2017-01-19 15:24:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የረዕቡ ጥር 10.01.17.


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በጥር 10/2009 ዓ.ም. ክርስቲያኖች ጠንክረው ከሰሩ በመካከላቸው  ሕብረት እና እርቅን መፍጥረ ይችላሉ ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ይህንን መልእክታቸውን ያስተላለፉት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ለተገኙ ምዕመናን እና ለሀገር ጎብኝዎች ባስተላለፉት ምልእክት ሲሆን መልእክታቸውም ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በጥር 10/2009 ዓ.ም. የተጀምረውን እና ለአንድ ሳምንት የሚቆየውን ለክርስቲያኖች ኅብረት የሚደረገው ጸሎት አስፈላጊነት እና ከእዚህ ቀደም የክርስቲያን ተስፋ በሚል አርዕስት ዙሪያ አድርገውት ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል ያካተተ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ዝርዝር ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመንካት ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ከሚለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ነገሮችን መመልከት ይኖርብናል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ክርስቲያኖች ህብረታቸውን ለማጠናከር አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.