2017-02-02 10:40:00

ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ታዋቂነትን ሳይሻ በመካከላችን ሁል ጊዜ እየተመላለሰ ይገኛል ማለተችው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጥር 23/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት ኢየሱስ ምንም ዓይነት ታዋቂነትን ሳይሻ በመካከላችን ሁል ጊዜ እየተመላለሰ ይገኛል ማለተችው ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዜት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ!

ዓይናችንን ያለማቋረጥ በኢየሱስ ላይ የሚያተኩር ከሆነ በሚይስደንቅ ሁኔታ እርሱም በፍቅር እንደ ሚመለከተን መገንዘብ እንችላለን በማለት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በእለቱ ከተነበበው ወደ ዕብራዊያን ከተጻፈው መልዕክት በመጥቀስ በጽናት ዓይናችን በኢየሱስ ላይ እንዲያተኩር ማድረግ ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ በወንጌል አማካይነት ኢየሱስ እኛን ይቀርባል፣ ይመለከተናልም ኢየሱስ ሁል ጊዜም ቢሆን ለእኛ ቅርብ ነው፣ በእኛ መካከልም ይመላለሳል ብለዋል።

“ኢየሱስ ሕዝቡ እንዳይነካው በማሰብ እንደ አንድ ባለ ስልጣን በጠባቂዎች ታጅቦ የሚዘዋወር አምላክ አልነበረም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሕዝቦች መካከል በነፃነት በመዘዋወር በሕዝቡ ተከቦ ይኖር እንደ ነበረም ገልጸዋል።

ኢየሱስ ለማስተማር በሚወጣባቸው ወቅቶች ሁሉ በብዙ ሕዝብ ይከበብ እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው እርሱም ሕዝቡን፣ ሕዝቡም እርሱን ይፈልጉት እንደ ነበረም ጠቅሰው ይህም የሚያሳየው እርሱ ሕዝቡን በአጽኖት እንደሚፈልግ እና የሕዝቡም ምልከታ በእርሱ እና በእርሱ ብቻ ላይ እንደ ነበረ ያሳያል ብለዋል።

ዛሬ ከማርቆስ ወንጌል ከምዕራፍ 5.21-43 ላይ ሲነበብ በሰማነው የእግዚኣብሔር ቃል ውስጥ ኢየሱስ ሁለት ታአምራትን መፈጸመኑ ይተርክልናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቅድሚያም ለአሥራ ሁለት ዓመታት ያህል ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል ሲመላለስ ባየችሁ ጊዜ ልብሱን እንኳን ብነካ እፈወሳለሁ በሚል እምነት የካባውን ጫፍ በነካችው ወቅት ኢየሱስም መነካቱን አውቆ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

በሁለተኛነትም የሙክራብ አለቃ የነበረው የኢያኢሮስ ልጅን ከሞት ማስነሳቱን በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህቺ ከሙታን የተነሳችው ልጅ እርቧት እንደ ነበረ ኢየሱስ በመረዳቱ ቤተሰቦቹዋ የሚበላ ነገር እንዲሰጡዋት መናገሩንም ጨምረው ገልጸዋል።

የኢየሱስ እነዚህን ሁለት ሴቶች አትኩሮ ተመልክቶዋቸው እንደ ነበረ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም እኛ በችግር ላይ በምንሆንባቸው ወቅቶች ሁሉ ኢየሱስ እያንድ አንዳችንን እንዴት አትኩሮ እንደ ሚመለከትን ያሳያል ካሉ ቡኋላ ታላላቅ የሚባሉ ችግሮቻችንን እና ደስታዎቻችንን እንዲሁም ጥቃቅን የሚባሉ ነገሮቻችንን ሁሉ አትኩሮ እንደ ሚመለከትም ገለጸዋል።

ኢየሱስም እነዚህን ነገሮቻችንን ለመረዳት ያቻለው ለእኛ ቅርብ ስለ ሆነ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው መቼም ቢሆን ከእኛ እንደ ማይርቅ፣ እንዲሁም በእየጊዜው ጥቃቅን የሚባሉ ነገሮቻችንን ሳይቀር እንደ ሚመለከትም ጨምረው ገልጸዋል።   

እኛም በአንጻሩም ወደ እርሱ ብንመለስ እና በብርታት አይናችንን በእርሱ ላይ እንዲያተኩር በምናደርግባቸው ወቅቶች ሁሉ ኢየሱስ በታላቅ አግራሞት ይመለከተናል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም ኢየሱስ የኢያኢሮስ ልጅን ከሞት ካስነሳት ቡኋላ ሕዝቡ በመገረም እንደ ተመለከተው ሁሉ እኛም በአግራሞት ወደ እርሱ መቅረብ የገባናል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያስዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.