2017-02-04 11:29:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የአርብ የጥር 26/2009 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በጥር 26/2009 ዓ.ም. የተከበረውንና በሙሴ ሕግ መሠረት የመንፃት ሥርዓት የሚፈጸምበት እለት በደረሰ ጊዜ እናቱ ማሪያም እና ዮሴፍ ሕፃኑን ኢየሱስን ለእግዚኣብሔር ለማቅረብ ወደ ኢየስሩሳሌም ይዘውት የሄዱበት ቀን የሚዘከርበት በዓልን ምክንያት በማድረግ እና በእለቱም በተመሳሳይ መልኩም የተከበረውን በምንኩስና ሕይወት የሚኖሩ ካህናት፣ ደናግላን እና ገዳማዊያን በተጨማሪም በሐዋሪያዊ ተልዕኮ የተሰማሩ ሰዎች የሚታሰቡበት በዓልን አስመልክተው ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእለቱም ዓለማቀፍ የመናኒያን ቀን የተዘከረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም በዓል በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሕይወታቸውን ለእግዚኣብሔር አገልግሎት ለየት ባለ ሁኔታ በንጽሕና፣ በድኽነት እና በታዛዥነት ለመኖር ቃል በመግባት ሕይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉ ሰዎች ሁሉ በሕይወታቸው ጽናት ይኖራቸው ዘንድ እግዚኣብሔር እንዲረዳቸው ጸሎት መደረጉ ታውቁዋል። ይህ ዓለማቀፍ የመናኒያን ቀን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1997 በጊዜው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩ በዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ አነሳሽነት መከበር እንደ ጀመረ የታወቀ ሲሆን በጥር 26/2009 ዓ.ም. የተከበረው 21ኛው የመናኒያን ቀነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.