2017-02-02 13:01:00

ከቫቲካን ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የጥር 22/2009 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 21/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስትምህሮ ማስተላለፋቸው የታወቀ ሲሆን በእለቱ ያስተላለፉት አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው እንደ ጎርጎሮሳዊያን የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 5 ላይ የተጠቀሰው ኢየሱስ በተራራ ላይ ሆኖ ያስተማረ ትምህርት ላይ ያተኮረ ሲሆን በእዚህም አስተምህሮዋቸው እውነተኛ ደስታን እንዴት ማግኘት እንደ ሚቻል ማብራራታቸውም ተገልጹዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዜት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የማቴዎስ ወንጌል በአዲስ ኪዳን ውስጥ በጣም አስፍልስጊ የሆነ መጽሐፍ መሆኑን በመግለጽ አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ የአባቱን ፈቃድ እና ሰዎች ሊከተሉት የሚገባውን ወደ ደስታ የሚመራ ጎዳናን ያሳየበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.