2017-01-30 16:15:00

ቅዱስነታቸው “በመንፈስ ድኸ የሆነ ሰው ትሁት፣ ታዛዥ እና ለእግዚኣብሔር ፀጋ ራሱን ያዘጋጀ ሰው ነው" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 21/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስትምህሮ ማስተላለፋቸው የታወቀ ሲሆን በእለቱ ያስተላለፉት አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው እንደ ጎርጎሮሳዊያን የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 5 ላይ የተጠቀሰው ኢየሱስ በተራራ ላይ ሆኖ ያስተማረ ትምህርት ላይ ያተኮረ ሲሆን በእዚህም አስተምህሮዋቸው እውነተኛ ደስታን እንዴት ማግኘት እንደ ሚቻል ማብራራታቸውም ተገልጹዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

የማቴዎስ ወንጌል በአዲስ ኪዳን ውስጥ በጣም አስፍልስጊ የሆነ መጽሐፍ መሆኑን በመግለጽ አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ የአባቱን ፈቃድ እና ሰዎች ሊከተሉት የሚገባውን ወደ ደስታ የሚመራ ጎዳናን ያሳየበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው ብለዋል።

ይህ መልእክት ከእዚህ ቀደም ለድሆችና ለተጨቆኑ ሰዎች ሁሉ አምላክ ነፃ እንደሚያወጣቸው እና  ሊታደጋቸው እንደ ሚመጣ በነቢያት የተነገረ መልዕክት ነው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ኢየሱስ ለሕዝቡ ያሳያቸው መነገድ ለየት ያለ ማንገድ መሆኑን አስረድተው ኢየሱስ በአስተምህሮው የክርስትናን ደስታ ለመጎናጸፍና ቃል የተገባልንን ደኅንነት መጎናጸፍ የምንችለው በእግዚኣብሔር ስንታመን ብቻ መሆኑን አስይቶናል ብለዋል።

“በመንፈስ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ስለ ሆነች ደስ ይበላቸው” የሚለውን እውነታኛ ደስታ በሚል አርዕስት ኢየሱስ ለሕዝቡ በተራራ ላይ ያስተላለፈውን የመጀመሪያ  ሐረግ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው “በመንፈስ ድኸ የሆነ ሰው” አመጸኛ ሰው አይደለም ነገር ግን ራሱን እንዴት ትሁት፣ ታዛዥ እና ለእግዚኣብሔር ፀጋ  ራሱን ዝግጁ ማደረግ እንደ ሚችል የሚያውቅ ሰው ነው ብለዋል።

በመንፈስ ድኸ የሆነ ሰው ደስታው ሁለት ገጽታ አለው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችለው ቁሳዊ የሆኑ ነገሮችን በግባቡ ከመጠቀም ጋር የተያያዘ ድኽነት መሆኑንም አስርድተዋል።

አንድ ሰው በከፍተኛ የሆነና በማይጠገብ የፍጆታ አስፈላጊነት አስተሳሰብ በሚለከፍበት ወቅት “ብዙ ነገር ባለኝ መጠን፣ የበለጠ ነገር ያስፈልገኛል” ብሎ እንዲያምን ይገፋፋዋል ያሉት ቅዱስነታቸው የእዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ነብሳችንን ያጠፋታል ካሉ ቡኋላ የእዚህ ዓይነቱ አባዜ የተጠናወተው ሰው በፍጹም ደስታ ሊኖረው አይችልም ብለዋል።

“የመንፈስ ድኽነት” አሉ ቅዱስነታቸው  “የመንፈስ ድኽነት የሚገለጸው ክርስቲያኖች ስያመሰግኑ እና እግዚኣብሔር እኛን እና ዓለምን በፍቅር መፍጠሩን አምነው ስቀበሉ ብቻ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው በተጫማሪም እምነቱን በእግዚኣብሔር ላይ ያደረገበትን መንገድ ትክክለኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ብለዋል።

“በቁሳዊ ነገሮች የማይተማመን ሰው እርሱ በመንፈስ ራሱን ዝቅ ያደረገ ክርስቲያን ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው በግሉ አስተያየት እና ሐሳብ ላይ ብቻ ግትር የሆነ ሰው ሳይሆን ነገር ግን በክብር እና በፍላጎት የሌሎች ሰዎችን ውሳኔ እና ሐሳብ ለመስማት ዝግጁ የሆነ ሰው መሆን የግባዋል ብለዋል።

“በማኅበረሳባችን ውስጥ በመንፈስ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ በረከት ያሉ ሰዎች ቢኖሩ ኖሮ በማኅበረሳባችን ውስጥ አሁን የሚታየው ክፍፍል፣ አለመግባባት እና ንትርክ ባልተፈጠረ ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው ትህትና እንደ ፍቅር በክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ በጋራ ለመኖር አስፈላጊ የሆነ ሥነ-ምግባር ነው ብለዋል።

ወንጌላዊ በሆነ አገላለጽ ድኽነት ወደ እግዚኣብሔር መንግሥት የሚያስገባ መንገድ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም መንገድ የሚከተለው ለራሳችን ብቻ ማግበስበስ የሚለውን አመለካከት ሳይሆን ያለንን መካፈል የሚለውን አመለካከት የያዘ በመሆኑ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት “በፍቅር መንገድ ላይ መጓዝ የምንችለው የተከፈተ ልብ ሲኖረን ብቻ ነው” ካሉ ቡኋላ በመንፈስ ራሷን ዝቅ ያደረገችሁን የእመቤታችንን የማሪያምን አብነት በመከተልና ለእግዚኣብሔር እቅድ ሙሉ በሙሉ ራሳችንን ስናስገዛ መሆኑንም ከጠቀሱ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።   

 








All the contents on this site are copyrighted ©.