2017-02-07 11:39:00

የባሕር ዳር ደሴ ጳጳስ የሆኑ ክቡር አቡነ ልሳነ-ክርስቶስ በቫቲካን በሚገኘው የቅ. እስጢፋኖስ የጸሎት ቤት ማዕረገ ድቁና ሰጡ።


በጥር 28/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ እስጢፋኖስ የጸሎት ቤት የድቁና ማዕረግ አሰጣጥ መፈጸሙ ታወቀ። የባሕር ዳር ደሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑ ክቡር አቡነ ልሳነ-ክርስቶስ ይህንን የድቁና ማዕረግ ለሪካርዶ ማርቲኖ መስጠታቸው የታወቀ ሲሆን ዲያቆን ሪካርዶ ማርቲኖ በዜግነት ሜክሲኮአዊ ሲሆን በኢትዮጲያ በሚገኘው የባሕር ዳር ደሴ ሀገረ ስብከት በመገኘት በተለይም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ስር በሚገኘው በመተከል ዞን አከባቢ ሐዋሪያዊ ተልዕኮን ለማከናወን ዝግጁ መሆኑን በእለቱ አስታውቁዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ዝርዝር ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡር አቡነ ልሳነ ክርስቶስ በእለቱ በተከናወነው የድቁና ማዕረግ አስጣጥ ስነስረዓት ላይ ባሰሙት ስብከት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድንበር የለሽ ቤተ ክርስቲያን መሆኑዋን እና በተጨማሪም አንዲት፣ ካቶሊካዊት፣ ሐዋሪያዊት መሆኑዋንም አውስተው ድያቆን ሪካርዶ ማርቲኖ ውድ እና ብርቅ የሆነውን የወጣትነት ሕይወቱን ለጌታ አገልግሎት ለማዋል ሀገሩን እና ቤተሰቦቹን ትቶ ክርስቶስ በሚፈቅደው መልኩ እርሱን ለማገልገል ወደ ኢትዮጲያ ለመሄድ መወሰኑ ታላቅ የሆነ ምስክርነት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.