2017-02-03 16:57:00

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፥ ማኅሌት ስነ ጥበብንና እምነትን የሚያዋህድ ጥበብ ነው


በጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ሕንፃ እ.ኤ.አ. የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው ቅኝትና ቤተ ክርስቲያን፡ ስግደት አምልኮና ባህል ከ50 ዓመት የማህሌታውያን ተቋም ቅዋሜ ውዲህ” በሚል ርእስ ሥር ያሰናዳው ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም. መከፈቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሉካ ፐለግሪኒ አስታወቁ።

የማህሌታውያን ተቋም ቅዋሜ ታውጆ እስራ ላይ መዋል ከጀመረ ይኸው 50 ዓመት ማስቆጠሩ ሲገለጥ ይኸንን የዚህ ተቋም ቅዋሜ አመጣጥ በጠቅላላ ታሪኩ ከምን እና ወዴት የሚለውን ሁሉ ለማስታወስ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያሰናዳው ዓውደ ጥናት ማህሌት ጥራትና ግጥም ብሎም ዜማዎችን ከሊጡርጊያ ጋር ያላቸው ተዛምዶነት የሚያብራራና በእምነትና በስነ ጥበብ መካከል ያለውን ግኑኝነት የሚቃኝ መሆኑ የባህል ጉዳይ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ የጠቀሱት ልኡክ ጋዜጠኛ ፐለግሪኒ ማህሌት በሊጡጊያ ስግው ሆኖ የውህበትና የውህበት መግለጫ ነው በማለት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ገልጠው በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ክብር በጥልቀት አውደ ጥናቱ በመተንተን መሻሻል የሚገባው እንዲሻሻል የንዋየ ማህሌት አጠቃቃም የማሕሌተኛው ክርስቲያናዊና ባህላዊ ብስለት ላይ እንዲተኰር የሚያስገነዝብና ማሕሌተኛው ስለ ሊጡርጊያና ባጠቃላይ የቲዮሎጊያ ጠቅለል ያለ ግንዛቤ ያለው እርሱም በቲዮሎጊያ ዙሪያ ሕንጸት እያገኘ ማህሌቱና የቲዮሎጊያና የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት አዛምዶ የእምነት ውበትንና ውህበትን መግለጫ ጥበብ እንዲሆን በማድረጉ አገልግሎት ብቃት ያለው ለማድረግ የሚያነቃቃና ይክ ዓይነቱ ኣካሄድም ከነበረው በበለጥ እንዲሻሻል የሚያስገነዝብ ዓውደ ጥናት እንደሚሆን ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ እንዳመለከቱ ልኡክ ጋዜጠኛ ፐለግሪኒ አስታውቋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.