2017-02-11 10:08:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "ከሰይጣን ጋር መወያየት በፍጹም አያስፈልግም" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በየካቲት 3/2009 ዓ.ም. ካህናት ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ፈተናዎች በሚያጋጥሙን ወቅቶች ሁሉ ራሳችንን ከእግዚኣብሔር እንዳናሸሽ የእግዚኣብሔር ጸጋ ይረዳናል” ካሉ ቡኋላ በተጨማሪም ለፈጸምናቸው ስህተቶች ይቅርታን በመጠየቅ ከወደቅንበት ተነስተን ወደ ፊት እንድንጓዝ ይረዳናል ማለታቸውም ተገልጽዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት መሰረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር ከኦሪት ዘፍጥረት በተወሰደውና አዳም እና ሄዋን እግዚኣብሔር አትብሉ ያላቸውን ፍሬ በበሉበት ወቅት ራቁታቸውን መሆናቸውን ተረድተው ከአምላክ የተደበቁበት ታሪክ ላይ ተመስርተውና ኢየሱስ መስማት የተሳነውን እና ድዳ የነበረውን ሰው መፈውሱን በሚያወሳው የወንጌል ክፍል ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

“በምንም አይነት ሁኔታ ከሴይጣን ጋር መደራደር የለብንም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ከሰይጣን ጋር መደራደር ወይም መወያየት የመጨረሻ ውጤቱ በኋጢያት ውስጥ መዘፈቅ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።

ፈተና ራሳችንን ከእግዚኣብሔር እንድንደብቅ ያደርገና በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ፈተና በኋጢያት ውስጥ ተዘፍቀን እንድንኖር ያደርገናል ብለዋል። የአዳም እና የሄዋንን መፈተን ኢየሱስ በበረሃ ውስጥ ከመፈተኑ ጋር በማያያዝ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሁለቱም ማለትም አዳም እና ሄዋንን እንዲሁም ኢየሱስ ራሱን ሊፈትነው የመጣው ሴይጣን በእባብ ተመስሎ መምጣቱን አስታውሰው በጣም ትሁት እና ማራኪ ለመሆን በመጣር በብልጣብልጥ ባሕሪው ሊያታልለን እንደ ሚመጣም ጨምረው ገለጸዋል።

እባብ በእዚህ የማታለል ባሕሪ በጣም የተካነ ነው “የውሸቶች ሁሉ አባት ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እንዴት ሕዝቡን ማታለል እንዳለበት ያውቅበታል፣ ይህንንም በሄዋን ላይ ተፈጻሚ በማድረግ ክህሎቱን በግልጽ አሳይቱዋል ብለዋል።

እባቡ በመጀመሪያ ሄዋን ጥሩ ስሜት እንዲሰማት ካደረገ ቡኋላ ቀስ በቅስም ከእርሱዋ ጋር መወያየት እና መነጋገር  መጀመሩን በማውሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቀስ በቀስም እርሱ ወደ ፈለገበት ዓላማ ውስጥ እንደ ከተታትም ጨምረው ገልጸዋል። ነገር ግን በኢየሱስ ላይ አድርጎት የነበረው ሙከራ ለየት ያለ እንደ ነበረ በመጠቅስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከኢየሱስ ጋር የነበረው ቆይታ ግን በኢየሱስ አሸናፊነት መጠናቀቁን ገልጸዋል። ሰይጣን ከኢየሱስ ጋር የተለያዩ አጉዋጊ የሆኑ ነገሮችን ሳይቀር በመጠቀም ሲወያይ ቆይቶ እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ሰይጣን በማነኛው ወቅት ሰዎችን ማሳሳት ሲፈልግ ይህንን ተግባሩን የሚጀምረው በውይይት ነው ብለዋል።

ሰይጣን በተደጋጋሚ ኢየሱስን ለማታለ ፈልጎ ነበረ፣ ነገር ግን ኢየሱስ አለተሸነፈም ያሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ በፈተናው ወቅት የስይጣኑን ፈተና ሊቋቋም የቻለው በራሱ ቃላት ሳይሆን ከእግዚኣብሔር ቃል በመጥቀስ እንደ ነበረ አስታውሰው “በራሳችን ቃላት እና ክህሎት ላይ ተመርኩዘን ከሴይጣን ጋር በምንወያይባቸው ወቅቶች ሁሉ መጨረሻችን እንደ አዳም እና ሄዋን የሚጠብቀን ውድቀት ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት ቤተ ክርስቲያን መታለልና ሞኝ መሆን እንደ ሌለብን ታስተምረናለች ካሉ ቡኋላ በምንታለልባቸው ወቅቶች ሁሉ ዐይናችንን መክፈት ይጠበቅብናል፣ ጌታ እንዲረዳንም መጠየቅ ይኖርብናል ብለው ፈተናዎችን በራሳችን ብርታት ማለፍ ስለ ማንችል ሁል ጊዜም ቢሆን የእግዚኣብሔር እርዳታ ያስፈልገናል ካሉ ቡኋላ አዳም እና ሄዋን ኋጢያት በሠሩበት ወቅት ከእግዚኣብሔር ተደበቁ፣ ኢየሱስ ግን በተቃራኒው ወደ እርሱ እንድንመለስ እና የኋጢያታችንን ስርዬት እንድናገኝ ሁሌም በፀጋው ይባርከናል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.