሚጋባ ማከናወን እንድንችል እግዚኣብሔር ይረዳን ዘንድ መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.