2017-01-23 14:46:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መንፈሳዊ ለውጥ ማለት የባሕሪ ለውጥ ማድረግ ማለት ነው ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 14/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ልምዳዊ ለሆነው ሳምንታዊ የጠቅላላ አስተምህሮ ለተሰበሰቡት ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ከመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት በፊት ባስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ገለጹት መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት ማለት ልማዳዊ የሆኑ ነገሮቻችንን መተው ማለት ሳይሆን የባሕሪ ለውጥ ማምጣት ማለት ነው ማለታቸው ተገልጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው ይህንን መልእክታቸውን ያስተላለፉት በእለቱ ባደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ ወቅት እንደነበረም የታወቀ ሲሆን በእለቱ በተነበበውና ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 4,12-23 ላይ በተወሰደው የወንጌላ ቃል ላይ ተመስርተው ያስተላለፉት አስተምህሮ ትኩረቱን ኢየሱስ በገሊላ ክፍለ ሀገር አስተምህሮውን በያፋ የጀመረበትን በመጥቀስ እንደ ነበረም የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጤኛ የሆነው ሰርጆ ቼንቶፋንቲ ዘግቡዋል።

ኢየሱስ የመጀመሪያ ስብከቱን የጀመረው አረማዊያን በሚበዙባት በቅፍርናሆም እንደ ነበረ በመጥቀስ አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በመልካ-ምድራዊ አቀማመጡዋ ምቹ ከሆነችው የኢየስሩሳሌም ከተማ ጋር፣ ቅፍርናሆም በንጽጽር ሲታይ ቅፍርናሆም “ሐይማኖታዊ ርኵሰት” ይታይባት የነበረ ከተማ እንደ ነበረና በተጨማሪም ከተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ እስራኤላዊያን የላሆኑ ነገዶች ይበዙባት የነበረ ከተማ መሆኑዋንም ገልጸዋል። “ምንም እንኳን ከገሊላ ለደኅንነታችን ታሪክ ከፍተኛ አስተዋጾ የሚያደርግ ታላላቅ ነገሮች እንደ ሚመነጩባት የሚጠበቅበት ከፍለ ሀገር ባትሆንም ቅሉ ነገር ግን በገሊላ ክፍለ ሀገር በምትገኘው የቅፍርናሆም ከተማ ነበረች በቀዳሚነት የኢየሱስን ብርሃን የተቀበለችው” በማለት ቅዱስነታቸው አስረድተዋል።

“የኢየሱስ መልእክት ‘የእግዚኣብሔር መንግሥት’ የሚለውን የመጥምቁ ዩሐንስን ስብከት ውጤታማነትን ያስታውሰናል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ‘ይህ አዲሱ መንግሥት” አዲስ ምድራዊ የሆነ ፖሌቲካዊ መግሥት ከመገናብት ጋር የተያያዘ አለምሆኑን ገልጸው ነገር ግን በእግዚኣብሔር እና በሕዝቦች መካከል የነበረውን ቃል ኪዳን ወደ ሙላኋት የሚያደርስ እና ሰላምን እና ፍትሕን የሚያበስር አዲስ መንፈስዊ መንግሥት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ከእግዚኣብሔር ጋር ያለንን የቃል ኪዳን ስምምነት አጥብቆ ለመያዝ ያስችለን ዘንድ እያንደንዳችን የአስተሳሰብ እና የኑሮ ዜይቤአችንን በመቀየር መንፈስዊ ለውጥ ማድረግ ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ጉዳይ ልብ ብላችሁ አዳምጡ መፈሳዊ ለውጥ ማምጣት ማለት ለማዳዊ የሆኑ ተግባሮቻችንን መቀየር ማለት ብቻ አይደለም፣ የአስተሳሰብ ዜይቤአችንንም መቀየር ማለት ጭምር ነው፣ ልማዳዊ የሆኑ ነገሮቻችንን መቀየር ብቻ ማለት ሳይሆን የባሕሪ ለውጥ ማድረግ ማለት” እንደ ሆነም በአጽኖት ገልጸዋል።

ኢየሱስ ሕዝቦቹ ወደ እርሱ እስኪመጡ ድረስ እጆቹን አጣጥፎ አይጠብቅም ነገር ግን ሕዝቦችን ለመገናኘት በቀዳሚነት ተነሳሽነትን በመውሰድ የጠፉ ሕዝቦቹን ሊፈልጋቸው እንደ ሚወጣ በመግልጸ አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ኢየሱስ የሚጠቀምበት ስልትና ዜይቤ መጥመቁ የሐንስ ይጠቀምበት ከነበረው ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

“ኢየሱስ አንደ አንድ ተጓዥ ነቢይ መሆንን ይመርጥ ነበረ እንጂ በአንድ ቦታ ብቻ ቆሞ ሕዝቦቹ ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ይጠባበቅ አልነበረም” ያሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ሁል ጊዜም ቢሆን በጉዞ ላይ እንደ ነበረ ጠቅሰው ለእዚህም እንደ ማረጋገጫ መውሰድ የምንችለው ኢየሱስ የመጀመሪያውን ሚስዮናዊ ተግባሩን ለማከናወን የወጣው በገሊላ በሕር አከባቢ እንደ ነበረና ከሕዝቡ ጋር በተለይም ከዐሣ አጥማጆች ጋር በመገናኘት እንደ ነበረም ጨምረው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። ኢየሱስም በእዚህ የመጀመሪያ ሚስዮናዊ ጉዞ ስለእግዚኣብሔር መንግሥት መምጣት ብቻ ሳይሆን የሰብክ የነበረው፣ ነገር ግን ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ የእዚህ የደኅንነት ተልዕኮ አጋር የሚሆኑ ሰዎችንም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ለመፈለግ እንደ ወጣም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው አስተምህሮዋቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ኢየሱስ የመጀመሪያ ሚስዮናዊ ተልዕኮውን ለመወጣት በሄደበት ወቅት ዐሣ አጥማጅ የነበሩ ሁለት ጥንድ ወንድማማቾችን ማለትም ስምሆን ጴጥሮስንና ወንድሙን እንድሪያስን እንዲሁም ያዕቆብ እና ወንድሙን ዩሐንስን በሥራ ላይ በነበሩበት ወቅት አግኝቱዋቸው እንዲከተሉት ጠርቶዋቸው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አውስተዋል።

“እነዚህ ሁለት ጥንድ ወንድማማቾች ይህ የጥሪ መልዕክት የደረሳቸው ልማዳዊ የሆነ ተግባራቸውን በማከናወን ላይ በነበሩበት ወቅት እንደ ነበረ” በመጥቀስ አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም የሚያሳየው ጌታ ለእኛ የሚገለጥልን በዓይነቱ ልዩ የሆነ ነገር በምንከናውንባቸው ወቅቶች ሳይሆን ነገር ግን በየቀኑ በሕይወታችን በምንፈጽማቸው የእለት ተእለት ተግባሮቻችንን በምንፈጽምበት ወቅቶች እንደ ሆነም ጨምረው ጠቅሰዋል።

እለታዊ በሆኑ ተግባሮቻችን ነው ጌታን መገናኘት የምንችለው፣ በእዚያም ወቅት እርሱ ራሱን ይገልጻል፣ ፍቅሩም ልባችን እንዲደርስ ያደርጋል፣ እለት በእለት በምናደርገው ተግባራችን ከእርሱ ጋር እንገናኛለን፣ ይህም ልባችንን እንድንቀይር ይረዳናል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ረገድ አራቱ የዐሣ አጥማጆች ለኢየሱስ ጥሪ ሰጥተውት የነበረው ምላሽ ቅጽበታዊ እንደ ነበረ ጠቅሰው በፍጥነትም “መረባቸውን ጥለው እርሱን ለመከተል ተነስተው እንደ ነበረውም ጨምረው ገልጸዋል።

እኛ ክርስቲያኖች ዛሬ ክርስትናችንን በደስታ ለማወጅ እና ለመመስከር መነሳሳት ይጠበቅብናል ምክንያቱም ይህ የምንመሰክረው እና የምናውጀው እምነታችን በታላቅ ትሕትናና ብርታት ለኢየሱስ ጥሪ በፍቅር ማላሽ በሰጡ ሐዋሪያት በደራ ስለተሰጠን ነው ያሉት ቅዱስነታቸው በባሕር አጠገብ በነበረችው እና በምንም ሁኔታ መልካም ነገር ይገኝባታል ተብሎ ከማይታሰብባት ከተማ የመጀመሪያዎቹ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መገኛ የሆነች የቀፍርናሆም ከተማ እንደ ነበረች ጨምረው ጠቅሰዋል።

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት ይህንን ማለትም ኢየሱስ የፈጸመውን ተግባር በቀዳሚነት በምንገነዘብበት ወቅት ሁሉ በእኛ ውስጥ ያለውን ቃል በመላው ዓለም ለማሰራጨት ፍላጎታችንን ያነሳሳል ካሉ ቡኋላ ኢየሱስ ለእኛ ያሳየውን ፍቅርና ርኅራኄን በምናስብበት ወቅቶች ሁሉ ቃሉን አስቸጋሪ በሚባሉ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ በማለፍ እንድንመሰክር ያበረታታናል ካሉ ቡኋላ የሰው ልጆች በሚኖሩበት ሥፍራ ሁሉ በመሄድ የወንጌልን ዘር በመዝራት የደኅንነት ፍሬ እስክያፈራ ድረስ መንከባከብ ይኖርብናል ካሉ ቡኋላ አስተምህሮዋቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.