2017-02-09 10:43:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የረዕቡ የየካቲት 1/2009 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በየካቲት 1/2009 ዓ.ም. የመንግሥት ባለስልጣናት የሰው ልጆችን ሕገወጥ በሆነ መልኩ የሚያዘዋውሩ ሰዎች እያስከተሉት ያለውን ከፍተኛ ጥፋት በጥብቅ እንዲዋጉ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ይህንን መልእክታቸውን ያስተላለፉት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር  በየካቲት 8/2016 ዓ.ም. ተከብሮ የዋለውን “የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰላባ ለሆኑ ሰዎች በዓለማቀፍ ደረጃ በሚደረገው የአንድ ቀን ጸሎት እና የግንዛቤ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት በተካሄደበት እለት ባስተላለፉት መልእክት መሆኑም ተዘግቡዋል።

ከቫቲካን ሬዲዮ የተላለፈውን የየካቲት 1/2009 ዓ.ም. ሙሉ ዜና ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በእለቱ በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ግብኝዎች ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት ለእዚህ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ በተለይም ሕፃናትንና ለአቅመ አዳም እና ሄዋን ያልደረሱ ታዳጊ ልጆችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መልኩ ከእዚህ አስከፊ፣ ጨቋኝና በዝባዥ ከሆነ ወንጀል እንዲወጡ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ ሰዎችንና ድርጅቶችን እጅግ በጣም ማመስገናቸውም ተገልጸዋል።

“በተለያዩ የመንግሥት ስልጣን ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ በአስቸኳይ ይህ አስከፊ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ለታዳጊ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ድምጽ በመሆን ከእዚህ ሕልውናቸውን እንዲያጡ ካደረገው ባርነት ይወጡ ዘንድ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ” በማለት ምልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በፍጹም ተቀባይነት የሌለውን አዋራጅ የሆነ ተግባር ማንኛውም መንገድ በመጠቀም ይህንን ወንጀል መዋጋት ይገባል ብለዋል።

የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰላባ ለሆኑ ሰዎች በዓለማቀፍ ደረጃ በሚደረገው የአንድ ቀን ጸሎትና የግንዛቤ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት የተካሄደበት የዛሬው እለት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የሥርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር በዛሬው እለት ከተከበረው የቅድስት ጁሴፒና ባኪታ በዓል ጋር መሳ ለመሳ የተከበረ መሆኑንም ለመራዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም እንደ ገለጹት በዜግነት ሱዳናዊት የሆነችው ቅድስት ባኪታ በልጅነቱዋ “አዋራጅ በሆነው የባርነት ቀንበር ሥር በነበረችበት ወቅት ሁሉ በምንም ዓይነት ሁኔታ ተስፋ ያለመቁረጧን” የገለጹት ቅዱስነታቸው ወደ አውሮፓ በባርነት ተሽጣ በመጣችበት ወቅት በእምነቱዋ በመጽናት የእግዚኣብሔርን የጥሪ ድምጽ ሰምታ የምንኩስናን ሕይወት ለመጀመር ወደ ገዳም ገብታ እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን በቅድስት ጁሴፒና ባኪታ በአሁኑ ወቅት ሀገራቸውን በተለያዩ አስገዳጅ ሁኔታዎች ጥለው በመሰደድ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ትረዳ ዘንድ መጸለይ እንደ ሚገባም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.