2017-02-14 11:06:00

ቅዱስነታቸው "ቅንዐትና ምቀኝነት የወንድማማችነት ስሜትን በማሻከር አለመጋባትን ስለሚፈጥሩ እነዚህን ስሜቶች ማስወገድ ይገባል" አሉ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የወንድማማችነት ስሜትን በማሻከር አለመግባባትን በቤተሰቦቻችንና በሕዝቡ ውስጥ እንዲከሰት ማድረገ የሚችሉትን ቅንዓትና ምቀኝነትን ማስወገድ ይገባል ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ይህንን ያሉት በየካቲት 6/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ሲሆን በእለቱ ያሰሙት ስብከት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የስርዓተ-ሊጡርጊያ አቆጣጠር በእለቱ በቀዳሚነት ከተነበበውና ከኦሪት ዘፍጥረት በተወሰደው የአቤል እና የቃየን ታሪክ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት ትችሉዋል።

“እግዚኣብሔር የቃየንን መስዋዕት ባለመቀበሉ የተነሳ ቃየን በውስጡ ባደረችበት ትንሽዬ ቅናት ተነሳስቶ ከፍተኛ የሆነ ስህተት ፈጽሞ እንደ ነበረ’ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህቺህ ትንሽዬ የቅናት ስሜት በልቡ ቀስ በቀስ ስትብላላ ቆያታ ቀስ በቀስ እያደገች መምጣቱዋንም ገልጸው በእዚህ መልኩ ነው የጠላትነት መነፍስ በእኛ ውስጥም የሚያድገው ብለዋል።

“ከአንዲት ትንሽዬ ነገር እንነሳና፣ ይህችም ነገር ወደ ትንሽዬ ቅናት ትቀየራለች፣ ይህችህም ቅናት ቀስ በቀስ እያደገች ነገሮችን በእዚህ የቅናት መንፈስ ውስጥ ሆነን እንድንምለከት ያደርገናል፣ ይህም ትንሽዬ ጉድፍ ነገር እያደገ እንደ አንድ ትልቅ ግንድ ሆኖ በፊታችን ላይ ይደነቀራል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሕይወታችንም በእዚህ በቅናት በተተበተበ ነገር ውስጥ እንዲሽከረከር በማድረግ ከወንድሞቻችን ጋር የነበረንን ግንኙነት ያሻክራል ወይም እንዲፈርስ ያደርጋል ብለዋል።

“በእዚህም መልኩ ያደገው የጠላትነት መንፈስ ምጥፎ ነገሮችን በማስከተል ይጠናቀቃል” ያሉት ቅዱስነታቸው “በወንድማማችነት ቦታ ጠላትነት ይተካል፣ ይህም እኛን ብቻ ሳይሆን ቀስ በቀስ ማኅበረሰቡንም ያፈርሳል” ብለዋል።

“ይህም እውነታ ነው በቃዬን ሕይወት ውስጥ የተንጸባረቀው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እቺ ትንሽዬ የተባለች ቅናት በከፍተኛ ሁኔታ አድጋ ቃዬን ወንድሙን አቤልን እንዲገለው አነሳስቶታል፣ አድርጎታልም” ካሉ ቡኋላ የእነዚህ ክፉ ነገሮች ሁሉ ምንጭ የሆኑትን መራራርና ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ስሜቶችን አውልቅን መጣል ይገባናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠናቀቂያ ላይ እንደ ገለጹት “ዛሬ እግዚኣብሔር ለቃሄን `ወንድምህ የታለ?` ያለውን ቃል በማስታወስ ዛሬም ቢሆን ይህንን ተመሳሳት ጥያቄ ለእኛም ያቀርብልና ካሉ ቡኋላ ይህም ጥያቄ እንደ ወንድም ሳይሆን እንድ ቁስ አካል በመቆጠር ላይ የሚገኙትን በዓለም ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ በምላሳችን እንዴት እየገደልናቸው እንደ ምንገኝ ያስታውሰናል ካሉ ቡኋላ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ከወንድማማችነት መንፈስ ይልቅ ትኩረት እየተሰጠው የሚገኘው የጥቅማጥቅም ጉዳይ በመሆኑ ይህንንም ግላዊ ስሜቶቻችንን አስወግደን ለወንድሞቻችን ተደራሽ የምንሆንበትን ጸጋ እግዚኣብሔር እንዲለግሰን መጸለይ ይገባል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.