2017-01-19 13:18:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የጥር 8/2009 ዓ.ም. ዜና።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ለማድዊ የሆነውን እና ዘወትር ርዕቡ እና እሁድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምዕመናን ጋር ከሚደግሙት የመልአከ  እግዚኣብሔር ጸሎት ቡኋላ ያሰተለለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን መጥመቁ ዩሐንስ ስለ ኢየሱስ በሰጠው ምስክርነት ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ዝርዝር ከእዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

“ቤተ ክርስቲያን” አሉ ቅዱስነታቸው “የተጠራችሁ መጥምቁ ዩሐንስ የሰጠውን አይነት ምስክርነት ለመስጠት ነው” ብለው የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ተግባሩዋ “እነሆ! የዓለምን ኃጢአት የሚያጠፋ የእግዚአብሔር በግ” በማለት ኢየሱስን ለሕዝቡ መግለጽ ይጠበቅባታል ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያን ስለ ራሷ ስታውጅ ሁልጊዜም ችግር ይገጥማታል፣ መንገዱዋንም ትስታለች፣ ወደ የት እንደ ምትሄድም አታውቅም” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ስለ ራሱዋ ሳይሆን ክርስቶስን ነው ማወጅ የሚጠበቅባት ምክንያቱም እርሱ እና እርሱ ብቻ ነው ማዳን የሚችለው፣ ሕዝቦቹን ከኋጥያት ቀንበር ነፃ ማውጣት የሚችለው እርሱ ብቻ ነው፣ እርሱ እና እርሱ ብቻ ናቸው  ሕዝቦቹን ነፃ በማውጣት ነጻነት ወደ ተሞላው ስፍራ መምራት የሚችለው እርሱ ብቻ ነው ካሉ ቡኋላ አስተምህሮዋቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.