2017-01-24 10:16:00

ከቫቲካን ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የጥር 15/2009 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ክርስቲያኖች ሕብረት ይፈጥሩ ዘንድ ሁል ጊዜ መጸለይ እንደ ሚገባ ጥሪ ማድረጋቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ይህንን ጥሪ ያደረጉት በጥር 14/2009 ዓ.ም. የጠቅላላ አስተምህሮዋቸውን ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት ካካሄዱት አስተምህሮ በመቀጠል ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙት የመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት ቡኋላ ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው አጽኖት ሰጥተው የገለጹት ለአንድ ሳምንት ያህል በጸሎት በመታሰብ ላይ ባለው እና ከጥር 10/2009 ዓ.ም. እሰክ መጭው ረዕቡ ጥር 17/2009 ዓ.ም. ስለ ክርስቲያን ሕብረት በሚደረገው ጸሎት አስፈላጊነ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

“ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ” ብሎ ኢየሱስ በዩሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 17,21 ላይ የጸለየው ጸሎት እስኪሳካ ድረስ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድነት እና ባለማቋረጥ ሊጸልዩ ይገባል ያሉት ቅዱስነታቸው ለእዚህ አመት ለክስቲያኖች ሕብረት በሚካሄደው የአንድ ሳምንት ጸሎት መሪ ቃል እንዲሆን የተመረጠው “የክርስቶስ ፍቅር ለእርቅ ይገፋፋናል” የሚለው ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች ከጻፈው ከሁለተኛ መልዕክቱ የተወሰደ መሆኑም ጨምረው ገልጸዋል።

በሚቀጥለው ርዕቡ ጥር 17/2009 ዓ.ም. ይህ ለክርስቲያንች ኅብረት የሚደረገው የአንድ ስማንት ጸሎት በይፋ የሚጠናቀቅ ሲሆን በእለቱም አመሻሽ ላይ በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮና ከሌላ እህት አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ ምዕመናን በተገኙበት በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ መሪነት የምሽት ጸሎት እንደ ሚደረግም ለማወቅ ተችሉዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.